Check out the new design

Ibisobanuro bya qoran ntagatifu - Ibisobanuro bya Qur'an Ntagatifu mu rurimi rw'iki Amhari - Ikigo Nyafurika. * - Ishakiro ry'ibisobanuro

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Ibisobanuro by'amagambo Isura: Al An’am   Umurongo:

አል-አንዓም

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَجَعَلَ ٱلظُّلُمَٰتِ وَٱلنُّورَۖ ثُمَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِرَبِّهِمۡ يَعۡدِلُونَ
1.ምስጋና ሁሉ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረ ጨለማዎችንና ብርሃንን ላደረገው ለአላህ የተገባ ነው:: ከዚያም እነዚያ በእርሱ የካዱ ሁሉ ጣዖታትን ከጌታቸው ጋር ያስተካክላሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن طِينٖ ثُمَّ قَضَىٰٓ أَجَلٗاۖ وَأَجَلٞ مُّسَمًّى عِندَهُۥۖ ثُمَّ أَنتُمۡ تَمۡتَرُونَ
2. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም የሞት ጊዜን የወሰነ ነው:: እርሱም ዘንድ ለትንሳኤ የተወሰነ ጊዜ አለ:: ከዚያም እናንተ በመቀስቀሳችሁ ትጠራጠራላችሁን?
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهُوَ ٱللَّهُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَفِي ٱلۡأَرۡضِ يَعۡلَمُ سِرَّكُمۡ وَجَهۡرَكُمۡ وَيَعۡلَمُ مَا تَكۡسِبُونَ
3. እርሱም ያ በሰማያትም በምድርም ሊገዙት የሚገባው አላህ ነው:: (ሰዎች ሆይ!) ሚስጥራችሁንም ሆነ ግልፃችሁን ጠንቅቆ ያውቃል። የምትሰሩትን ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمَا تَأۡتِيهِم مِّنۡ ءَايَةٖ مِّنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِمۡ إِلَّا كَانُواْ عَنۡهَا مُعۡرِضِينَ
⒋ ከጌታቸው አናቅጽ አንዱም አይመጣላቸዉም ከእርሱ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَقَدۡ كَذَّبُواْ بِٱلۡحَقِّ لَمَّا جَآءَهُمۡ فَسَوۡفَ يَأۡتِيهِمۡ أَنۢبَٰٓؤُاْ مَا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
5. ቁርኣን በመጣላቸው ጊዜም በእርግጥ አስተባበሉ:: ግን የእዚያ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ነገር ዜናዎች ቅጣት ይመጣባቸዋል።
Ibisobanuro by'icyarabu:
أَلَمۡ يَرَوۡاْ كَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِن قَبۡلِهِم مِّن قَرۡنٖ مَّكَّنَّٰهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَا لَمۡ نُمَكِّن لَّكُمۡ وَأَرۡسَلۡنَا ٱلسَّمَآءَ عَلَيۡهِم مِّدۡرَارٗا وَجَعَلۡنَا ٱلۡأَنۡهَٰرَ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمۡ فَأَهۡلَكۡنَٰهُم بِذُنُوبِهِمۡ وَأَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قَرۡنًا ءَاخَرِينَ
6. ከበፊታቸው ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች መካከል ብዙዎቹን ማጥፋታችንን አላዩምን? ለእናንተ ያላስመቸነውን ለእነርሱ በምድር ውስጥ አስመቸናቸው:: በእነርሱም ላይ ዝናብን የተከታተለ ሲሆን ላክን:: ወንዞችንም በስራቸው እንዲፈሱ አደረግን:: በኃጢአቶቻቸዉም ምክንያት አጠፋናቸው:: ከኋላቸዉም ሌሎችን ሰዎች በየክፍለ ዘመኑ አስገኘን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَوۡ نَزَّلۡنَا عَلَيۡكَ كِتَٰبٗا فِي قِرۡطَاسٖ فَلَمَسُوهُ بِأَيۡدِيهِمۡ لَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٞ
7. በእነርሱ ላይ በወረቀት የተፃፈን መጽሐፍ ባወረድንና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ ከሓዲያን «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።» ባሉ ነበር::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَقَالُواْ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ مَلَكٞۖ وَلَوۡ أَنزَلۡنَا مَلَكٗا لَّقُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ ثُمَّ لَا يُنظَرُونَ
8. «በእርሱ (በሙሐመድ) ላይ መልአክ ለምን አይወረድለትም?» አሉ። ነገር ግን መላዕክን ባወረድንለትና (ባያምኑ ኖሮ) የጥፋታቸው ነገር በተፈረደ ነበር:: ከዚያም አይቆዩም ነበር::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَوۡ جَعَلۡنَٰهُ مَلَكٗا لَّجَعَلۡنَٰهُ رَجُلٗا وَلَلَبَسۡنَا عَلَيۡهِم مَّا يَلۡبِسُونَ
9. መልዕክተኛውን ከመላዕክት መካከል ባደረግነው ኖሮ ወንድ ሰው አድርገን በመላክ በእነርሱ ላይ የሚያመሳስሉትን ነገር ባመሳሰልንባቸው ነበር።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَقَدِ ٱسۡتُهۡزِئَ بِرُسُلٖ مِّن قَبۡلِكَ فَحَاقَ بِٱلَّذِينَ سَخِرُواْ مِنۡهُم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት በነበሩ መልዕክተኞችም ላይ ተላግጧል:: እናም በእነዚያ ባላገጡት ላይ ያላገጡበት ውጤት በእነርሱ ላይ ተፈጽሟል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ سِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ ثُمَّ ٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُكَذِّبِينَ
11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ከሓዲያንን) «በምድር ላይ ሂዱና የእነዚያን የአስተባባዮችን መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ።» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُل لِّمَن مَّا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ قُل لِّلَّهِۚ كَتَبَ عَلَىٰ نَفۡسِهِ ٱلرَّحۡمَةَۚ لَيَجۡمَعَنَّكُمۡ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَا رَيۡبَ فِيهِۚ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የማን ነው?» በላቸውም: «የአላህ ብቻ ነው። አላህ በራሱ ላይ እዝነትን ፃፈ:: በዚያ ጥርጥር በሌለበት በትንሳኤ ቀን ይሰበስባችኋል:: እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ማለት እነርሱው ናቸው። እናም አያምኑም።
Ibisobanuro by'icyarabu:
۞ وَلَهُۥ مَا سَكَنَ فِي ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِۚ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
13. «በሌሊትም ሆነ በቀን ጸጥ ያለው ሁሉ የእርሱው ነው:: እርሱም ሰሚውና አዋቂው ነው።»
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيّٗا فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَهُوَ يُطۡعِمُ وَلَا يُطۡعَمُۗ قُلۡ إِنِّيٓ أُمِرۡتُ أَنۡ أَكُونَ أَوَّلَ مَنۡ أَسۡلَمَۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከሆነው አላህ እርሱ ፍጡርን የሚመግብና ለራሱ የማይመገብ አምላክ ሲሆን ሌላን አምላክ እይዛለሁን?» በላቸው። «እኔ መጀመሪያ ትዕዛዝን ከተቀበለ ሰው እንድሆን ታዘዝኩ:: ‹ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትሁን።› ተብያለሁ።» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ إِنِّيٓ أَخَافُ إِنۡ عَصَيۡتُ رَبِّي عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ
15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ በጌታዬ ላይ ባምጽ የዚያን የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
مَّن يُصۡرَفۡ عَنۡهُ يَوۡمَئِذٖ فَقَدۡ رَحِمَهُۥۚ وَذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡمُبِينُ
16. በዚያ ቀን ከእርሱ ላይ ቅጣት የሚመለስለት ሰው ሁሉ በእርግጥ አላህ አዘነለት:: ይህም ግልጽ ስኬት ነው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِن يَمۡسَسۡكَ ٱللَّهُ بِضُرّٖ فَلَا كَاشِفَ لَهُۥٓ إِلَّا هُوَۖ وَإِن يَمۡسَسۡكَ بِخَيۡرٖ فَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ችግር ቢያደርስብህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ማንም አስወጋጅ የለም:: በጎ ነገርን ቢሰጥህም እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهُوَ ٱلۡقَاهِرُ فَوۡقَ عِبَادِهِۦۚ وَهُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡخَبِيرُ
18. እርሱ ከባሮቹ በላይ ሲሆን ሁሉን አሸናፊ ነው:: እርሱ ጥበበኛውና ውስጠ አዋቂው ነው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ أَيُّ شَيۡءٍ أَكۡبَرُ شَهَٰدَةٗۖ قُلِ ٱللَّهُۖ شَهِيدُۢ بَيۡنِي وَبَيۡنَكُمۡۚ وَأُوحِيَ إِلَيَّ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانُ لِأُنذِرَكُم بِهِۦ وَمَنۢ بَلَغَۚ أَئِنَّكُمۡ لَتَشۡهَدُونَ أَنَّ مَعَ ٱللَّهِ ءَالِهَةً أُخۡرَىٰۚ قُل لَّآ أَشۡهَدُۚ قُلۡ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞ وَإِنَّنِي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تُشۡرِكُونَ
19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከምስክርነት ሁሉ ይበልጥ ታላቁ የትኛው ነው?» በላቸው። «አላህ፤ በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ ነው። ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውንም ሁሉ ላስፈራራበት ወደ እኔ ተወረደ:: ከአላህ ጋር ሌሎች አማልክት መኖራቸውን እናንተ ትመሰክራላቸሁን?» በላቸው:: «እኔ ግን ፈጽሞ በዚህ አልመሰክርም።» በላቸው:: «እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እኔም በአላህ ከምታጋሩት ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
ٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ يَعۡرِفُونَهُۥ كَمَا يَعۡرِفُونَ أَبۡنَآءَهُمُۘ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
20. እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው አይሁድና ክርስቲያኖች ልክ ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ ሁሉ ሙሐመድንም በትክክል ያውቁታል:: እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩት እነርሱ ፈጽሞ አያምኑም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوۡ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ
21. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአናቅጽ ካስተባበለ ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? እነሆ በደለኞች አይድኑም።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَيَوۡمَ نَحۡشُرُهُمۡ جَمِيعٗا ثُمَّ نَقُولُ لِلَّذِينَ أَشۡرَكُوٓاْ أَيۡنَ شُرَكَآؤُكُمُ ٱلَّذِينَ كُنتُمۡ تَزۡعُمُونَ
22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሁላቸውንም በምንሰበሰብበትና ከዚያም ለእነዚያም በአላህ ላጋሩት፤ «‹እነዚያም ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው› ብላችሁ ታስቧቸው የነበሩት ተጋሪዎቻችሁ የት ናቸው?» የምንልበትን ቀን (አስታውስ)።
Ibisobanuro by'icyarabu:
ثُمَّ لَمۡ تَكُن فِتۡنَتُهُمۡ إِلَّآ أَن قَالُواْ وَٱللَّهِ رَبِّنَا مَا كُنَّا مُشۡرِكِينَ
23. ከዚያም የፊትና መልሳቸው «በጌታችን በአላህ ይሁንብን አጋሪዎች አልነበርንም።» ማለት እንጂ ሌላ አይሆንም።
Ibisobanuro by'icyarabu:
ٱنظُرۡ كَيۡفَ كَذَبُواْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡۚ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በነፍሶቻቸው ላይ እንዴት እንደዋሹና ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ሁሉ ከእነርሱ እንዴት እንደተሰወረባቸው ተመልከት::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمِنۡهُم مَّن يَسۡتَمِعُ إِلَيۡكَۖ وَجَعَلۡنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ أَكِنَّةً أَن يَفۡقَهُوهُ وَفِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٗاۚ وَإِن يَرَوۡاْ كُلَّ ءَايَةٖ لَّا يُؤۡمِنُواْ بِهَاۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوكَ يُجَٰدِلُونَكَ يَقُولُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
25. ከእነርሱ መካከል ወደ አንተ የሚያዳምጥ ሰው አለ:: በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሽፋኖችን፤ በጆሮዎቻቸዉም ላይ እንዳይሰሙት ድንቁርናን አደረግን:: ተዐምርን ሁሉ እንኳን ቢያዩ በእርሷ አያምኑም:: ወደ አንተ በመጡ ጊዜ የሚከራከሩህ ሆነው እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች «ይህ ቁርኣን የቀድሞዎቹ ሰዎች ጹሑፍ ተረቶች ስብስብ እንጂ ሌላ አይደለም።» ይላሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهُمۡ يَنۡهَوۡنَ عَنۡهُ وَيَنۡـَٔوۡنَ عَنۡهُۖ وَإِن يُهۡلِكُونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمۡ وَمَا يَشۡعُرُونَ
26. እነርሱም ሰዎችን ከእርሱ ይከልክላሉ፤ ከእርሱም ይርቃሉ፤ በዚህም ተግባራቸው ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላን አያጠፉም:: ግን አያውቁም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذۡ وُقِفُواْ عَلَى ٱلنَّارِ فَقَالُواْ يَٰلَيۡتَنَا نُرَدُّ وَلَا نُكَذِّبَ بِـَٔايَٰتِ رَبِّنَا وَنَكُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእሳትም ላይ እንዲቆሙ በተደረጉ ጊዜ «ምን ነው ወደ ምድረ ዓለም በተመለስንና በጌታችን አናቅጽ ባላስተባበልን ከትክክለኛ አማኞችም ጋር በሆንን ዋ! ምኞታችን።» ባሉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (የሚያስደነግጥህን ነገር ባየህ ነበር)
Ibisobanuro by'icyarabu:
بَلۡ بَدَا لَهُم مَّا كَانُواْ يُخۡفُونَ مِن قَبۡلُۖ وَلَوۡ رُدُّواْ لَعَادُواْ لِمَا نُهُواْ عَنۡهُ وَإِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ
28. ይልቁንስ ከዚህ በፊት ይደብቁት የነበሩት ነገር ሁሉ ለእነርሱ ተገለጸ:: ወደ ምድረ ዓለም በተመለሱም ኖሮ ወደ ተከለከሉት ነገር በተመለሱ ነበር:: እነርሱ ሐሰተኞች ናቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَقَالُوٓاْ إِنۡ هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنۡيَا وَمَا نَحۡنُ بِمَبۡعُوثِينَ
29. «ሕይወት ማለት ቅርቢቱ ሕይወታችን እንጂ ሌላ አይደለችም:: እኛም ፈጽሞ ተቀስቃሾች አይደለንም።» አሉ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذۡ وُقِفُواْ عَلَىٰ رَبِّهِمۡۚ قَالَ أَلَيۡسَ هَٰذَا بِٱلۡحَقِّۚ قَالُواْ بَلَىٰ وَرَبِّنَاۚ قَالَ فَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡفُرُونَ
30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጌታቸው ዘንድ ለምርመራ እንዲቆሙ በተደረጉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ባየህ ነበር::) «ይህ እውነት አይደለምን?» ይላቸዋል:: እነርሱም «በጌታችን ይሁንብን እውነት ነው።» ይላሉ:: «እናም ትክዱት በነበራችሁት ምክንያት ቅጣቱን ቅመሱ።» ይላቸዋል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَدۡ خَسِرَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِلِقَآءِ ٱللَّهِۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَتۡهُمُ ٱلسَّاعَةُ بَغۡتَةٗ قَالُواْ يَٰحَسۡرَتَنَا عَلَىٰ مَا فَرَّطۡنَا فِيهَا وَهُمۡ يَحۡمِلُونَ أَوۡزَارَهُمۡ عَلَىٰ ظُهُورِهِمۡۚ أَلَا سَآءَ مَا يَزِرُونَ
31. እነዚያ ከአላህ ጋር መገናኘትን ያስተባበሉ ሁሉ በእርግጥ ከሰሩ:: ስዓቲቱም በድንገት በመጣችባቸው ጊዜ እነርሱ ኃጢአቶቻቸውን በጀርባዎቻቸው ላይ የሚሸከሙ ሲሆኑ «በምድረ ዓለም ባጓደልነው ነገር ላይ ዋ ጥፋታችን!» ይላሉ። አዋጅ ያ የሚሸከሙት ነገር ምንኛ ከፋ!
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمَا ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَآ إِلَّا لَعِبٞ وَلَهۡوٞۖ وَلَلدَّارُ ٱلۡأٓخِرَةُ خَيۡرٞ لِّلَّذِينَ يَتَّقُونَۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ
32. የቅርቢቱ ሕይወት ማለት ጨዋታና ላግጣ እንጂ ሌላ አይደለችም። የመጨረሻይቱ አገር (ገነት) ግን ለእነዚያ ለሚጠነቀቁት ሰዎች ሁሉ በጣም በላጭ ናት። አታውቁምን? (አትገነዘቡምን)?
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَدۡ نَعۡلَمُ إِنَّهُۥ لَيَحۡزُنُكَ ٱلَّذِي يَقُولُونَۖ فَإِنَّهُمۡ لَا يُكَذِّبُونَكَ وَلَٰكِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ يَجۡحَدُونَ
33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ የሚሉህ ነገር እንደሚያሳዝንህ በእርግጥ እናውቃለን:: እነርሱ በእርግጥ አያስተባብሉህም:: ግን በዳዮች በአላህ አናቅጽ ይክዳሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَقَدۡ كُذِّبَتۡ رُسُلٞ مِّن قَبۡلِكَ فَصَبَرُواْ عَلَىٰ مَا كُذِّبُواْ وَأُوذُواْ حَتَّىٰٓ أَتَىٰهُمۡ نَصۡرُنَاۚ وَلَا مُبَدِّلَ لِكَلِمَٰتِ ٱللَّهِۚ وَلَقَدۡ جَآءَكَ مِن نَّبَإِيْ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከበፊትህ የነበሩት መልዕክተኞች ተስተባብለዋል:: በተስተባበሉበትም ነገርና በተሰቃዩት ላይ እርዳታችን እስከመጣላቸው ድረስ ታገሱ:: የአላህን ቃላት የሚለዉጥ የለም:: ከመልዕክተኞቹም ወሬ (የምትረጋጋበት) በእርግጥ መጣልህ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِن كَانَ كَبُرَ عَلَيۡكَ إِعۡرَاضُهُمۡ فَإِنِ ٱسۡتَطَعۡتَ أَن تَبۡتَغِيَ نَفَقٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ أَوۡ سُلَّمٗا فِي ٱلسَّمَآءِ فَتَأۡتِيَهُم بِـَٔايَةٖۚ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَمَعَهُمۡ عَلَى ٱلۡهُدَىٰۚ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡجَٰهِلِينَ
35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢስላምን መተዋቸው ባንተ ላይ ከባድ ቢሆንብህም በምድር ውስጥ ቀዳዳን ወይም በሰማይ ውስጥ መሰላልን ልትፈልግና ተዓምር ልታመጣላቸው ከቻልክ ሞክር:: አላህ በፈለገ ኖሮ ሁሉንም በቅኑ መንገድ ላይ በሰበሰባቸው ነበር:: ስለዚህ ከተሳሳቱት ሰዎች በፍጹም አትሁን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
۞ إِنَّمَا يَسۡتَجِيبُ ٱلَّذِينَ يَسۡمَعُونَۘ وَٱلۡمَوۡتَىٰ يَبۡعَثُهُمُ ٱللَّهُ ثُمَّ إِلَيۡهِ يُرۡجَعُونَ
36. ጥሪን የሚቀበሉት እነዚያ የሚሰሙት ብቻ ናቸው:: ሙታንማ አላህ ይቀሰቅሳቸዋል:: ከዚያም ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَقَالُواْ لَوۡلَا نُزِّلَ عَلَيۡهِ ءَايَةٞ مِّن رَّبِّهِۦۚ قُلۡ إِنَّ ٱللَّهَ قَادِرٌ عَلَىٰٓ أَن يُنَزِّلَ ءَايَةٗ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን «ከጌታው በእርሱ ላይ ለምን ተአምር አልተወረደለትም?» አሉ:: «አላህ ተአምርን ለማውረድ ቻይ ነው:: ግን አብዛኞቻቸው ይህን እውነታ አያውቁም።» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمَا مِن دَآبَّةٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا طَٰٓئِرٖ يَطِيرُ بِجَنَاحَيۡهِ إِلَّآ أُمَمٌ أَمۡثَالُكُمۚ مَّا فَرَّطۡنَا فِي ٱلۡكِتَٰبِ مِن شَيۡءٖۚ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ يُحۡشَرُونَ
38. በምድር ላይ የሚሄድ ተንቀሳቃሽም ሆነ በሁለት ክንፎቹ የሚበር ሁሉ መሰሎቻችሁ ሕዝቦች እንጂ ሌላ አይደሉም:: በመጽሐፉ ውስጥ ምንንም ነገር አልተውንም:: ከዚያ ሁሉም ወደ ጌታቸው ይሰበሰባሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا صُمّٞ وَبُكۡمٞ فِي ٱلظُّلُمَٰتِۗ مَن يَشَإِ ٱللَّهُ يُضۡلِلۡهُ وَمَن يَشَأۡ يَجۡعَلۡهُ عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
39. እነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉ ሁሉ እውነትን የማይሰሙ ደንቆሮዎች፤ ሐቅን የማይናገሩ ዲዳዎችና በጨለማዎች ውስጥ ያሉ ናቸው:: አላህ መጥመሙን የሚሻበትን ሰው ያጠመዋል:: ወደ ቀናው መንገድ መመራቱን የሚሻለትን ሰው ደግሞ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ያደርገዋል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ أَرَءَيۡتَكُمۡ إِنۡ أَتَىٰكُمۡ عَذَابُ ٱللَّهِ أَوۡ أَتَتۡكُمُ ٱلسَّاعَةُ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ تَدۡعُونَ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የአላህ ቅጣት ቢመጣባችሁ ወይም ትንሳኤ ብትመጣባችሁ ከአላህ ሌላ ትጠራላችሁን? እውነተኞች ከሆናችሁ (እስኪ ንገሩኝ።)» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
بَلۡ إِيَّاهُ تَدۡعُونَ فَيَكۡشِفُ مَا تَدۡعُونَ إِلَيۡهِ إِن شَآءَ وَتَنسَوۡنَ مَا تُشۡرِكُونَ
41. «በፍፁም። እውነታው እርሱን ብቻ ትጠራላችሁ:: ቢሻ ወደ እርሱ የምትጠሩበትን ነገር ያስወግድላችኋልና የምታጋሩትንም ሁሉ ትረሱታላችሁ።» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَآ إِلَىٰٓ أُمَمٖ مِّن قَبۡلِكَ فَأَخَذۡنَٰهُم بِٱلۡبَأۡسَآءِ وَٱلضَّرَّآءِ لَعَلَّهُمۡ يَتَضَرَّعُونَ
42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለነበሩት ሕዝቦች አያሌ መልዕክተኞችን በእርግጥ ላክን:: (ከዚያም እንቢተኛ ሆኑ::) ለእኛ ይተናነሱም ዘንድ በድህነትና በችግር ቀጣናቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَلَوۡلَآ إِذۡ جَآءَهُم بَأۡسُنَا تَضَرَّعُواْ وَلَٰكِن قَسَتۡ قُلُوبُهُمۡ وَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
43. ታዲያ ቅጣታችን በመጣባቸው ጊዜ አይተናነሱም ኖሯልን? ነገር ግን ልቦቻቸው ደረቁ:: ይሰሩት የነበሩትንም መጥፎ ነገር ሰይጣን መልካም ነገር አስመስሎ አሳያቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَلَمَّا نَسُواْ مَا ذُكِّرُواْ بِهِۦ فَتَحۡنَا عَلَيۡهِمۡ أَبۡوَٰبَ كُلِّ شَيۡءٍ حَتَّىٰٓ إِذَا فَرِحُواْ بِمَآ أُوتُوٓاْ أَخَذۡنَٰهُم بَغۡتَةٗ فَإِذَا هُم مُّبۡلِسُونَ
44. በእርሱ ይገሰጹበት የነበረውን ነገር በዘነጉ ጊዜ ለእነርሱ የሁሉን ነገር ደጃፎችን ከፈትንላቸውና በኑሮ አስመቸናቸው:: በተሰጡትም ነገር በተደሰቱ ጊዜ በድንገት ያዝናቸው:: ወዲያውኑም እነርሱ ተስፋ ቆራጮች ሆኑ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَقُطِعَ دَابِرُ ٱلۡقَوۡمِ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْۚ وَٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
45. የእነዚያ የበደሉት ሕዝቦች መጨረሻ ተቆረጠ:: ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِنۡ أَخَذَ ٱللَّهُ سَمۡعَكُمۡ وَأَبۡصَٰرَكُمۡ وَخَتَمَ عَلَىٰ قُلُوبِكُم مَّنۡ إِلَٰهٌ غَيۡرُ ٱللَّهِ يَأۡتِيكُم بِهِۗ ٱنظُرۡ كَيۡفَ نُصَرِّفُ ٱلۡأٓيَٰتِ ثُمَّ هُمۡ يَصۡدِفُونَ
46.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እስቲ ንገሩኝ አላህ መስሚያችሁንና ማያዎቻችሁን ቢወሰድባችሁና በልቦቻችሁ ላይ ቢያትም ከአላህ ሌላ እርሱኑ የሚያመጣላችሁ አምላክ ማን ነው?» በላቸው:: አናቅጽን እንዴት እንደምናብራራና ከዚያም እነርሱ እንዴት መንገዱን እንደሚስቱ ተመልከት::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ أَرَءَيۡتَكُمۡ إِنۡ أَتَىٰكُمۡ عَذَابُ ٱللَّهِ بَغۡتَةً أَوۡ جَهۡرَةً هَلۡ يُهۡلَكُ إِلَّا ٱلۡقَوۡمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እስቲ ንገሩኝ የአላህ ቅጣት ድንገት ወይም በይፋ ቢመጣባችሁ ከአመጸኛ ህዝቦች ሌላ ይጠፋልን?» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمَا نُرۡسِلُ ٱلۡمُرۡسَلِينَ إِلَّا مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَۖ فَمَنۡ ءَامَنَ وَأَصۡلَحَ فَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ
48. መልዕክተኞችንም በመልካም አብሳሪና ከመጥፎ አስፈራሪ አድርገን እንጂ አንልክም:: እናም በእነርሱ ያመኑና በጎ ተግባርን የሰሩ ሁሉ ስጋት የለባቸዉም። አይተክዙምም።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يَمَسُّهُمُ ٱلۡعَذَابُ بِمَا كَانُواْ يَفۡسُقُونَ
49. እነዚያ አናቅጻችንን ያስተባበሉት ደግሞ በአመፃቸው ምክንያት ቅጣት ያገኛቸዋል።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمۡ عِندِي خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعۡلَمُ ٱلۡغَيۡبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمۡ إِنِّي مَلَكٌۖ إِنۡ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَيَّۚ قُلۡ هَلۡ يَسۡتَوِي ٱلۡأَعۡمَىٰ وَٱلۡبَصِيرُۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ
50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልላችሁም:: ሩቅ ሚስጥርንም አላውቅም:: መልዓክ ነኝም አልልም:: ወደ እኔ የሚወርድልኝን መልዕክት ብቻ እንጂ ሌላን አልከተልም።» በላቸው። «እውርና የሚያይ ይስተካከላሉን? አታስተነትኑምን!» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَأَنذِرۡ بِهِ ٱلَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحۡشَرُوٓاْ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ لَيۡسَ لَهُم مِّن دُونِهِۦ وَلِيّٞ وَلَا شَفِيعٞ لَّعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ
51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከአላህ ሌላ ወዳጅና አማላጅ የሌላቸው ሲሆኑ ወደ ጌታቸው መሰብሰብን የሚፈሩትን ሰዎች ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ(ቁርኣን) አስፈራራ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَا تَطۡرُدِ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ رَبَّهُم بِٱلۡغَدَوٰةِ وَٱلۡعَشِيِّ يُرِيدُونَ وَجۡهَهُۥۖ مَا عَلَيۡكَ مِنۡ حِسَابِهِم مِّن شَيۡءٖ وَمَا مِنۡ حِسَابِكَ عَلَيۡهِم مِّن شَيۡءٖ فَتَطۡرُدَهُمۡ فَتَكُونَ مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያን የጌታቸውን ፊት የሚሹ ሆነው በጧትና በማታ የሚጠሩትን አማኞች ከአጠገብህ አታባር:: እነርሱን መቆጣጠር ባንተ ላይ ምንም የለብህም:: አንተንም መቆጣጠር በእነርሱ ላይ ምንም የለባቸዉም::ታባርራቸውና ከበደለኞችም ትኾን ዘንድ (አታባር)።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَكَذَٰلِكَ فَتَنَّا بَعۡضَهُم بِبَعۡضٖ لِّيَقُولُوٓاْ أَهَٰٓؤُلَآءِ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَيۡهِم مِّنۢ بَيۡنِنَآۗ أَلَيۡسَ ٱللَّهُ بِأَعۡلَمَ بِٱلشَّٰكِرِينَ
53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁም «ከመካከላችን አላህ በእነርሱ ላይ ችሮታውን የለገሳቸው እነዚህ ናቸውን?» ይሉ ዘንድ ከፊላቸውን በከፊሎች ሞከርን:: አላህ አመስጋኞቹን ከሁሉም በላይ አዋቂ አይደለምን?
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِذَا جَآءَكَ ٱلَّذِينَ يُؤۡمِنُونَ بِـَٔايَٰتِنَا فَقُلۡ سَلَٰمٌ عَلَيۡكُمۡۖ كَتَبَ رَبُّكُمۡ عَلَىٰ نَفۡسِهِ ٱلرَّحۡمَةَ أَنَّهُۥ مَنۡ عَمِلَ مِنكُمۡ سُوٓءَۢا بِجَهَٰلَةٖ ثُمَّ تَابَ مِنۢ بَعۡدِهِۦ وَأَصۡلَحَ فَأَنَّهُۥ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በተዐምራታችን የሚያምኑት ሰዎች ሁሉ ወደ አንተ በመጡ ጊዜ «ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን:: ጌታችን በራሱ ላይ እዝነትን ፃፈ:: እነሆ ከናንተ ውስጥ ስህተትን ስራ የሰራና ከዚያ ተጸጽቶ ወዲያውኑ ስራውን ላሳመረ እርሱ (አላህ) መሀሪና አዛኝ ነው።» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَكَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ وَلِتَسۡتَبِينَ سَبِيلُ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
55. ልክ እንደዚሁም እውነቱ እንዲገለጽና የወንጀለኞችም መንገድ ትብራራ ዘንድ አናቅጽን እንገልፃለን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ إِنِّي نُهِيتُ أَنۡ أَعۡبُدَ ٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِۚ قُل لَّآ أَتَّبِعُ أَهۡوَآءَكُمۡ قَدۡ ضَلَلۡتُ إِذٗا وَمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُهۡتَدِينَ
56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸውን (ባዕድ አማልክት) ከመገዛት ተከልክያለሁ።» በላቸው። «ዝንባሌያችሁንም አልከተልም:: ያን ካደረኩኝ በእርግጥ ተሳሳትኩ:: እኔም ከተመሪዎቹ አይደለሁም።» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ إِنِّي عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَكَذَّبۡتُم بِهِۦۚ مَا عِندِي مَا تَسۡتَعۡجِلُونَ بِهِۦٓۚ إِنِ ٱلۡحُكۡمُ إِلَّا لِلَّهِۖ يَقُصُّ ٱلۡحَقَّۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلۡفَٰصِلِينَ
57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እኔ ከጌታዬ በመጣልኝ ግልጽ ማስረጃ ላይ ነኝ:: እናንተ ግን በእርሱ አስተባበላችሁ:: ያ የምትቻኮሉበት ቅጣት ውሳኔ እኔ ዘንድ አይደለም:: ፍርዱ ለአላህ ብቻ ነው:: አላህ እውነቱን ይፈርዳል:: እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነውና።» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُل لَّوۡ أَنَّ عِندِي مَا تَسۡتَعۡجِلُونَ بِهِۦ لَقُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ بَيۡنِي وَبَيۡنَكُمۡۗ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِٱلظَّٰلِمِينَ
58. «ያ የምትቻኮሉበት ቅጣት እኔ ዘንድ በሆነ ኖሮ በእኔና በእናንተ መካከል ነገሩ (ቅጣታችሁ) በተፈጸመ ነበር:: አላህ በደለኞችን አዋቂ ነው።» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
۞ وَعِندَهُۥ مَفَاتِحُ ٱلۡغَيۡبِ لَا يَعۡلَمُهَآ إِلَّا هُوَۚ وَيَعۡلَمُ مَا فِي ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِۚ وَمَا تَسۡقُطُ مِن وَرَقَةٍ إِلَّا يَعۡلَمُهَا وَلَا حَبَّةٖ فِي ظُلُمَٰتِ ٱلۡأَرۡضِ وَلَا رَطۡبٖ وَلَا يَابِسٍ إِلَّا فِي كِتَٰبٖ مُّبِينٖ
59. የሩቅ ሚስጥሮች መክፈቻዎች ሁሉ እርሱ ዘንድ ብቻ ናቸው:: ከእርሱ በስተቀር ማንም አያውቃቸዉም:: በየብስና በባህር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: አንዲትም ቅጠል አትረግፍም አላህ የሚያውቃት ብትሆን እንጂ:: በመሬት ጨለማዎች ውስጥ ቅንጣት እርጥብም ሆነ ደረቅ አንድም ነገር የለም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢሆን እንጂ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهُوَ ٱلَّذِي يَتَوَفَّىٰكُم بِٱلَّيۡلِ وَيَعۡلَمُ مَا جَرَحۡتُم بِٱلنَّهَارِ ثُمَّ يَبۡعَثُكُمۡ فِيهِ لِيُقۡضَىٰٓ أَجَلٞ مُّسَمّٗىۖ ثُمَّ إِلَيۡهِ مَرۡجِعُكُمۡ ثُمَّ يُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
60. እርሱ (አላህ) ያ በሌሊት የሚያስተኛችሁ በቀን የሰራችሁትንም ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈጸም ዘንድ በቀን ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ ነው:: ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እርሱ ብቻ ነው:: ከዚያም ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ሁሉ ይነግራችኋል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهُوَ ٱلۡقَاهِرُ فَوۡقَ عِبَادِهِۦۖ وَيُرۡسِلُ عَلَيۡكُمۡ حَفَظَةً حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَحَدَكُمُ ٱلۡمَوۡتُ تَوَفَّتۡهُ رُسُلُنَا وَهُمۡ لَا يُفَرِّطُونَ
61. እርሱ ከባሮቹ በላይ ሲሆን ሁሉን አሸናፊ ነው:: በእናንተ ላይም ተጠባባቂዎች መላዕክትን ይልካል:: አንዳችሁንም የሞት ሰዓቱ በመጣበት ጊዜ የሞት መልዕክተኞቻችን ትዕዛዛትን የማያጓድሉ ሲሆኑ ይገድሉታል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
ثُمَّ رُدُّوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ مَوۡلَىٰهُمُ ٱلۡحَقِّۚ أَلَا لَهُ ٱلۡحُكۡمُ وَهُوَ أَسۡرَعُ ٱلۡحَٰسِبِينَ
62. ከዚያም እውነተኛ ወደ ሆነው ጌታቸው ወደ አላህ ይመለሳሉ:: (ሰዎች ሆይ!) አስትዉሉ! አዋጅ ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ مَن يُنَجِّيكُم مِّن ظُلُمَٰتِ ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِ تَدۡعُونَهُۥ تَضَرُّعٗا وَخُفۡيَةٗ لَّئِنۡ أَنجَىٰنَا مِنۡ هَٰذِهِۦ لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّٰكِرِينَ
63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ ከየብስና ከባህር ጨለማዎች በግልጽና በሚስጢር ‹ከዚህ ቢያድነን ከአመስጋኞች እንሆናለን› ስትሉ የምትጠሩት ስትሆኑ የሚያድናችሁ ማን ነው?» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلِ ٱللَّهُ يُنَجِّيكُم مِّنۡهَا وَمِن كُلِّ كَرۡبٖ ثُمَّ أَنتُمۡ تُشۡرِكُونَ
64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ከእርሷና ከጭንቅም ሁሉ ያድናችኋል:: ከዚያ እናንተ በእሱ ባዕድ አምላክን ታጋራላችሁ።» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ هُوَ ٱلۡقَادِرُ عَلَىٰٓ أَن يَبۡعَثَ عَلَيۡكُمۡ عَذَابٗا مِّن فَوۡقِكُمۡ أَوۡ مِن تَحۡتِ أَرۡجُلِكُمۡ أَوۡ يَلۡبِسَكُمۡ شِيَعٗا وَيُذِيقَ بَعۡضَكُم بَأۡسَ بَعۡضٍۗ ٱنظُرۡ كَيۡفَ نُصَرِّفُ ٱلۡأٓيَٰتِ لَعَلَّهُمۡ يَفۡقَهُونَ
65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱ (አላህ) ከበላያችሁ ወይም ከእግሮቻችሁ በታች ቅጣትን በእናንተ ላይ ሊልክ ወይም የተለያዩ ሕዝቦች ስትሆኑ ሊያደባልቃችሁና ከፊላችሁን የከፊሉን ጭካኔ ሊያቀምስ ቻይ ነው።» በላቸው። ይገነዘቡ ዘንድ አናቅጽን እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَكَذَّبَ بِهِۦ قَوۡمُكَ وَهُوَ ٱلۡحَقُّۚ قُل لَّسۡتُ عَلَيۡكُم بِوَكِيلٖ
66. እርሱ(ቁርኣን) ከአላህ የመጣ እውነት ሲሆን ህዝቦችህ ግን አስተባበሉት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም።» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
لِّكُلِّ نَبَإٖ مُّسۡتَقَرّٞۚ وَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ
67. ለየወሬ ሁሉ የሚደርስበት መፈጸሚያ ጊዜ አለው:: ወደ ፊትም በትክክል ታውቁታላችሁ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِذَا رَأَيۡتَ ٱلَّذِينَ يَخُوضُونَ فِيٓ ءَايَٰتِنَا فَأَعۡرِضۡ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ يَخُوضُواْ فِي حَدِيثٍ غَيۡرِهِۦۚ وَإِمَّا يُنسِيَنَّكَ ٱلشَّيۡطَٰنُ فَلَا تَقۡعُدۡ بَعۡدَ ٱلذِّكۡرَىٰ مَعَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ አናቅጻችንን ለማስተባበል ወደ ክርክር የሚገቡትን ሰዎች በምታይ ጊዜ በሌላ ወሬ እስከሚገቡ ድረስ ተዋቸው:: ሰይጣንም መከልከልህን ቢያስረሳህና አብረሀቸው ሆነህ እንኳን ካስታወስክ በኋላ ከበደለኞች ሕዝቦች ጋር አትቀመጥ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمَا عَلَى ٱلَّذِينَ يَتَّقُونَ مِنۡ حِسَابِهِم مِّن شَيۡءٖ وَلَٰكِن ذِكۡرَىٰ لَعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ
69. እነዚያም በሚጠነቀቁት ህዝቦች ላይ በሂሳባቸው ምንም የለባቸዉም:: ግን ይጠነቀቁ ዘንድ መገሰጽ አለባቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَذَرِ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ دِينَهُمۡ لَعِبٗا وَلَهۡوٗا وَغَرَّتۡهُمُ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَاۚ وَذَكِّرۡ بِهِۦٓ أَن تُبۡسَلَ نَفۡسُۢ بِمَا كَسَبَتۡ لَيۡسَ لَهَا مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلِيّٞ وَلَا شَفِيعٞ وَإِن تَعۡدِلۡ كُلَّ عَدۡلٖ لَّا يُؤۡخَذۡ مِنۡهَآۗ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ أُبۡسِلُواْ بِمَا كَسَبُواْۖ لَهُمۡ شَرَابٞ مِّنۡ حَمِيمٖ وَعَذَابٌ أَلِيمُۢ بِمَا كَانُواْ يَكۡفُرُونَ
70. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም ሃይማኖታቸውን ጨዋታና ቀልድ አድርገው የያዙትንና ቅርቢቱ ሕይወት ያታለለቻቸውን ተዋቸው:: ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ እንዳትጠፋ በእርሱ (በቁርአን) አስታውስ:: ለእርሷ ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ አማላጅ ማንም የላትም:: ፊዳ የተባለን ሁሉ ብትከፍል እንኳን ተቀባይነት የላትም:: እነዚያ በሰሩት ስራ የተጠፉት ናቸው:: በክህደታቸው ምክንያት ከፈላ ውሃ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ أَنَدۡعُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُنَا وَلَا يَضُرُّنَا وَنُرَدُّ عَلَىٰٓ أَعۡقَابِنَا بَعۡدَ إِذۡ هَدَىٰنَا ٱللَّهُ كَٱلَّذِي ٱسۡتَهۡوَتۡهُ ٱلشَّيَٰطِينُ فِي ٱلۡأَرۡضِ حَيۡرَانَ لَهُۥٓ أَصۡحَٰبٞ يَدۡعُونَهُۥٓ إِلَى ٱلۡهُدَى ٱئۡتِنَاۗ قُلۡ إِنَّ هُدَى ٱللَّهِ هُوَ ٱلۡهُدَىٰۖ وَأُمِرۡنَا لِنُسۡلِمَ لِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ ሌላ የማይጠቅምንና የማይጎዳን እንገዛለን? አላህ በቀናው መንገድ ከመራን በኋላ የኋሊት እንመለሳለን? እንደዚያ በምድር ላይ የዋለለ ሲሆን ሰይጣናት አሳስተውት ለእርሱ ‹ወደ እኛ ና› እያሉ ወደ ቅን መንገድ የሚጠሩ ወዳጆች ቢኖሩትም (እንደማይከተላቸው) እንሆናለንን?» በላቸው:: «የአላህ መንገድ ቀጥተኛው መንገድ ነው:: ለዓለማት ጌታ ልንገዛም ታዘዝን።» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَأَنۡ أَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَٱتَّقُوهُۚ وَهُوَ ٱلَّذِيٓ إِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ
72. «ሶላትን በትክክል ስገዱ አላህን ፍሩትም።» (ተብለን ታዘናል በላቸው።) እርሱ ወደ እርሱ የምትሰበሰቡበት አምላክ ነው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهُوَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّۖ وَيَوۡمَ يَقُولُ كُن فَيَكُونُۚ قَوۡلُهُ ٱلۡحَقُّۚ وَلَهُ ٱلۡمُلۡكُ يَوۡمَ يُنفَخُ فِي ٱلصُّورِۚ عَٰلِمُ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِۚ وَهُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡخَبِيرُ
73. እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በትክክል የፈጠረ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁን» የሚልበትንና ወዲያዉም የሚሆንበትን ቀን አስታውስ:: ቃሉም እውነት ነው:: በቀንዱ በሚነፋበት ቀንም ንግስናው የእርሱ ብቻ ነው:: ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ ነው:: እርሱም ጥበበኛውና ውስጠ አዋቂው ነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
۞ وَإِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِيمُ لِأَبِيهِ ءَازَرَ أَتَتَّخِذُ أَصۡنَامًا ءَالِهَةً إِنِّيٓ أَرَىٰكَ وَقَوۡمَكَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ
74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም ለአባቱ ለአዘር፡- «ጣኦትን አማልክት ታደርጋለህን? እኔ አንተንም ወገኖችህንም ግልጽ ጥመት ውስጥ ሆናችሁ አየኋችሁ።» ባለው ጊዜ የሆነውን አስታውስ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَكَذَٰلِكَ نُرِيٓ إِبۡرَٰهِيمَ مَلَكُوتَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلِيَكُونَ مِنَ ٱلۡمُوقِنِينَ
75. ልክ በዚህ አኳኋን ኢብራሂም ጽኑ እምነት ይኖረው ዘንድ የሰማያትንና የምድርን ግዛት አሳየነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَلَمَّا جَنَّ عَلَيۡهِ ٱلَّيۡلُ رَءَا كَوۡكَبٗاۖ قَالَ هَٰذَا رَبِّيۖ فَلَمَّآ أَفَلَ قَالَ لَآ أُحِبُّ ٱلۡأٓفِلِينَ
76. ሌሊቱ በጽልመቱ በሸፈነው ጊዜ አንድ ኮከብ አየ። «ይህ ጌታዬ ነው» አለም:: ኮከቡ በጠለቀ ጊዜም፡- «ጠላቂዎችን አልወድም» አለ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَلَمَّا رَءَا ٱلۡقَمَرَ بَازِغٗا قَالَ هَٰذَا رَبِّيۖ فَلَمَّآ أَفَلَ قَالَ لَئِن لَّمۡ يَهۡدِنِي رَبِّي لَأَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلضَّآلِّينَ
77. ጨረቃውን ደምቆ ባየ ጊዜም፡- «ይህ ጌታዬ ነው።» አለ:: ጨረቃውም በጠለቀ ጊዜ፡- «ጌታዬ ቅኑን ጎዳና ካልመራኝ መንገድ ከተሳሳቱ ሰዎች እሆናለሁ።» አለ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَلَمَّا رَءَا ٱلشَّمۡسَ بَازِغَةٗ قَالَ هَٰذَا رَبِّي هَٰذَآ أَكۡبَرُۖ فَلَمَّآ أَفَلَتۡ قَالَ يَٰقَوۡمِ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تُشۡرِكُونَ
78. ጸሐይዋንም ደምቃ ጮራዋን ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው። ይህ በጣም ትልቅ ነው።» አለ:: በጠለቀችም ጊዜ (አንዲህ) አለ፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ከምታጋሩት ሁሉ የጠራሁ ነኝ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِنِّي وَجَّهۡتُ وَجۡهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ حَنِيفٗاۖ وَمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
79. «እኔ ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበልኩ ስሆን ፊቴን ሰማያትንና ምድርን ወደ ፈጠረው አምላክ አላህ አዙሬያለሁ:: እናም ከአጋሪዎችም አይደለሁም።» (አለ)።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَحَآجَّهُۥ قَوۡمُهُۥۚ قَالَ أَتُحَٰٓجُّوٓنِّي فِي ٱللَّهِ وَقَدۡ هَدَىٰنِۚ وَلَآ أَخَافُ مَا تُشۡرِكُونَ بِهِۦٓ إِلَّآ أَن يَشَآءَ رَبِّي شَيۡـٔٗاۚ وَسِعَ رَبِّي كُلَّ شَيۡءٍ عِلۡمًاۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُونَ
80. ወገኖቹም ተከራከሩት። (እርሱም) አላቸው: «በእርግጥ የመራኝ ስሆን በአላህ ጉዳይ ትከራከሩኛላችሁን? በእርሱም የምታጋሩትን ነገር አልፈራም:: ግን ጌታዬ ቢሻ (ያገኘኛል):: ጌታዬም ሁሉንም ነገር በእውቀቱ ሰፋ። አትገነዘቡምን?
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَكَيۡفَ أَخَافُ مَآ أَشۡرَكۡتُمۡ وَلَا تَخَافُونَ أَنَّكُمۡ أَشۡرَكۡتُم بِٱللَّهِ مَا لَمۡ يُنَزِّلۡ بِهِۦ عَلَيۡكُمۡ سُلۡطَٰنٗاۚ فَأَيُّ ٱلۡفَرِيقَيۡنِ أَحَقُّ بِٱلۡأَمۡنِۖ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
81. «በእናንተ ላይ በእርሱ ማስረጃ ያላወረደበትን እናንተ ማጋራታችሁን የማትፈሩ ስትሆኑ የምታጋሩትን ጣዖት እንዴት እኔ እፈራለሁ?! የምታውቁም ብትሆኑ ከሁለቱ ክፍሎች ደህና ለመሆን ይበልጥ ተገቢው ማንኛው ነው?» አለ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَلَمۡ يَلۡبِسُوٓاْ إِيمَٰنَهُم بِظُلۡمٍ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلۡأَمۡنُ وَهُم مُّهۡتَدُونَ
82. እነዚያ በአላህ ያመኑና እምነታቸውን በእሱ በማጋራት ያልቀላቀሉ ሁሉ እነዚያ ለእነርሱ የተሟላ ደህንነት አለላቸው:: ወደ ቀናው መንገድ የተመሩም እነርሱው ናቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَتِلۡكَ حُجَّتُنَآ ءَاتَيۡنَٰهَآ إِبۡرَٰهِيمَ عَلَىٰ قَوۡمِهِۦۚ نَرۡفَعُ دَرَجَٰتٖ مَّن نَّشَآءُۗ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٞ
83. እነዚህ ማስረጃዎቻችን ናቸው:: ለኢብራሂም በህዝቦቹ ላይ አስረጅ እንዲሆኑ ሰጠነው:: የምንፈልገውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ጥበበኛና አዋቂ ነውና::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَوَهَبۡنَا لَهُۥٓ إِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَۚ كُلًّا هَدَيۡنَاۚ وَنُوحًا هَدَيۡنَا مِن قَبۡلُۖ وَمِن ذُرِّيَّتِهِۦ دَاوُۥدَ وَسُلَيۡمَٰنَ وَأَيُّوبَ وَيُوسُفَ وَمُوسَىٰ وَهَٰرُونَۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
84. ለእርሱም ልጁን ነብዩ ኢስሀቅንና የልጅ ልጁን ነብዩ የዕቆብን ሰጠነው:: ሁሉንም ወደ ቀናው መንገድ መራናቸው:: ኑህንም ከእነርሱ በፊት ወደ ቀናው መንገድ መራነው:: ከዘሮቹም ነብዩ ዳውድንም፤ ነብዩ ሱለይማንንም፤ ነብዩ አዩብንም፤ ነብዩ ዮሱፍንም፤ ነብዩ ሙሳንና፤ ነብዩ ሀሩንንም መራን:: በጎ ሰሪዎችን ሁሉ ልክ እንደዚሁ እንመነዳለን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَزَكَرِيَّا وَيَحۡيَىٰ وَعِيسَىٰ وَإِلۡيَاسَۖ كُلّٞ مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
85. ዘከርያን፤ ያህያን፤ ዒሳን፤ ኢልያስንም ወደ ቀናው መንገድ መራን:: ሁሉም ከመልካሞቹ ናቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِسۡمَٰعِيلَ وَٱلۡيَسَعَ وَيُونُسَ وَلُوطٗاۚ وَكُلّٗا فَضَّلۡنَا عَلَى ٱلۡعَٰلَمِينَ
86. ነብዩ ኢስማኢልንም፤ ነብዩ አል የሰዕንም፤ ነብዩ ዩኑስንም፤ ነብዩ ሉጥንም መራን:: ሁሉንም በዓለማት ላይ አበለጥናቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمِنۡ ءَابَآئِهِمۡ وَذُرِّيَّٰتِهِمۡ وَإِخۡوَٰنِهِمۡۖ وَٱجۡتَبَيۡنَٰهُمۡ وَهَدَيۡنَٰهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
87. ከአባቶቻቸዉም፣ ከዘሮቻቸዉም፣ ከወንድሞቻቸዉም ብዙዎችን መራን:: መረጥናቸዉም:: ወደ ቀጥታኛዉም መንገድ መራናቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
ذَٰلِكَ هُدَى ٱللَّهِ يَهۡدِي بِهِۦ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦۚ وَلَوۡ أَشۡرَكُواْ لَحَبِطَ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
88. ይህ የአላህ መመሪያ ነው:: በእርሱ ከባሮቹ የሚሻውን ወደ ቀናው መንገድ ይመራበታል:: በአላህ ባጋሩም ኖሮ ይሰሩት የነበሩት መልካም ተግባር ሁሉ ከእነርሱ በታበሰባቸው ነበር::
Ibisobanuro by'icyarabu:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحُكۡمَ وَٱلنُّبُوَّةَۚ فَإِن يَكۡفُرۡ بِهَا هَٰٓؤُلَآءِ فَقَدۡ وَكَّلۡنَا بِهَا قَوۡمٗا لَّيۡسُواْ بِهَا بِكَٰفِرِينَ
89. እነዚህ እነዚያ መጽሐፍትንና ጥበብን ነብይነትንም የሰጠናቸው ሰዎች ናቸው:: እነዚህ የመካ ከሓዲያን በእርሷ ቢክዱም በእርሷ የማይክዱ ሕዝቦችን አዘጋጅተንላታል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ هَدَى ٱللَّهُۖ فَبِهُدَىٰهُمُ ٱقۡتَدِهۡۗ قُل لَّآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ أَجۡرًاۖ إِنۡ هُوَ إِلَّا ذِكۡرَىٰ لِلۡعَٰلَمِينَ
90. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ ነብያት እነዚያ አላህ የመራቸው ናቸው:: ስለሆነም ፈለጋቸውን ተከተል:: «በእርሱ (በቁርኣን) ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም:: እርሱ ለዓለማት ግሳጼ ሊሆን የወረደ እንጂ ሌላ አይደለም።» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمَا قَدَرُواْ ٱللَّهَ حَقَّ قَدۡرِهِۦٓ إِذۡ قَالُواْ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَىٰ بَشَرٖ مِّن شَيۡءٖۗ قُلۡ مَنۡ أَنزَلَ ٱلۡكِتَٰبَ ٱلَّذِي جَآءَ بِهِۦ مُوسَىٰ نُورٗا وَهُدٗى لِّلنَّاسِۖ تَجۡعَلُونَهُۥ قَرَاطِيسَ تُبۡدُونَهَا وَتُخۡفُونَ كَثِيرٗاۖ وَعُلِّمۡتُم مَّا لَمۡ تَعۡلَمُوٓاْ أَنتُمۡ وَلَآ ءَابَآؤُكُمۡۖ قُلِ ٱللَّهُۖ ثُمَّ ذَرۡهُمۡ فِي خَوۡضِهِمۡ يَلۡعَبُونَ
91. (ከሓዲያን) «አላህ በሰው ላይ ምንም አላወረደም።» ባሉ ጊዜ አላህን ተገቢውን ክብሩን አላከበሩትም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዲህ በላቸው «ያንን ለሰዎች ብርሃንና ቅን መመሪያ ሆኖ ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትሆኑ ማን አወረደው? (የወደዳችኋትን) ትገልጿታላችሁ ብዙውንም ትደብቃላችሁ፤ እናንተም ሆናችሁ አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ::» (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ አወረደው።» በላቸው:: ከዚያም በውሸታቸው ውስጥ የሚጫወቱ ሲሆኑ ተዋቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهَٰذَا كِتَٰبٌ أَنزَلۡنَٰهُ مُبَارَكٞ مُّصَدِّقُ ٱلَّذِي بَيۡنَ يَدَيۡهِ وَلِتُنذِرَ أُمَّ ٱلۡقُرَىٰ وَمَنۡ حَوۡلَهَاۚ وَٱلَّذِينَ يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ يُؤۡمِنُونَ بِهِۦۖ وَهُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ يُحَافِظُونَ
92. ይህ ያወረድነው ብሩክና ያንንም በፊት የነበረውን (መጽሐፍ) አረጋጋጭ መጽሐፍ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የከተሞችንም እናት (መካን) ኗሪዎችን እና በዙሪያዋ ያሉትንም ሰዎች ልታስጠነቅቅበት አወረድነው:: እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የሚያምኑት ሰዎች እነርሱ በሶላታቸው የሚጠባበቁ ሲሆኑ በእርሱ ያምናሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوۡ قَالَ أُوحِيَ إِلَيَّ وَلَمۡ يُوحَ إِلَيۡهِ شَيۡءٞ وَمَن قَالَ سَأُنزِلُ مِثۡلَ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُۗ وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذِ ٱلظَّٰلِمُونَ فِي غَمَرَٰتِ ٱلۡمَوۡتِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ بَاسِطُوٓاْ أَيۡدِيهِمۡ أَخۡرِجُوٓاْ أَنفُسَكُمُۖ ٱلۡيَوۡمَ تُجۡزَوۡنَ عَذَابَ ٱلۡهُونِ بِمَا كُنتُمۡ تَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ غَيۡرَ ٱلۡحَقِّ وَكُنتُمۡ عَنۡ ءَايَٰتِهِۦ تَسۡتَكۡبِرُونَ
93. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም ወደ እርሱ ምንም ያልተወረደለት ሲሆን «ወደ እኔ ተወረደልኝ።» ካለና «አላህ ያወረደውን አይነት ማውረድም በእርግጥ እችላለሁ።» ካለ ይበልጥ እራሱን በዳይ ማን ነው? በደለኞችን በሞት መከራዎች ውስጥ በሆኑ ጊዜ መላዕክት እጆቻቸውን ዘርጊዎች ሆነው (ለቅጥጥብ) «ነፍሶቻችሁን አውጡ:: ከአላህ ላይ እውነትን ያልሆነን ነገር ትናገሩም የነበራችሁና በአናቅጽም ላይ ትኮሩ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬ የውርደት ቅጣት ትመነዳላችሁ» በሚሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ባየህ ነበር)::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَقَدۡ جِئۡتُمُونَا فُرَٰدَىٰ كَمَا خَلَقۡنَٰكُمۡ أَوَّلَ مَرَّةٖ وَتَرَكۡتُم مَّا خَوَّلۡنَٰكُمۡ وَرَآءَ ظُهُورِكُمۡۖ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمۡ شُفَعَآءَكُمُ ٱلَّذِينَ زَعَمۡتُمۡ أَنَّهُمۡ فِيكُمۡ شُرَكَٰٓؤُاْۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيۡنَكُمۡ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمۡ تَزۡعُمُونَ
94. «በመጀመሪያ ጊዜ ልክ እንደፈጠርናችሁ ሆናችሁ የሰጠናችሁን ሁሉ ከጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትሆኑ ለየብቻችሁ ሆናችሁ በእርግጥ ወደ እኛ መጣችሁ:: እነዚያንም እነርሱ በእናንተ (ጉዳይ) ለአላህ ተጋሪዎቹ ናቸው:: የምትሏቸውን አማላጆቻችሁን ከናንተ ጋር አናይም:: ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ:: ከናንተም ያ ያማልደናል የምትሉት ሁሉ ጠፋ» (ይባላሉ።)
Ibisobanuro by'icyarabu:
۞ إِنَّ ٱللَّهَ فَالِقُ ٱلۡحَبِّ وَٱلنَّوَىٰۖ يُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَمُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتِ مِنَ ٱلۡحَيِّۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُۖ فَأَنَّىٰ تُؤۡفَكُونَ
95. አላህ የፍሬና የዛፍ ቅንጣትን ፈልቃቂ ነው:: ከሙት ነገር ሕያውን ያወጣል:: ከሕያዉም ነገር ሙትን አውጭ ነው:: ይህ አላህ ጌታችሁ ነው:: ታዲያ እንዴት ከእውነት ትሸሻላችሁ (ትርቃላችሁ)?
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَالِقُ ٱلۡإِصۡبَاحِ وَجَعَلَ ٱلَّيۡلَ سَكَنٗا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ حُسۡبَانٗاۚ ذَٰلِكَ تَقۡدِيرُ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡعَلِيمِ
96. ጎሕን ከጽልመት ጨለማ ፈልቃቂ፤ ሌሊቱን ማረፊያ፤ ጸሐይንና ጨረቃን ለጊዜ ስሌት መጠቀሚያ ያደረገ አምላክ ነው:: ይህ የዚያ የአሸናፊውና የሁሉን አዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهُوَ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلنُّجُومَ لِتَهۡتَدُواْ بِهَا فِي ظُلُمَٰتِ ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِۗ قَدۡ فَصَّلۡنَا ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ
97. አላህ ያ በየብስና በባህር ጨለማዎች ውስጥ ራሳችሁን መምራት ትችሉ ዘንድ ከዋክብትን የፈጠረላችሁ አምላክ ነው:: ለሚያውቁ ሁሉ አናቅጽን በሚገባ አብራርተናል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَكُم مِّن نَّفۡسٖ وَٰحِدَةٖ فَمُسۡتَقَرّٞ وَمُسۡتَوۡدَعٞۗ قَدۡ فَصَّلۡنَا ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَفۡقَهُونَ
98. (ሰዎች ሆይ! ) እርሱ (አላህ) ያ ከአንዲት ነፍስ ያስገኛችሁ አምላክ ነው:: በማሕጸን ውስጥ ማረፊያንና ምድር ላይም መኖሪያን አመቻቸላችሁ:: መገንዘብ ለሚችሉ ሁሉ አናቅጽን በሚገባ አብራርተናል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَخۡرَجۡنَا بِهِۦ نَبَاتَ كُلِّ شَيۡءٖ فَأَخۡرَجۡنَا مِنۡهُ خَضِرٗا نُّخۡرِجُ مِنۡهُ حَبّٗا مُّتَرَاكِبٗا وَمِنَ ٱلنَّخۡلِ مِن طَلۡعِهَا قِنۡوَانٞ دَانِيَةٞ وَجَنَّٰتٖ مِّنۡ أَعۡنَابٖ وَٱلزَّيۡتُونَ وَٱلرُّمَّانَ مُشۡتَبِهٗا وَغَيۡرَ مُتَشَٰبِهٍۗ ٱنظُرُوٓاْ إِلَىٰ ثَمَرِهِۦٓ إِذَآ أَثۡمَرَ وَيَنۡعِهِۦٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكُمۡ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
99. እርሱ (አላህ) ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ አምላክ ነው:: በእርሱም የሁሉንም ዓይነት እጽዋት አበቀልን:: የተደራረበን ቅንጣት የምናወጣበትን ለምለም አዝመራም ከርሱ አወጣን:: ከዘንባባ እንቡጥም የተቀራረቡ የሆኑ ዘለላዎችን አወጣን:: የወይን አትክልት ቦታዎችን አዘጋጀን:: ቅጠሎቻቸው የሚመሳሰሉ ፍሬዎቻቸው ግን የማይመሳሰሉ የሆኑትን የዘይቱን(ወይራ) እና የሩማን እጽዋትም ከሰማይ ባወረድነው ዝናብ አበቀልን:: (የሰው ልጆች ሆይ!) ፍሬውን ባፈራና በበሰለ ጊዜ እስቲ ተመልከቱት:: እጅግ አስደናቂ ሆኖ ታገኙታላችሁ:: በእነዚህ ክስተቶች ውስጥ በትክክል በአላህ ለሚያምኑ ሰዎች ሁሉ በርካታ ተአምራት አሉበት::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَجَعَلُواْ لِلَّهِ شُرَكَآءَ ٱلۡجِنَّ وَخَلَقَهُمۡۖ وَخَرَقُواْ لَهُۥ بَنِينَ وَبَنَٰتِۭ بِغَيۡرِ عِلۡمٖۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يَصِفُونَ
100. (ሰዎች) የፈጠራቸው አላህ ሲሆን አጋንንትን በመታዘዝ ለእርሱ ተጋሪዎች አደረጉ:: ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆች አለው በማለት ያለ ዕውቀት በእርሱ ላይ ቀጠፉ:: አላህ ጥራት የተገባውና ከሚሉት ነገር ሁሉ የላቀ ነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
بَدِيعُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُۥ وَلَدٞ وَلَمۡ تَكُن لَّهُۥ صَٰحِبَةٞۖ وَخَلَقَ كُلَّ شَيۡءٖۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ
101. እርሱ ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነው:: ለእርሱም ሚስት የሌለው ሲሆን እንዴት ለእርሱ ልጅ ይኖረዋል? ሁሉንም ነገር ፈጠረ:: እርሱ ሁሉንም ነገር አዋቂ ነውና::
Ibisobanuro by'icyarabu:
ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ خَٰلِقُ كُلِّ شَيۡءٖ فَٱعۡبُدُوهُۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ وَكِيلٞ
102. ይህ ጌታችሁ አላህ ነው:: ከእርሱ በስተቀር አምላክ የለም:: ሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው:: ስለዚህ እርሱን ብቻ ተገዙት:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና::
Ibisobanuro by'icyarabu:
لَّا تُدۡرِكُهُ ٱلۡأَبۡصَٰرُ وَهُوَ يُدۡرِكُ ٱلۡأَبۡصَٰرَۖ وَهُوَ ٱللَّطِيفُ ٱلۡخَبِيرُ
103. አይኖች አያገኙትም:: እርሱ ግን አይኖችን ያያል:: እርሱም ሩህሩህና ውስጠ አዋቂ ነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَدۡ جَآءَكُم بَصَآئِرُ مِن رَّبِّكُمۡۖ فَمَنۡ أَبۡصَرَ فَلِنَفۡسِهِۦۖ وَمَنۡ عَمِيَ فَعَلَيۡهَاۚ وَمَآ أَنَا۠ عَلَيۡكُم بِحَفِيظٖ
104. (ሰዎች ሆይ!) «ከጌታችሁ ዘንድ ብርሃኖች በእርግጥ መጡላችሁ:: እውነቱን የተመለከተ ሰው ጥቅሙ ለነፍሱ ብቻ ነው:: የታወረም ሰው ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው:: እኔ በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም።» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَكَذَٰلِكَ نُصَرِّفُ ٱلۡأٓيَٰتِ وَلِيَقُولُواْ دَرَسۡتَ وَلِنُبَيِّنَهُۥ لِقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ
105. ልክ እንደዚሁ ገምግመው «መጽሐፍ አጥንተሃል» እንዲሉና ለሚያውቁ ህዝቦች ቁርኣንን እንድናብራራ አናቅጽን እንገልፃለን።
Ibisobanuro by'icyarabu:
ٱتَّبِعۡ مَآ أُوحِيَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ وَأَعۡرِضۡ عَنِ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ብቻ ተከተል:: ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላክ የለም:: አጋሪዎችንም ተዋቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَآ أَشۡرَكُواْۗ وَمَا جَعَلۡنَٰكَ عَلَيۡهِمۡ حَفِيظٗاۖ وَمَآ أَنتَ عَلَيۡهِم بِوَكِيلٖ
107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በፈለገ ኖሮ እነርሱ ጣኦትን ባላጋሩ ነበር:: በእነርሱም ላይ ጠባቂ አላደረግንህም:: አንተም በእነርሱ ላይ ኃላፊ አይደለህም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَا تَسُبُّواْ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ فَيَسُبُّواْ ٱللَّهَ عَدۡوَۢا بِغَيۡرِ عِلۡمٖۗ كَذَٰلِكَ زَيَّنَّا لِكُلِّ أُمَّةٍ عَمَلَهُمۡ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّهِم مَّرۡجِعُهُمۡ فَيُنَبِّئُهُم بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
108. (ሙስሊሞች ሆይ!) እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዟቸውን ጣዖታትን አትስደቡ:: እነርሱም ድንበርን በማለፍ ያለ እውቀት አላህን ይሰድባሉና:: ልክ እንደዚሁ ለህዝቦች ሁሉ ስራቸውን ደግ አስመሰልንላቸው:: ከዚያም መመለሻቸው ወደ ጌታቸው ብቻ ነው:: ይሰሩት የነበሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَأَقۡسَمُواْ بِٱللَّهِ جَهۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡ لَئِن جَآءَتۡهُمۡ ءَايَةٞ لَّيُؤۡمِنُنَّ بِهَاۚ قُلۡ إِنَّمَا ٱلۡأٓيَٰتُ عِندَ ٱللَّهِۖ وَمَا يُشۡعِرُكُمۡ أَنَّهَآ إِذَا جَآءَتۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተዐምር ብትመጣላቸው በእርሷ በቁርጥ እንደሚያምኑ ጥብቅ መሀላዎቻቸውን በአላህ ማሉ:: «ተዓምራትም ሁሉ የሚከሰቱት ከአላህ ብቻ ነው። እርሷ በመጣች ጊዜም አለማመናቸውን ወይም ማመናቸውን ምን አሳወቃችሁ?» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَنُقَلِّبُ أَفۡـِٔدَتَهُمۡ وَأَبۡصَٰرَهُمۡ كَمَا لَمۡ يُؤۡمِنُواْ بِهِۦٓ أَوَّلَ مَرَّةٖ وَنَذَرُهُمۡ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ
110. በመጀመሪያም ጊዜ በእርሱ እንዳላመኑ ሁሉ ልቦቻቸውንና አይኖቻቸውን እናገላብጣለን:: በጥመታቸዉም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ እንተዋቸዋለን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
۞ وَلَوۡ أَنَّنَا نَزَّلۡنَآ إِلَيۡهِمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ وَكَلَّمَهُمُ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَحَشَرۡنَا عَلَيۡهِمۡ كُلَّ شَيۡءٖ قُبُلٗا مَّا كَانُواْ لِيُؤۡمِنُوٓاْ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ يَجۡهَلُونَ
111. እኛ ወደ እነርሱ መላዕክትን ባወረድንም ኖሮ ሙታንን ባነጋገሩዋቸውና ነገሩን ሁሉ በቡድን በቡድን በእነርሱ ላይ በሰበሰብንም ኖሮ አላህ ካልሻ በስተቀር የሚያምኑ ባልሆኑ ነበር:: ግን አብዛኞቻቸው ይህንን እውነታ ይስታሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَكَذَٰلِكَ جَعَلۡنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوّٗا شَيَٰطِينَ ٱلۡإِنسِ وَٱلۡجِنِّ يُوحِي بَعۡضُهُمۡ إِلَىٰ بَعۡضٖ زُخۡرُفَ ٱلۡقَوۡلِ غُرُورٗاۚ وَلَوۡ شَآءَ رَبُّكَ مَا فَعَلُوهُۖ فَذَرۡهُمۡ وَمَا يَفۡتَرُونَ
112. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንደዚሁም ለነብያት ሁሉ ከሰውና ከጋኔን የሆኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን:: ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ለማታለል የተዋበን ንግግር ይጥላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በፈለገ ኖሮ ይህን ጸያፍ ተግባር ባልሰሩት ነበር:: ከቅጥፈታቸዉም ጋር ተዋቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلِتَصۡغَىٰٓ إِلَيۡهِ أَفۡـِٔدَةُ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ وَلِيَرۡضَوۡهُ وَلِيَقۡتَرِفُواْ مَا هُم مُّقۡتَرِفُونَ
113. ሊያታልሉ የሚጥሩትና የነዚያም በመጨረሻይቱ ህይወት የማያምኑት ሰዎች ልቦች ወደ እርሱ እንዲያዘነብሉ፤ እንዲወዱትና እነርሱ ይቀጥፉ የነበሩትንም እንዲቀጣጥፉ ነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
أَفَغَيۡرَ ٱللَّهِ أَبۡتَغِي حَكَمٗا وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ إِلَيۡكُمُ ٱلۡكِتَٰبَ مُفَصَّلٗاۚ وَٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ يَعۡلَمُونَ أَنَّهُۥ مُنَزَّلٞ مِّن رَّبِّكَ بِٱلۡحَقِّۖ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُمۡتَرِينَ
114. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ ያ መጽሐፍን የተብራራ ሆኖ ወደ እናንተ ያወረደ ሲሆን ከአላህ ሌላ ዳኛን እፈልጋለሁን? በላቸው:: እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ሰዎች ቁርኣን ከጌታህ ዘንድ በእውነት የተወረደ መሆኑን በትክክል ያውቃሉ:: እናም ከተጠራጣሪዎቹ አትሁን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَتَمَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ صِدۡقٗا وَعَدۡلٗاۚ لَّا مُبَدِّلَ لِكَلِمَٰتِهِۦۚ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
115. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትሆን ተፈጸመች:: ለቃላቱ ምንጊዜም ለዋጭ የለም:: እርሱ ሰሚውና አዋቂው ነው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِن تُطِعۡ أَكۡثَرَ مَن فِي ٱلۡأَرۡضِ يُضِلُّوكَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنۡ هُمۡ إِلَّا يَخۡرُصُونَ
116. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምድር ካሉት መካከል አብዛኞቹን ብትከተል የአላህን መንገድ ያሳስቱሀል:: ጥርጣሬን እንጂ ሌላን አይከተሉምና:: እነርሱም የሚዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ مَن يَضِلُّ عَن سَبِيلِهِۦۖ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُهۡتَدِينَ
117. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ከመንገዱ የሚሳሳቱትን አዋቂ ነው:: እርሱም ተመሪዎቹን እንዲሁ አዋቂ ነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَكُلُواْ مِمَّا ذُكِرَ ٱسۡمُ ٱللَّهِ عَلَيۡهِ إِن كُنتُم بِـَٔايَٰتِهِۦ مُؤۡمِنِينَ
118. (ሰዎች ሆይ!) በአናቅጹም አማኞች እንደሆናችሁ ሲታረድ የአላህ ስም በእርሱ ላይ የተወሳበትን እንሰሳ ብቻ ብሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمَا لَكُمۡ أَلَّا تَأۡكُلُواْ مِمَّا ذُكِرَ ٱسۡمُ ٱللَّهِ عَلَيۡهِ وَقَدۡ فَصَّلَ لَكُم مَّا حَرَّمَ عَلَيۡكُمۡ إِلَّا مَا ٱضۡطُرِرۡتُمۡ إِلَيۡهِۗ وَإِنَّ كَثِيرٗا لَّيُضِلُّونَ بِأَهۡوَآئِهِم بِغَيۡرِ عِلۡمٍۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُعۡتَدِينَ
119. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱን መብላት ካልተገደዳችሁበት በስተቀር በእናንተ እርም የተደረገውን ለእናተ አላህ በእርግጥ የዘረዘረ ሲሆን ከዚያ በእርሱ ላይ የአላህ ስም ከተጠራበት የማትበሉት ምን ምክንያት አላችሁ? ብዙዎቹም ያለ እውቀት በዝንባሌዎቻቸው ብቻ ያሳስታሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ወሰን አላፊዎቹን አዋቂ ነውና::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَذَرُواْ ظَٰهِرَ ٱلۡإِثۡمِ وَبَاطِنَهُۥٓۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكۡسِبُونَ ٱلۡإِثۡمَ سَيُجۡزَوۡنَ بِمَا كَانُواْ يَقۡتَرِفُونَ
120. የኃጢአትን ግልጹንም ድብቁንም ተው:: እነዚያ ኃጢአትን የሚሰሩ ሁሉ ይሰሩት በነበሩበት ነገር በእያንዳንዱ በእርግጥ ይመነዳሉ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَا تَأۡكُلُواْ مِمَّا لَمۡ يُذۡكَرِ ٱسۡمُ ٱللَّهِ عَلَيۡهِ وَإِنَّهُۥ لَفِسۡقٞۗ وَإِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ لَيُوحُونَ إِلَىٰٓ أَوۡلِيَآئِهِمۡ لِيُجَٰدِلُوكُمۡۖ وَإِنۡ أَطَعۡتُمُوهُمۡ إِنَّكُمۡ لَمُشۡرِكُونَ
121. (ሙስሊሞች ሆይ!) በእርሱ ላይ የአላህ ስም ያልተወሳበትን አትብሉ:: እርሱም በእርግጥ አመጽ ነው:: ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው በክትን በመብላት ይከራከሯችሁ ዘንድ ያሾከሹካሉ:: ታዲያ ብትታዘዟቸው በእርግጥ አጋሪዎች ናችሁ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
أَوَمَن كَانَ مَيۡتٗا فَأَحۡيَيۡنَٰهُ وَجَعَلۡنَا لَهُۥ نُورٗا يَمۡشِي بِهِۦ فِي ٱلنَّاسِ كَمَن مَّثَلُهُۥ فِي ٱلظُّلُمَٰتِ لَيۡسَ بِخَارِجٖ مِّنۡهَاۚ كَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِلۡكَٰفِرِينَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
122. ሙት የነበረና ከዚያም ህያው አድርገነው ለርሱም በሰዎች መካከል የሚሄድበትን ብርሃን ያደረግንለት በጨለማዎች ውስጥ ምንጊዜም የማይወጣ ሆኖ እንዳለው ብጤ ነውን? ልክ እንደዚሁ ለከሓዲያን ሁሉ ይሰሩት የነበሩት ነገር ተዋበላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَكَذَٰلِكَ جَعَلۡنَا فِي كُلِّ قَرۡيَةٍ أَكَٰبِرَ مُجۡرِمِيهَا لِيَمۡكُرُواْ فِيهَاۖ وَمَا يَمۡكُرُونَ إِلَّا بِأَنفُسِهِمۡ وَمَا يَشۡعُرُونَ
123. ልክ እንደዚሁ በየከተማይቱ ውስጥ ታላላቅ ወንጀለኞቿ በውስጧ እንዲያሴሩ አደረግን። በነፍሶቻቸው ላይ እንጂ በሌላ ላይ አያሴሩም:: ግን ይህን እውነታ አያውቁም።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِذَا جَآءَتۡهُمۡ ءَايَةٞ قَالُواْ لَن نُّؤۡمِنَ حَتَّىٰ نُؤۡتَىٰ مِثۡلَ مَآ أُوتِيَ رُسُلُ ٱللَّهِۘ ٱللَّهُ أَعۡلَمُ حَيۡثُ يَجۡعَلُ رِسَالَتَهُۥۗ سَيُصِيبُ ٱلَّذِينَ أَجۡرَمُواْ صَغَارٌ عِندَ ٱللَّهِ وَعَذَابٞ شَدِيدُۢ بِمَا كَانُواْ يَمۡكُرُونَ
124. ተዓምር በመጣላቸውም ጊዜ «የአላህ መልዕክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ:: አላህ መልዕክቱን የሚያደርግበትን ስፍራ አዋቂ ነው:: እነዚያን በአላህ ያመጹ ሰዎች ይዶልቱት በነበሩት ነገር አላህ ዘንድ ውርደትና ብርቱ ቅጣት ያገኛቸዋል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَمَن يُرِدِ ٱللَّهُ أَن يَهۡدِيَهُۥ يَشۡرَحۡ صَدۡرَهُۥ لِلۡإِسۡلَٰمِۖ وَمَن يُرِدۡ أَن يُضِلَّهُۥ يَجۡعَلۡ صَدۡرَهُۥ ضَيِّقًا حَرَجٗا كَأَنَّمَا يَصَّعَّدُ فِي ٱلسَّمَآءِۚ كَذَٰلِكَ يَجۡعَلُ ٱللَّهُ ٱلرِّجۡسَ عَلَى ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ
125. አላህ ሊመራው የሚሻውን ሁሉ ልቡን ለኢስላም ይከፍትለታል:: ሊያጠመው የሚሻውን ደግሞ ልቡን ጠባብና ተቸጋሪ ወደ ሰማይ ለመውጣት እንደሚታገል ያደርገዋል:: ልክ እንደዚሁ አላህ በእነዚያ በማያምኑት ሰዎች ላይ ርክሰትን ያደርጋል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهَٰذَا صِرَٰطُ رَبِّكَ مُسۡتَقِيمٗاۗ قَدۡ فَصَّلۡنَا ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَذَّكَّرُونَ
126. ይህ ያለህበት መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን የጌታህ መንገድ ነው:: ለሚያስታውሱ ህዝቦች አናቅጽን እርግጥ ዘርዝረናል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
۞ لَهُمۡ دَارُ ٱلسَّلَٰمِ عِندَ رَبِّهِمۡۖ وَهُوَ وَلِيُّهُم بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
127. ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሰላም ሀገር አለላቸው። እርሱ ይሰሩት በነበሩት ምክንያትም ረዳታቸው ነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَيَوۡمَ يَحۡشُرُهُمۡ جَمِيعٗا يَٰمَعۡشَرَ ٱلۡجِنِّ قَدِ ٱسۡتَكۡثَرۡتُم مِّنَ ٱلۡإِنسِۖ وَقَالَ أَوۡلِيَآؤُهُم مِّنَ ٱلۡإِنسِ رَبَّنَا ٱسۡتَمۡتَعَ بَعۡضُنَا بِبَعۡضٖ وَبَلَغۡنَآ أَجَلَنَا ٱلَّذِيٓ أَجَّلۡتَ لَنَاۚ قَالَ ٱلنَّارُ مَثۡوَىٰكُمۡ خَٰلِدِينَ فِيهَآ إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۚ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٞ
128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሁሉንም በአንድ ቦታ በሚሰበስባቸው ቀን የሚሆነውን አስታውስ:: «የአጋንንት ቡድኖች ሆይ! ከሰዎች ቡድንን በማጥመም በእርግጥ አበዛችሁ።» ይባላሉ:: ከሰዎችም መካከል የሆኑት ወዳጆቻቸው «ጌታችን ሆይ! ከፊላችን በከፊሉ ተጠቀመ:: ያንን ለእኛ የወሰንክልንን ጊዜያችንን ደረስን።» ይላሉ:: «እሳቲቱ አላህ የሻው ጊዜ ሲቀር በውስጧ ዘወታሪዎች ስትሆኑ መኖሪያችሁ ናት።» ይላቸዋል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ጥበበኛና አዋቂ ነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَكَذَٰلِكَ نُوَلِّي بَعۡضَ ٱلظَّٰلِمِينَ بَعۡضَۢا بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ
129. ልክ እንደዚሁ አንዳንድ በደለኞችን ይሰሩት በነበሩት ጥፋት ምክንያት በከፊሎች ላይ እንሾማለን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
يَٰمَعۡشَرَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِ أَلَمۡ يَأۡتِكُمۡ رُسُلٞ مِّنكُمۡ يَقُصُّونَ عَلَيۡكُمۡ ءَايَٰتِي وَيُنذِرُونَكُمۡ لِقَآءَ يَوۡمِكُمۡ هَٰذَاۚ قَالُواْ شَهِدۡنَا عَلَىٰٓ أَنفُسِنَاۖ وَغَرَّتۡهُمُ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا وَشَهِدُواْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ أَنَّهُمۡ كَانُواْ كَٰفِرِينَ
130. «የአጋንትና የሰዎች ቡድኖች ሆይ! አንቀፆቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን ቅጣት ማግኘትን የሚያስፈራሯችሁ ከናንተው የሆኑ መልዕክተኞች አልመጡላችሁም ነበርን?» ይባላሉ:: «በነፍሶቻችን ላይ መሰከርን።» ይላሉ። የዱንያ ህይወት አታለለቻቸው። በነፍሶቻቸው ላይ እነርሱ ከሓዲያን የነበሩ መሆናቸውንም በራሳቸው መሰከሩ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
ذَٰلِكَ أَن لَّمۡ يَكُن رَّبُّكَ مُهۡلِكَ ٱلۡقُرَىٰ بِظُلۡمٖ وَأَهۡلُهَا غَٰفِلُونَ
131. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ የሆነው ጌታህ ከተሞችን ባለቤቶችዋ (ማስጠንቀቂያ ያልመጣላቸው) ዘንጊዎች ሆነው ሳሉ በበደል ምክንያት አጥፊ ባለመሆኑ ነው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلِكُلّٖ دَرَجَٰتٞ مِّمَّا عَمِلُواْۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَٰفِلٍ عَمَّا يَعۡمَلُونَ
132. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለሁሉም ከሰሩት (አንፃር) የተበላለጡ ደረጃዎች አሏቸው:: ጌታህም ከሚሰሩት ስራ ዝንጉ አይደለም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَرَبُّكَ ٱلۡغَنِيُّ ذُو ٱلرَّحۡمَةِۚ إِن يَشَأۡ يُذۡهِبۡكُمۡ وَيَسۡتَخۡلِفۡ مِنۢ بَعۡدِكُم مَّا يَشَآءُ كَمَآ أَنشَأَكُم مِّن ذُرِّيَّةِ قَوۡمٍ ءَاخَرِينَ
133. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በራሱ ተብቃቂ የእዝነት ባለቤት ነው:: ቢሻ ከምድረ ገጽ ያጠፋችኋል:: ከሌሎች ህዝቦችም ዘሮች እንዳስገኛችሁ ሁሉ ከበኋላችሁም የሚሻውን ሰው ይተካል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِنَّ مَا تُوعَدُونَ لَأٓتٖۖ وَمَآ أَنتُم بِمُعۡجِزِينَ
134. (ሰዎች ሆይ!) የምትቀጠሩት ሁሉ በእርግጥ መጪ ነው:: እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ يَٰقَوۡمِ ٱعۡمَلُواْ عَلَىٰ مَكَانَتِكُمۡ إِنِّي عَامِلٞۖ فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ مَن تَكُونُ لَهُۥ عَٰقِبَةُ ٱلدَّارِۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ
135. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ህዝቦቼ ሆይ! በችሎታችሁ ላይ ስሩ እኔ በችሎታዬ ላይ ሰሪ ነኝና:: ምስጉኒቱ ሀገር ገነት ለእርሱ የምትሆንለት ሰው ማን እንደሆነ ወደፊት ታውቃላችሁ:: እነሆ በደለኞች ሁሉ ምንጊዜም አይድኑም።» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَجَعَلُواْ لِلَّهِ مِمَّا ذَرَأَ مِنَ ٱلۡحَرۡثِ وَٱلۡأَنۡعَٰمِ نَصِيبٗا فَقَالُواْ هَٰذَا لِلَّهِ بِزَعۡمِهِمۡ وَهَٰذَا لِشُرَكَآئِنَاۖ فَمَا كَانَ لِشُرَكَآئِهِمۡ فَلَا يَصِلُ إِلَى ٱللَّهِۖ وَمَا كَانَ لِلَّهِ فَهُوَ يَصِلُ إِلَىٰ شُرَكَآئِهِمۡۗ سَآءَ مَا يَحۡكُمُونَ
136. አጋሪዎች ለአላህ ከፈጠራቸው ፍጡራን ከአዝመራውም ከግመል፣ ከከብት፣ ከፍየል፤ ከበጉም ድርሻን አደረጉለት:: በሀሳባቸዉም «ይህ የአላህ ነው፤ ይህ ደግሞ ለተጋሪዎቻችን ነው።» አሉ። ለተጋሪዎቻቸው የሆነው ነገር ወደ አላህ ምንጊዜም አይደርስም:: ለአላህ የሆነው ነገር ግን ወደ ተጋሪዎቹ ይደርሳል አሉ። የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ!
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَكَذَٰلِكَ زَيَّنَ لِكَثِيرٖ مِّنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ قَتۡلَ أَوۡلَٰدِهِمۡ شُرَكَآؤُهُمۡ لِيُرۡدُوهُمۡ وَلِيَلۡبِسُواْ عَلَيۡهِمۡ دِينَهُمۡۖ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَا فَعَلُوهُۖ فَذَرۡهُمۡ وَمَا يَفۡتَرُونَ
137. ልክ እንደዚሁ ከአጋሪዎች ለብዙዎቹ ሊያጠፏቸውና ሀይማኖታቸውንም በነሱ ላይ ሊያቀላቅሉባቸው ዘንድ ልጆቻቸውን መግደልን ተጋሪዎቻቸው ጣኦታቱ አሳመሩላቸው:: አላህም በሻ ኖሮ (ይህን ጸያፍ ተግባር) ባልሰሩት ነበር:: እናም ከቅጥፈታቸው ጋር ተዋቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَقَالُواْ هَٰذِهِۦٓ أَنۡعَٰمٞ وَحَرۡثٌ حِجۡرٞ لَّا يَطۡعَمُهَآ إِلَّا مَن نَّشَآءُ بِزَعۡمِهِمۡ وَأَنۡعَٰمٌ حُرِّمَتۡ ظُهُورُهَا وَأَنۡعَٰمٞ لَّا يَذۡكُرُونَ ٱسۡمَ ٱللَّهِ عَلَيۡهَا ٱفۡتِرَآءً عَلَيۡهِۚ سَيَجۡزِيهِم بِمَا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
138. በሀሳባቸውም «እነዚህ እርም የሆኑ ለማዳ እንሰሳና አዝመራ ናቸው:: የምንሻለት ሰው እንጂ ሌላ ማንም አይበላቸዉም:: እነዚህ ደግሞ ጀርባዎቻቸው እርም የተደረገ ለማዳ እንሰሳ ናቸው:: አይጫኑም:: እነዚህ ሲታረዱ በእነርሱ ላይ የአላህን ስም የማይጠሩባቸዉም እንሳሳት ናቸው።» አሉ:: በእርሱ ላይ ለመቅጠፍ ነገሩን ወደ አላህ አስጠጉ:: ይቀጥፉት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣቸዋል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَقَالُواْ مَا فِي بُطُونِ هَٰذِهِ ٱلۡأَنۡعَٰمِ خَالِصَةٞ لِّذُكُورِنَا وَمُحَرَّمٌ عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِنَاۖ وَإِن يَكُن مَّيۡتَةٗ فَهُمۡ فِيهِ شُرَكَآءُۚ سَيَجۡزِيهِمۡ وَصۡفَهُمۡۚ إِنَّهُۥ حَكِيمٌ عَلِيمٞ
139. «በእነዚህ እንስሳት ሆዶች ውስጥ ያለው ጽንሱ ሁሉ ለወንዶቻችን ብቻ በተለይ የተፈቀደ ነው:: በሚስቶቻችን ላይ ግን እርም የተደረገ ነው:: ሙት ሆኖ ቢወለድ ግን ወንዶቹም ሆነ ሴቶች በእርሱ ላይ ተጋሪዎች ናቸው።» አሉ:: ይህን በመቅጠፋቸው አላህ በእርግጥ ይቀጣቸዋል:: እርሱ ጥበበኛና አዋቂ ነውና::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَدۡ خَسِرَ ٱلَّذِينَ قَتَلُوٓاْ أَوۡلَٰدَهُمۡ سَفَهَۢا بِغَيۡرِ عِلۡمٖ وَحَرَّمُواْ مَا رَزَقَهُمُ ٱللَّهُ ٱفۡتِرَآءً عَلَى ٱللَّهِۚ قَدۡ ضَلُّواْ وَمَا كَانُواْ مُهۡتَدِينَ
140. እነዚያ ያለ እውቀት በሞኝነት ልጆቻቸውን የገደሉና አላህም የሰጣቸውን ሲሳይ በአላህ ላይ በመቅጠፍ በራሳቸው ላይ እርም ያደረጉ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ ከሰሩ:: ተሳሳቱም:: ወደ ትክክለኛው መንገድም የተመሩ አልነበሩም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
۞ وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَ جَنَّٰتٖ مَّعۡرُوشَٰتٖ وَغَيۡرَ مَعۡرُوشَٰتٖ وَٱلنَّخۡلَ وَٱلزَّرۡعَ مُخۡتَلِفًا أُكُلُهُۥ وَٱلزَّيۡتُونَ وَٱلرُّمَّانَ مُتَشَٰبِهٗا وَغَيۡرَ مُتَشَٰبِهٖۚ كُلُواْ مِن ثَمَرِهِۦٓ إِذَآ أَثۡمَرَ وَءَاتُواْ حَقَّهُۥ يَوۡمَ حَصَادِهِۦۖ وَلَا تُسۡرِفُوٓاْۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُسۡرِفِينَ
141. አላህ ያ (በሀረጉ) ዳስ የሚያደርግላቸውንና ዳስ የማያደርግላቸውን አትክልቶች የፈጠረ ነው:: የተምርን ዛፍ፣ አዝመራን፣ ፍሬዎቹ የተለያዩ ሲሆኑ ወይራንና ሩማንንም ቅጠላቸው ተመሳሳይና ጣዕማቸው የማይመሳሰል ሲሆኑ ፈጠረ:: (ሰዎች ሆይ!) ባፈራ ጊዜም ከፍሬው ብሉ:: ባጨዳዉም ቀን ተገቢውን (ዘካ) ለተገቢው ስጡለት:: አታባክኑም:: አላህ አባካኞችን አይወድምና::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمِنَ ٱلۡأَنۡعَٰمِ حَمُولَةٗ وَفَرۡشٗاۚ كُلُواْ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ وَلَا تَتَّبِعُواْ خُطُوَٰتِ ٱلشَّيۡطَٰنِۚ إِنَّهُۥ لَكُمۡ عَدُوّٞ مُّبِينٞ
142. ከለማዳ እንሰሳዎችም የሚጫኑትንም የማይጫኑትንም ፈጠረ:: (ሰዎች ሆይ!) አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ብሉ:: የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ:: እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና::
Ibisobanuro by'icyarabu:
ثَمَٰنِيَةَ أَزۡوَٰجٖۖ مِّنَ ٱلضَّأۡنِ ٱثۡنَيۡنِ وَمِنَ ٱلۡمَعۡزِ ٱثۡنَيۡنِۗ قُلۡ ءَآلذَّكَرَيۡنِ حَرَّمَ أَمِ ٱلۡأُنثَيَيۡنِ أَمَّا ٱشۡتَمَلَتۡ عَلَيۡهِ أَرۡحَامُ ٱلۡأُنثَيَيۡنِۖ نَبِّـُٔونِي بِعِلۡمٍ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
143. ስምንትን ዓይነቶች፤ ከበግ ሁለትን (ወንድና ሴትን) ከፍየልም ሁለትን ፈጠረ:: «ከሁለቱም ክፍሎች አላህ ወንዶችን ብቻ እርም አደረገን? ወይንስ ሴቶችን ብቻ? ወይስ በእርሱ ላይ የሁለቱ ሴቶች ማህጸኖች ያጠቃለሉትን እርም አደረገ? እውነተኞች እንደሆናችሁ በእውቀት (በአስረጂ) ንገሩኝ» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمِنَ ٱلۡإِبِلِ ٱثۡنَيۡنِ وَمِنَ ٱلۡبَقَرِ ٱثۡنَيۡنِۗ قُلۡ ءَآلذَّكَرَيۡنِ حَرَّمَ أَمِ ٱلۡأُنثَيَيۡنِ أَمَّا ٱشۡتَمَلَتۡ عَلَيۡهِ أَرۡحَامُ ٱلۡأُنثَيَيۡنِۖ أَمۡ كُنتُمۡ شُهَدَآءَ إِذۡ وَصَّىٰكُمُ ٱللَّهُ بِهَٰذَاۚ فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبٗا لِّيُضِلَّ ٱلنَّاسَ بِغَيۡرِ عِلۡمٍۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
144. ከግመል ሁለትን፤ ከከብት ሁለትን ፈጠረ። «አላህ ከሁለቱ ወንዶችን ብቻ እርም አደረገን? ወይንስ ሴቶችን ብቻ? ወይስ የሁለቱ ሴቶች ማህጸኖች ያጠቃለሉትን? በእውነቱ አላህ በዚህ ነገር ባዘዛችሁ ጊዜ በቦታው ነበራችሁን? ሰዎችን ያለ እውቀት ሊያጠም በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? አላህ በደለኞችን ህዝቦች ቅኑን መንገድ አይመራም::» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُل لَّآ أَجِدُ فِي مَآ أُوحِيَ إِلَيَّ مُحَرَّمًا عَلَىٰ طَاعِمٖ يَطۡعَمُهُۥٓ إِلَّآ أَن يَكُونَ مَيۡتَةً أَوۡ دَمٗا مَّسۡفُوحًا أَوۡ لَحۡمَ خِنزِيرٖ فَإِنَّهُۥ رِجۡسٌ أَوۡ فِسۡقًا أُهِلَّ لِغَيۡرِ ٱللَّهِ بِهِۦۚ فَمَنِ ٱضۡطُرَّ غَيۡرَ بَاغٖ وَلَا عَادٖ فَإِنَّ رَبَّكَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
145. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ወደ እኔ በተወረደው ቁርኣን ውስጥ በክት ወይም የፈሰሰ ደም፤ ወይም የአሳማ ስጋ እርሱ እርኩስ ነውና፤ ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልሆነ በስተቀር ተመጋቢ ላይ እርም የሆነ ነገር አላገኝም። አመጸኛና ወሰን ያለፈ ሳይሆን የተገደደ ሰው ከተወሱት ነገሮች ነፍስን የማዳን ያህል ቢበላ ኃጢአት የለበትም:: ጌታህ መሀሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَعَلَى ٱلَّذِينَ هَادُواْ حَرَّمۡنَا كُلَّ ذِي ظُفُرٖۖ وَمِنَ ٱلۡبَقَرِ وَٱلۡغَنَمِ حَرَّمۡنَا عَلَيۡهِمۡ شُحُومَهُمَآ إِلَّا مَا حَمَلَتۡ ظُهُورُهُمَآ أَوِ ٱلۡحَوَايَآ أَوۡ مَا ٱخۡتَلَطَ بِعَظۡمٖۚ ذَٰلِكَ جَزَيۡنَٰهُم بِبَغۡيِهِمۡۖ وَإِنَّا لَصَٰدِقُونَ
146. በአይሁዳውያን ላይ የጥፍር ባለቤት እንስሳትን ሁሉ እርም አደረግንባቸው:: ከከብት፤ ከፍየልና ከበግ ሞራዎቻቸውን፤ ጀርባዎቻቸው ወይም አንጀቶቻቸው የተሸከሙት ወይም በአጥንት የተቀላቀሉ ስብ ሲቀር በእነርሱ ላይ እርም አደረግን:: በአመፃቸው ምክንያት ይህን በማድረግ ቀጣናቸው:: እኛም እውነተኞች ነን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَإِن كَذَّبُوكَ فَقُل رَّبُّكُمۡ ذُو رَحۡمَةٖ وَٰسِعَةٖ وَلَا يُرَدُّ بَأۡسُهُۥ عَنِ ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
147. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉልህ፡- «ጌታችሁ የሰፊ ችሮታ ባለቤት ነው:: ብርቱ ቅጣቱም ከአመጸኞች ህዝቦች ላይ አይመለስም።» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
سَيَقُولُ ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ لَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَآ أَشۡرَكۡنَا وَلَآ ءَابَآؤُنَا وَلَا حَرَّمۡنَا مِن شَيۡءٖۚ كَذَٰلِكَ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ حَتَّىٰ ذَاقُواْ بَأۡسَنَاۗ قُلۡ هَلۡ عِندَكُم مِّنۡ عِلۡمٖ فَتُخۡرِجُوهُ لَنَآۖ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا تَخۡرُصُونَ
148. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ በአላህ ያጋሩት ሰዎች አላህ በሻ ኖሮ እኛም ሆነ አባቶቻችን በአላህ ባላጋራንና አንዳችንም ነገር እርም ባላደረግን ነበር።» ይላሉ:: ልክ እነዚህ እንደ አስተባበሉህ ሁሉ እነዚያ ከበፊታቸው የነበሩ ሕዝቦችም ብርቱ ቅጣታችንን እስከ ቀመሱ ድረስ አስተባበሉ:: «ለእኛ ታስተምሩን ዘንድ ማጋራታችሁን ለመውደዱ እናንተ ዘንድ እውቀት አለን? ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አትከተሉም:: እናንተ ዋሾዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ فَلِلَّهِ ٱلۡحُجَّةُ ٱلۡبَٰلِغَةُۖ فَلَوۡ شَآءَ لَهَدَىٰكُمۡ أَجۡمَعِينَ
149. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የተሟላው ማስረጃ የአላህ ማስረጃ ብቻ ነው:: በፈለገ ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር።» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ هَلُمَّ شُهَدَآءَكُمُ ٱلَّذِينَ يَشۡهَدُونَ أَنَّ ٱللَّهَ حَرَّمَ هَٰذَاۖ فَإِن شَهِدُواْ فَلَا تَشۡهَدۡ مَعَهُمۡۚ وَلَا تَتَّبِعۡ أَهۡوَآءَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ وَهُم بِرَبِّهِمۡ يَعۡدِلُونَ
150. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ አላህ ይህንን እርም ማድረጉን የሚመሰክሩትን ምስክሮቻችሁን እስቲ አምጡ።» በላቸው:: ቢመሰክሩም ከእነርሱ ጋር አትመስክር:: የእነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን፤ የእነዚያንም በጌታቸው ሌላን የሚያስተካክሉ ሲሆኑ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑትን ሰዎች ዝንባሌዎች አትከተል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
۞ قُلۡ تَعَالَوۡاْ أَتۡلُ مَا حَرَّمَ رَبُّكُمۡ عَلَيۡكُمۡۖ أَلَّا تُشۡرِكُواْ بِهِۦ شَيۡـٔٗاۖ وَبِٱلۡوَٰلِدَيۡنِ إِحۡسَٰنٗاۖ وَلَا تَقۡتُلُوٓاْ أَوۡلَٰدَكُم مِّنۡ إِمۡلَٰقٖ نَّحۡنُ نَرۡزُقُكُمۡ وَإِيَّاهُمۡۖ وَلَا تَقۡرَبُواْ ٱلۡفَوَٰحِشَ مَا ظَهَرَ مِنۡهَا وَمَا بَطَنَۖ وَلَا تَقۡتُلُواْ ٱلنَّفۡسَ ٱلَّتِي حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلۡحَقِّۚ ذَٰلِكُمۡ وَصَّىٰكُم بِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ
151. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸውም: «ኑ ጌታችሁ በእናተ ላይ እርም ያደረገውን ነገርና (በእርሱም ያዘዛችሁን) ላንብብላችሁ። እርሱም በአላህ ምንንም ነገር አታጋሩ:: ለወላጆቻችሁም በጎ ስራን ስሩ:: ልጆቻችሁንም ድህነትን ፈርታችሁ አትግደሉ:: እኛ እናንተንም ሆነ እነርሱን እንመግባችኋለንና:: ወደ ግልፅም ይሁን ድብቅ መጥፎ ስራ አትቅረቡ:: ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሀቅ ቢሆን እንጂ አትግደሉ:: ይሀችሁ! ታውቁ ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَا تَقۡرَبُواْ مَالَ ٱلۡيَتِيمِ إِلَّا بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ حَتَّىٰ يَبۡلُغَ أَشُدَّهُۥۚ وَأَوۡفُواْ ٱلۡكَيۡلَ وَٱلۡمِيزَانَ بِٱلۡقِسۡطِۖ لَا نُكَلِّفُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۖ وَإِذَا قُلۡتُمۡ فَٱعۡدِلُواْ وَلَوۡ كَانَ ذَا قُرۡبَىٰۖ وَبِعَهۡدِ ٱللَّهِ أَوۡفُواْۚ ذَٰلِكُمۡ وَصَّىٰكُم بِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ
152. «የየቲምንም ገንዘብ አካለ መጠን እስኪድረስ ድረስ በመልካም ሁኔታ እንጂ አትቅረቡ:: ስፍርንና ሚዛንንም በትክከል ሙሉ:: ማንኛዋም ነፍስ የችሎታዋን ያህል እንጂ አናስገድድም:: በተናገራችሁ ጊዜ በዘመዶቻችሁ ላይ ቢሆንም እንኳ እውነትን በመናገር አስተካክሉ:: በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ:: ይሀችሁ ትገሰጹ ዘንድ አላህ በእርሱ አዘዛችሁ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَأَنَّ هَٰذَا صِرَٰطِي مُسۡتَقِيمٗا فَٱتَّبِعُوهُۖ وَلَا تَتَّبِعُواْ ٱلسُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمۡ عَن سَبِيلِهِۦۚ ذَٰلِكُمۡ وَصَّىٰكُم بِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ
153. «ይህ ቀጥተኛው መንገዴ ነው:: እናም እርሱን ብቻ ተከተሉ:: የተለያዩ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ:: ከቀጥተኛው የርሱ መንገድ እናንተን ይለያይዋችኋልና:: ይሀችሁ ትጠነቀቁ ዘንድ አላህ በእርሱ አዘዛችሁ።»
Ibisobanuro by'icyarabu:
ثُمَّ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ تَمَامًا عَلَى ٱلَّذِيٓ أَحۡسَنَ وَتَفۡصِيلٗا لِّكُلِّ شَيۡءٖ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٗ لَّعَلَّهُم بِلِقَآءِ رَبِّهِمۡ يُؤۡمِنُونَ
154. ከዚያ ለሙሳ መፅሀፍ ሰጠነው መልካም በሰራው ላይ ጸጋችንን ለማሟላት፤ ነገርንም ሁሉ ለመዘርዘር፤ ለህዝቦቹም መሪና እዝነት ይሆን ዘንድ:: እነርሱ ከጌታቸው በመገናኘት ጉዳይ ሊያምኑ ይከጀላልና::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهَٰذَا كِتَٰبٌ أَنزَلۡنَٰهُ مُبَارَكٞ فَٱتَّبِعُوهُ وَٱتَّقُواْ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ
155. ይህ ያወረድነው የሆነ የተባረከ መጽሐፍ ነው:: እናም ተከተሉት፤ ይታዘንላችሁም ዘንድ ከክህደት ተጠንቀቁ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
أَن تَقُولُوٓاْ إِنَّمَآ أُنزِلَ ٱلۡكِتَٰبُ عَلَىٰ طَآئِفَتَيۡنِ مِن قَبۡلِنَا وَإِن كُنَّا عَن دِرَاسَتِهِمۡ لَغَٰفِلِينَ
156. (ያወረድነውም) «መጽሐፍ የተወረደው ከፊታችን በነበሩ ሁለቱ ህዝቦች ላይ ብቻ ነው:: እኛም ከንባባቸው ዘንጊዎች ነበርን» እንዳትሉም ነው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
أَوۡ تَقُولُواْ لَوۡ أَنَّآ أُنزِلَ عَلَيۡنَا ٱلۡكِتَٰبُ لَكُنَّآ أَهۡدَىٰ مِنۡهُمۡۚ فَقَدۡ جَآءَكُم بَيِّنَةٞ مِّن رَّبِّكُمۡ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٞۚ فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَصَدَفَ عَنۡهَاۗ سَنَجۡزِي ٱلَّذِينَ يَصۡدِفُونَ عَنۡ ءَايَٰتِنَا سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ بِمَا كَانُواْ يَصۡدِفُونَ
157. ወይም «እኛ መጽሐፍ በእኛ ላይ በተወረደ ኖሮ ከእነርሱ ይበልጥ የተመራን እንሆን ነበር።» እንዳትሉም ነው:: ስለዚህም ከጌታችሁ ግልጽ ማስረጃ፤ መመሪያ እና እዝነት በእርግጥ መጣላችሁ:: በአላህ አናቅጽ ካስተባበለና ከእርሱም ከዞረ ሰው ይበልጥ ራሱን በዳይ ማን ነው? እነዚያን አናቅጽን የሚተውትን ይተውት በነበሩት አንቀጽ ምክንያት ብርቱ ቅጣት በእርግጥ እንቀጣቸዋለን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّآ أَن تَأۡتِيَهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ أَوۡ يَأۡتِيَ رَبُّكَ أَوۡ يَأۡتِيَ بَعۡضُ ءَايَٰتِ رَبِّكَۗ يَوۡمَ يَأۡتِي بَعۡضُ ءَايَٰتِ رَبِّكَ لَا يَنفَعُ نَفۡسًا إِيمَٰنُهَا لَمۡ تَكُنۡ ءَامَنَتۡ مِن قَبۡلُ أَوۡ كَسَبَتۡ فِيٓ إِيمَٰنِهَا خَيۡرٗاۗ قُلِ ٱنتَظِرُوٓاْ إِنَّا مُنتَظِرُونَ
158. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን መላዕክት ልትመጣላቸው ወይንም ጌታህ ሊመጣ ወይም ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ ሊመጣ እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ የሚመጣበት ቀን ግን ከዚያ በፊት አማኝ ያልነበረች ነፍስ ሁሉ ወይም አምና በእምነቷ በጎ ያልሰራች ነፍስ ሁሉ እምነቷ (ጸጸቷ) አይጠቅማትም:: «ያን ቀን እናንተም ተጠባበቁ እኛም ተጠባባቂዎች ነን።» በላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِنَّ ٱلَّذِينَ فَرَّقُواْ دِينَهُمۡ وَكَانُواْ شِيَعٗا لَّسۡتَ مِنۡهُمۡ فِي شَيۡءٍۚ إِنَّمَآ أَمۡرُهُمۡ إِلَى ٱللَّهِ ثُمَّ يُنَبِّئُهُم بِمَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ
159. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነዚያ ሃይማኖታቸውን ከለያዩና ቡድን ቡድን ከሆኑ (ሰዎች) ጋር አይደለህም:: ነገራቸው ወደ አላህ ብቻ ነው:: ከዚያም ይሰሩት የነበሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
مَن جَآءَ بِٱلۡحَسَنَةِ فَلَهُۥ عَشۡرُ أَمۡثَالِهَاۖ وَمَن جَآءَ بِٱلسَّيِّئَةِ فَلَا يُجۡزَىٰٓ إِلَّا مِثۡلَهَا وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ
160. መልካምን ስራ የሰራ ሁሉ ለእርሱ አስር እጥፍ ምንዳ አሉት:: ክፉ ስራን የሰራ ግን መሰሏን ብቻ እንጂ አይመነዳም:: እነርሱም ቅንጣት አይበደሉም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ إِنَّنِي هَدَىٰنِي رَبِّيٓ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ دِينٗا قِيَمٗا مِّلَّةَ إِبۡرَٰهِيمَ حَنِيفٗاۚ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
161. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ፤ የተስተካከለ ወደሆነው ሃይማኖት የኢብራሂም መንገድ መራኝ:: እሱም ከአጋሪዎች አልነበረም።» በል።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحۡيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
162.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «ስግደቴ፤ መገዛቴ (መስዋዕቴ)፣ ሕይወቴ፤ ሞቴ የሚገባው ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ነው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
لَا شَرِيكَ لَهُۥۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرۡتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلۡمُسۡلِمِينَ
163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለእርሱ (ለአላህ) አጋር የለዉም:: በዚህ (አላህን ከተጋሪ በማጥራት) ታዘዝኩ:: እኔ የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ።» በል።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قُلۡ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ أَبۡغِي رَبّٗا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَيۡءٖۚ وَلَا تَكۡسِبُ كُلُّ نَفۡسٍ إِلَّا عَلَيۡهَاۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰۚ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُم مَّرۡجِعُكُمۡ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ
164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የሁሉ ጌታ ሲሆን ከአላህ በስተቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስ ሁሉ በራሷ ላይ እንጂ ክፉን አትሰራም:: ወንጀለኛ ነፍስ ሁሉ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም:: ከዚያ መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው:: ከዚያም ትለያዩበት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَهُوَ ٱلَّذِي جَعَلَكُمۡ خَلَٰٓئِفَ ٱلۡأَرۡضِ وَرَفَعَ بَعۡضَكُمۡ فَوۡقَ بَعۡضٖ دَرَجَٰتٖ لِّيَبۡلُوَكُمۡ فِي مَآ ءَاتَىٰكُمۡۗ إِنَّ رَبَّكَ سَرِيعُ ٱلۡعِقَابِ وَإِنَّهُۥ لَغَفُورٞ رَّحِيمُۢ
165. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ (አላህ) ያ በምድር ላይ ምትኮች ያደረጋችሁ በሰጣችሁም ጸጋ ሊፈትናችሁ ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በደረጃዎች ከፍ ያደረገ ሃያል ጌታ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ቅጣቱ ፈጣን ነው:: አላህ እጅግ መሀሪና ሩህሩህ ነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
 
Ibisobanuro by'amagambo Isura: Al An’am
Urutonde rw'amasura numero y'urupapuro
 
Ibisobanuro bya qoran ntagatifu - Ibisobanuro bya Qur'an Ntagatifu mu rurimi rw'iki Amhari - Ikigo Nyafurika. - Ishakiro ry'ibisobanuro

Ibisobanuro bya Qur'an Ntagatifu byasobanuwe na Muhammad Zayn Zaher Al-Din. Byasohowe n'Ikigo cya Afurika.

Gufunga