Check out the new design

அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - ஆபிரிக்கா அகாடமி * - மொழிபெயர்ப்பு அட்டவணை


மொழிபெயர்ப்பு அத்தியாயம்: முஹம்மத்   வசனம்:

ሙሀመድ

ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ أَضَلَّ أَعۡمَٰلَهُمۡ
1. እነዚያ የካዱ እና ከአላህ መንገድ ሌሎችን የከለከሉ አላህ ስራዎቻቸውን አጠፋባቸው::
அரபு விரிவுரைகள்:
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَءَامَنُواْ بِمَا نُزِّلَ عَلَىٰ مُحَمَّدٖ وَهُوَ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّهِمۡ كَفَّرَ عَنۡهُمۡ سَيِّـَٔاتِهِمۡ وَأَصۡلَحَ بَالَهُمۡ
2. እነዚያም ያመኑ በጎዎችንም ተግባራት የሰሩ በሙሐመድ ላይም የተወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲሆን እውነት ስለሆነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያብሳል:: ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል::
அரபு விரிவுரைகள்:
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱتَّبَعُواْ ٱلۡبَٰطِلَ وَأَنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّبَعُواْ ٱلۡحَقَّ مِن رَّبِّهِمۡۚ كَذَٰلِكَ يَضۡرِبُ ٱللَّهُ لِلنَّاسِ أَمۡثَٰلَهُمۡ
3.ይህ እነዚያ የካዱት ውሸትን የተከተሉ በመሆናቸውና እነዚያም ያመኑት ከጌታቸው የሆነን እውነት ስለተከተሉ ነው:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለሰዎች ምሳሌዎቻቸውን ያብራራል።
அரபு விரிவுரைகள்:
فَإِذَا لَقِيتُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَضَرۡبَ ٱلرِّقَابِ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَثۡخَنتُمُوهُمۡ فَشُدُّواْ ٱلۡوَثَاقَ فَإِمَّا مَنَّۢا بَعۡدُ وَإِمَّا فِدَآءً حَتَّىٰ تَضَعَ ٱلۡحَرۡبُ أَوۡزَارَهَاۚ ذَٰلِكَۖ وَلَوۡ يَشَآءُ ٱللَّهُ لَٱنتَصَرَ مِنۡهُمۡ وَلَٰكِن لِّيَبۡلُوَاْ بَعۡضَكُم بِبَعۡضٖۗ وَٱلَّذِينَ قُتِلُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ فَلَن يُضِلَّ أَعۡمَٰلَهُمۡ
4. አማኞች ሆይ! እነዚያንም የካዱትን ሰዎች በጦር ላይ ባገኛችኋቸው ጊዜ ጫንቃዎችን በሀይል ምቱ:: ባደከማችኋቸው ጊዜም አትግደሏቸው፤ ማርኳቸው:: መሳሪያውንም አጥብቁ:: በኋላም በነጻ ትለቋቸዋላችሁ:: ወይም ፊዳ ታስከፍሏቸዋላችሁ:: ይህም ጦሩ መሳሪያዉን እስከሚጥል ድረስ ነው:: ነገሩ ይህ ነው:: አላህም ቢፈልግ ከእነርሱ ያለ ጦር በተበቀለ ነበር ግን ከፊላችሁን በከፊሉ ሊሞክር (በዚህ አዘዛችሁ)። እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉት ሰዎች ስራዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸዉም::
அரபு விரிவுரைகள்:
سَيَهۡدِيهِمۡ وَيُصۡلِحُ بَالَهُمۡ
5. በእርግጥ ይመራቸዋል:: ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል::
அரபு விரிவுரைகள்:
وَيُدۡخِلُهُمُ ٱلۡجَنَّةَ عَرَّفَهَا لَهُمۡ
6. ገነትንም ያገባቸዋል፡፡ ለእነርሱ አስታውቋታል፡፡
அரபு விரிவுரைகள்:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِن تَنصُرُواْ ٱللَّهَ يَنصُرۡكُمۡ وَيُثَبِّتۡ أَقۡدَامَكُمۡ
7. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የአላህን ሃይማኖት ብትረዱ ይረዳችኋል:: ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል።ያጸናላችኋል።
அரபு விரிவுரைகள்:
وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَتَعۡسٗا لَّهُمۡ وَأَضَلَّ أَعۡمَٰلَهُمۡ
8. እነዚያም የካዱት ለእነርሱ ጥፋት ተገባቸው:: ስራዎቻቸውንም አጠፋባቸው።
அரபு விரிவுரைகள்:
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ كَرِهُواْ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فَأَحۡبَطَ أَعۡمَٰلَهُمۡ
9. ይህ እነርሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው:: ስለዚህ ስራዎቻቸውን አበላሸባቸው::
அரபு விரிவுரைகள்:
۞ أَفَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۖ دَمَّرَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡۖ وَلِلۡكَٰفِرِينَ أَمۡثَٰلُهَا
10. የእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩ ከሓዲያን ሁሉ መጨረሻ እንዴት እንደነበር ያዩ ዘንድ በምድር ላይ አልሄዱምን? አላህ ያላቸውን ሁሉ አጠፋባቸው። ለካሓዲያንም ሁሉ የዚሁ ተመሳሳይ አለባቸው።
அரபு விரிவுரைகள்:
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ مَوۡلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَأَنَّ ٱلۡكَٰفِرِينَ لَا مَوۡلَىٰ لَهُمۡ
11. ይህ አላህ የእነዚያ ያመኑት ረዳት ስለሆነና ከሓዲያንም ለእነርሱ ረዳት ስሌላቸው ነው::
அரபு விரிவுரைகள்:
 
மொழிபெயர்ப்பு அத்தியாயம்: முஹம்மத்
அத்தியாயங்களின் அட்டவணை பக்க எண்
 
அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - ஆபிரிக்கா அகாடமி - மொழிபெயர்ப்பு அட்டவணை

மொழிபெயர்த்தவர் முகமது ஜைன் ஜஹ்ருத்தீன். ஆபிரிக்கா அகாடமி வெளியீடு.

மூடுக