Check out the new design

Përkthimi i kuptimeve të Kuranit Fisnik - Përkthimi emherisht - Akademia e Afrikës * - Përmbajtja e përkthimeve


Përkthimi i kuptimeve Surja: El Isra   Ajeti:
۞ قُلۡ كُونُواْ حِجَارَةً أَوۡ حَدِيدًا
50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በላቸው: «ድንጋዮች ወይም ብረትም ሁኑ፤
Tefsiret në gjuhën arabe:
أَوۡ خَلۡقٗا مِّمَّا يَكۡبُرُ فِي صُدُورِكُمۡۚ فَسَيَقُولُونَ مَن يُعِيدُنَاۖ قُلِ ٱلَّذِي فَطَرَكُمۡ أَوَّلَ مَرَّةٖۚ فَسَيُنۡغِضُونَ إِلَيۡكَ رُءُوسَهُمۡ وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هُوَۖ قُلۡ عَسَىٰٓ أَن يَكُونَ قَرِيبٗا
51. ወይም በልቦቻቸሁ ውስጥ የሚተልቅን ፍጥረትም ሁኑ (መቀስቀሳችሁ አይቀርም።)» «የሚመልሰንም ማነው?» ይላሉም። «ያ በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ ነው።» በላቸው:: ወደ አንተም ራሶቻቸውን ይነቀንቃሉ። «እርሱም መቼ ነው?» ይላሉም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በላቸው: «እርሱ በቅርብ ቀን ሊሆን ይችላል።
Tefsiret në gjuhën arabe:
يَوۡمَ يَدۡعُوكُمۡ فَتَسۡتَجِيبُونَ بِحَمۡدِهِۦ وَتَظُنُّونَ إِن لَّبِثۡتُمۡ إِلَّا قَلِيلٗا
52. «እርሱም የሚጠራችሁንና አላህን አመስጋኞቹ ሆናችሁ ጥሪውን የምትቀበሉበት፤ ጥቂትን ቀናት እንጂ ያልቆያችሁ መሆናችሁን የምትጠራጠሩበት ቀን ነው።» በላቸው::
Tefsiret në gjuhën arabe:
وَقُل لِّعِبَادِي يَقُولُواْ ٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُۚ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ يَنزَغُ بَيۡنَهُمۡۚ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ كَانَ لِلۡإِنسَٰنِ عَدُوّٗا مُّبِينٗا
53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለባሮቼም ንገራቸው:: መልካም የሆነችውን ቃል ብቻ ይናገሩ:: ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና:: ሰይጣን ለሰው ልጆች ግልጽ ጠላት ነውና::
Tefsiret në gjuhën arabe:
رَّبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِكُمۡۖ إِن يَشَأۡ يَرۡحَمۡكُمۡ أَوۡ إِن يَشَأۡ يُعَذِّبۡكُمۡۚ وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ عَلَيۡهِمۡ وَكِيلٗا
54. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁ በእናንተ ሁኔታ አዋቂ ነው:: ቢፈልግ ያዝንላችኋል፤ ቢፈልግም ይቀጣችኃል። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱ ላይ ሀላፊ ሆነህ አላክንህም:: አታስገድዳቸዉም::
Tefsiret në gjuhën arabe:
وَرَبُّكَ أَعۡلَمُ بِمَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۗ وَلَقَدۡ فَضَّلۡنَا بَعۡضَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ عَلَىٰ بَعۡضٖۖ وَءَاتَيۡنَا دَاوُۥدَ زَبُورٗا
55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ አዋቂ ነው:: ከፊሉን ነብያት በከፊሉ ላይ አብልጠናል:: ዳውድንም ዘቡርን ሰጥተነዋል::
Tefsiret në gjuhën arabe:
قُلِ ٱدۡعُواْ ٱلَّذِينَ زَعَمۡتُم مِّن دُونِهِۦ فَلَا يَمۡلِكُونَ كَشۡفَ ٱلضُّرِّ عَنكُمۡ وَلَا تَحۡوِيلًا
56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በለቸው (ጣዖታዊያን ሆይ!) « እነዚያን ከእርሱ ሌላ አማልዕክት የምትሏቸውን እስቲ ጥሯቸው:: ከናንተም ላይ ጉዳትን ማስወገድን ወደ ሌላ ማዞርንም አይችሉም።»።
Tefsiret në gjuhën arabe:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ يَبۡتَغُونَ إِلَىٰ رَبِّهِمُ ٱلۡوَسِيلَةَ أَيُّهُمۡ أَقۡرَبُ وَيَرۡجُونَ رَحۡمَتَهُۥ وَيَخَافُونَ عَذَابَهُۥٓۚ إِنَّ عَذَابَ رَبِّكَ كَانَ مَحۡذُورٗا
57. እነዚያ እነርሱ የሚገዟቸው ማንኛቸዉም (ወደ አላህ) በጣም ቀራቢያቸው እንኳን ለራሳቸው ወደ ጌታቸው መቃረቢያን ሥራ ይፈልጋሉ:: እዝነቱንም ይከጅላሉ:: ቅጣቱንም ይፈራሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቅጣት የሚፈራ ነውና::
Tefsiret në gjuhën arabe:
وَإِن مِّن قَرۡيَةٍ إِلَّا نَحۡنُ مُهۡلِكُوهَا قَبۡلَ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ أَوۡ مُعَذِّبُوهَا عَذَابٗا شَدِيدٗاۚ كَانَ ذَٰلِكَ فِي ٱلۡكِتَٰبِ مَسۡطُورٗا
58. አንዲትም ከተማ የለችም እኛ ከትንሳኤ ቀን በፊት አጥፊዎችዋ ወይም ብርቱን ቅጣት ቀጭዎችዋ ብንሆን እንጂ:: ይህም በመጽሐፍ የተጻፈ ነው::
Tefsiret në gjuhën arabe:
 
Përkthimi i kuptimeve Surja: El Isra
Përmbajtja e sureve Numri i faqes
 
Përkthimi i kuptimeve të Kuranit Fisnik - Përkthimi emherisht - Akademia e Afrikës - Përmbajtja e përkthimeve

Përkthyer nga Muhamed Zein Zehruddin. Botuar nga Akademia e Afrikës.

Mbyll