Check out the new design

Përkthimi i kuptimeve të Kuranit Fisnik - Përkthimi emherisht - Akademia e Afrikës * - Përmbajtja e përkthimeve


Përkthimi i kuptimeve Surja: El A’raf   Ajeti:
وَجَٰوَزۡنَا بِبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱلۡبَحۡرَ فَأَتَوۡاْ عَلَىٰ قَوۡمٖ يَعۡكُفُونَ عَلَىٰٓ أَصۡنَامٖ لَّهُمۡۚ قَالُواْ يَٰمُوسَى ٱجۡعَل لَّنَآ إِلَٰهٗا كَمَا لَهُمۡ ءَالِهَةٞۚ قَالَ إِنَّكُمۡ قَوۡمٞ تَجۡهَلُونَ
138. የኢስራኢል ልጆችን ባህሩን አሻገርናቸው:: ለእነርሱ በሆኑ ጣኦታት መገዛት ላይ በሚዘወትሩ ህዝቦች አጠገብ አለፉም:: «ሙሳ ሆይ! ለእነርሱ ለሰዎቹ አማልክት እንዳሏቸው ሁሉ ለኛም አምላክን አድርግልን።» አሉት:: «እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው።
Tefsiret në gjuhën arabe:
إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ مُتَبَّرٞ مَّا هُمۡ فِيهِ وَبَٰطِلٞ مَّا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
139. «እነዚህ እነርሱ በውስጡ ያሉበት ነገር ጠፊ ነው:: ይሰሩት የነበሩትም ብልሹ ነው።» አላቸው።
Tefsiret në gjuhën arabe:
قَالَ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ أَبۡغِيكُمۡ إِلَٰهٗا وَهُوَ فَضَّلَكُمۡ عَلَى ٱلۡعَٰلَمِينَ
140. «እርሱ ከዓለማት ያበለጣችሁ ሲሆን ከአላህ ሌላ የምትገዙትን አምላክ እፈልግላችኋለሁን?» አለ::
Tefsiret në gjuhën arabe:
وَإِذۡ أَنجَيۡنَٰكُم مِّنۡ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ يَسُومُونَكُمۡ سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ يُقَتِّلُونَ أَبۡنَآءَكُمۡ وَيَسۡتَحۡيُونَ نِسَآءَكُمۡۚ وَفِي ذَٰلِكُم بَلَآءٞ مِّن رَّبِّكُمۡ عَظِيمٞ
141. የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ከፈርዖንም ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ ወንዶች ልጆቻችሁንም የሚገድሉ ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲሆኑ ባዳንናችሁ ጊዜ (የሆነዉን አስታውሱ):: በዚህ ውስጥ ከጌታችሁ የሆነ ከባድ ፈተና አለበት::
Tefsiret në gjuhën arabe:
۞ وَوَٰعَدۡنَا مُوسَىٰ ثَلَٰثِينَ لَيۡلَةٗ وَأَتۡمَمۡنَٰهَا بِعَشۡرٖ فَتَمَّ مِيقَٰتُ رَبِّهِۦٓ أَرۡبَعِينَ لَيۡلَةٗۚ وَقَالَ مُوسَىٰ لِأَخِيهِ هَٰرُونَ ٱخۡلُفۡنِي فِي قَوۡمِي وَأَصۡلِحۡ وَلَا تَتَّبِعۡ سَبِيلَ ٱلۡمُفۡسِدِينَ
142. ነብዩ ሙሳን ሰላሳን ሌሊት (ሊፆምና ልናነጋግረው) ቀጠርነው:: በአስርም (ሌሊት) ሞላናት:: የጌታዉም ቀጠሮ አርባ ሌሊት ሲሆን ተፈጸመ:: ሙሳም ለወንድሙ ለሀሩን «በህዝቦቼ ላይ ተተካኝና አሳምር:: የአጥፊዎችን መንገድ አትከተል።» አለው::
Tefsiret në gjuhën arabe:
وَلَمَّا جَآءَ مُوسَىٰ لِمِيقَٰتِنَا وَكَلَّمَهُۥ رَبُّهُۥ قَالَ رَبِّ أَرِنِيٓ أَنظُرۡ إِلَيۡكَۚ قَالَ لَن تَرَىٰنِي وَلَٰكِنِ ٱنظُرۡ إِلَى ٱلۡجَبَلِ فَإِنِ ٱسۡتَقَرَّ مَكَانَهُۥ فَسَوۡفَ تَرَىٰنِيۚ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُۥ لِلۡجَبَلِ جَعَلَهُۥ دَكّٗا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقٗاۚ فَلَمَّآ أَفَاقَ قَالَ سُبۡحَٰنَكَ تُبۡتُ إِلَيۡكَ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
143. ሙሳ ለቀጠሮው በመጣና ጌታዉም ባነጋገረው ጊዜ፡ «ጌታዬ ሆይ! በእርግጥ ራስህን አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና።» አለ። (አላህም)፡- «እኔን በፍጹም አታየኝም:: ግን ወደ ተራራው ተመልከትና በስፍራው ከረጋ አንተም ታየኛለህ።» አለው:: ጌታዉም ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው:: ሙሳም ጮኸና ወደቀ:: በአንሰራራም ጊዜ «ጌታዬ ጥራት ይገባህ ወደ አንተ ተመለስኩ:: እኔም በጊዜያቴ የአማኞች መጀመሪያ ነኝ።» አለ።
Tefsiret në gjuhën arabe:
 
Përkthimi i kuptimeve Surja: El A’raf
Përmbajtja e sureve Numri i faqes
 
Përkthimi i kuptimeve të Kuranit Fisnik - Përkthimi emherisht - Akademia e Afrikës - Përmbajtja e përkthimeve

Përkthyer nga Muhamed Zein Zehruddin. Botuar nga Akademia e Afrikës.

Mbyll