Check out the new design

அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - ஆபிரிக்கா அகாடமி * - மொழிபெயர்ப்பு அட்டவணை


மொழிபெயர்ப்பு அத்தியாயம்: அல்இஸ்ரா   வசனம்:
ذَٰلِكَ مِمَّآ أَوۡحَىٰٓ إِلَيۡكَ رَبُّكَ مِنَ ٱلۡحِكۡمَةِۗ وَلَا تَجۡعَلۡ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتُلۡقَىٰ فِي جَهَنَّمَ مَلُومٗا مَّدۡحُورًا
39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ጌታህ ከጥበብ ወደ አንተ ካወረደው ነገር ነው:: ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ አታድርግ:: የተወቀስክ፤ የተባረርክ ሆነህ በገሀነም ውስጥ ትጣላለህና::
அரபு விரிவுரைகள்:
أَفَأَصۡفَىٰكُمۡ رَبُّكُم بِٱلۡبَنِينَ وَٱتَّخَذَ مِنَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ إِنَٰثًاۚ إِنَّكُمۡ لَتَقُولُونَ قَوۡلًا عَظِيمٗا
40. (ጣኦታዊያን ሆይ!) ጌታችሁ በወንዶች ልጆች መረጣችሁና ከመላዕክት ሴቶችን ልጆች ለራሱ ያዘን? እናንተ ከባድ ቃልን በእርግጥ ትናገራላችሁ::
அரபு விரிவுரைகள்:
وَلَقَدۡ صَرَّفۡنَا فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ لِيَذَّكَّرُواْ وَمَا يَزِيدُهُمۡ إِلَّا نُفُورٗا
41. ይገሰጹ ዘንድ በዚህ ቁርኣን ውስጥ ደጋግመን በእርግጥ ገለጽን:: ለእነርሱ ግን ከትክክለኛው መንገድ መበርገግን እንጂ ሌላን አይጨምርላቸዉም::
அரபு விரிவுரைகள்:
قُل لَّوۡ كَانَ مَعَهُۥٓ ءَالِهَةٞ كَمَا يَقُولُونَ إِذٗا لَّٱبۡتَغَوۡاْ إِلَىٰ ذِي ٱلۡعَرۡشِ سَبِيلٗا
42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነርሱ እንደሚሉት ከእርሱ ጋር ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ ያን ጊዜ ወደ ዐርሹ ባለቤት መንገድን በፈለጉ ነበር።» በላቸው።
அரபு விரிவுரைகள்:
سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يَقُولُونَ عُلُوّٗا كَبِيرٗا
43. ጥራት ይገባው:: አላህ እነርሱ ከሚሉት ነገር ሁሉ ከፍ ያለን ልቅና ላቀ::
அரபு விரிவுரைகள்:
تُسَبِّحُ لَهُ ٱلسَّمَٰوَٰتُ ٱلسَّبۡعُ وَٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهِنَّۚ وَإِن مِّن شَيۡءٍ إِلَّا يُسَبِّحُ بِحَمۡدِهِۦ وَلَٰكِن لَّا تَفۡقَهُونَ تَسۡبِيحَهُمۡۚ إِنَّهُۥ كَانَ حَلِيمًا غَفُورٗا
44. ሰባቱ ሰማያትና ምድር እንዲሁም በውስጣቸውም ያለው ሁሉ እርሱን ያጠራሉ:: ከነገሩ ሁሉ እሱን ከማመስገን ጋር የሚያጠራው እንጂ አንድም የለም:: ማጥራታቸውን ግን አታውቁትም:: እርሱ ታጋሽና መሓሪ ነው::
அரபு விரிவுரைகள்:
وَإِذَا قَرَأۡتَ ٱلۡقُرۡءَانَ جَعَلۡنَا بَيۡنَكَ وَبَيۡنَ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ حِجَابٗا مَّسۡتُورٗا
45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን ባነበብክ ጊዜ ባንተና በእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም በማያምኑት ሰዎች መካከል የሚሸሸግን ግርዶሽ አድርገናል::
அரபு விரிவுரைகள்:
وَجَعَلۡنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ أَكِنَّةً أَن يَفۡقَهُوهُ وَفِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٗاۚ وَإِذَا ذَكَرۡتَ رَبَّكَ فِي ٱلۡقُرۡءَانِ وَحۡدَهُۥ وَلَّوۡاْ عَلَىٰٓ أَدۡبَٰرِهِمۡ نُفُورٗا
46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዳያውቁትም በልቦቻቸው ላይ ሽፋንን፤ በጆሮቻቸዉም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን:: ጌታህንም ብቻውን ሆኖ በቁርኣን ባወሳሀው ጊዜ የሚሸሹ ሆነው በጀርባዎቻቸዉ ላይ ይዞራሉ::
அரபு விரிவுரைகள்:
نَّحۡنُ أَعۡلَمُ بِمَا يَسۡتَمِعُونَ بِهِۦٓ إِذۡ يَسۡتَمِعُونَ إِلَيۡكَ وَإِذۡ هُمۡ نَجۡوَىٰٓ إِذۡ يَقُولُ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلٗا مَّسۡحُورًا
47. እኛ ወደ አንተ በሚያዳምጡ፤ በሚንሾካሸኩ፤ በዳዮችም እርስ በእርሳቸው «የተደገመበትን ሰው እንጂ አትከተሉም።» በሚሉ ጊዜ የሚያዳምጡበትን ምክንያት አዋቂ ነን።
அரபு விரிவுரைகள்:
ٱنظُرۡ كَيۡفَ ضَرَبُواْ لَكَ ٱلۡأَمۡثَالَ فَضَلُّواْ فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ سَبِيلٗا
48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ላንተ ምሳሌዎችን እንዴት እንዳደረጉልህና ከዚያም እንዴት እንደ ተሳሳቱ ተመልከት:: ወደ እውነቱ ለመድረስ ትክክለኛውን መንገድ መከተል አይችሉም።
அரபு விரிவுரைகள்:
وَقَالُوٓاْ أَءِذَا كُنَّا عِظَٰمٗا وَرُفَٰتًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ خَلۡقٗا جَدِيدٗا
49. አሉም፡- «አጥንቶችና ብስብሶች በሆን ጊዜ እኛ እንዴት እንደገና አዲስ ፍጥረት ሆነን በእርግጥ ተቀስቃሾች እንሆናለን?»
அரபு விரிவுரைகள்:
 
மொழிபெயர்ப்பு அத்தியாயம்: அல்இஸ்ரா
அத்தியாயங்களின் அட்டவணை பக்க எண்
 
அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - ஆபிரிக்கா அகாடமி - மொழிபெயர்ப்பு அட்டவணை

மொழிபெயர்த்தவர் முகமது ஜைன் ஜஹ்ருத்தீன். ஆபிரிக்கா அகாடமி வெளியீடு.

மூடுக