Check out the new design

அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - ஆபிரிக்கா அகாடமி * - மொழிபெயர்ப்பு அட்டவணை


மொழிபெயர்ப்பு அத்தியாயம்: அல்மஆரிஜ்   வசனம்:

አል መዓሪጅ

سَأَلَ سَآئِلُۢ بِعَذَابٖ وَاقِعٖ
1. ወዳቂ (ተከሳች) ከሆነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ::
அரபு விரிவுரைகள்:
لِّلۡكَٰفِرِينَ لَيۡسَ لَهُۥ دَافِعٞ
2. ከሓዲያን ላይ (ወዳቂ ከሆነው) ለእርሱ መላሽ የለዉም።
அரபு விரிவுரைகள்:
مِّنَ ٱللَّهِ ذِي ٱلۡمَعَارِجِ
3. የ (ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከሆነው አላህ (መላሽ የለዉም)::
அரபு விரிவுரைகள்:
تَعۡرُجُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَٱلرُّوحُ إِلَيۡهِ فِي يَوۡمٖ كَانَ مِقۡدَارُهُۥ خَمۡسِينَ أَلۡفَ سَنَةٖ
4. መላዕክትና መንፈሱም ልኩ ሀምሳ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ (ይወጣሉ)::
அரபு விரிவுரைகள்:
فَٱصۡبِرۡ صَبۡرٗا جَمِيلًا
5. መልካምን ትዕግስት ታገስ::
அரபு விரிவுரைகள்:
إِنَّهُمۡ يَرَوۡنَهُۥ بَعِيدٗا
6. እነርሱ ያንን ቀን ሩቅ አድርገው ያዩታል::
அரபு விரிவுரைகள்:
وَنَرَىٰهُ قَرِيبٗا
7. እኛም ቅርብ ሆኖ እናየዋለን::
அரபு விரிவுரைகள்:
يَوۡمَ تَكُونُ ٱلسَّمَآءُ كَٱلۡمُهۡلِ
8. ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትሆንበት ቀን፤
அரபு விரிவுரைகள்:
وَتَكُونُ ٱلۡجِبَالُ كَٱلۡعِهۡنِ
9. ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ንፋስ) እንደበተነውና እንደሚያበረው በሚሆኑበት ቀን፤
அரபு விரிவுரைகள்:
وَلَا يَسۡـَٔلُ حَمِيمٌ حَمِيمٗا
10. ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን መላሽ የለዉም::
அரபு விரிவுரைகள்:
يُبَصَّرُونَهُمۡۚ يَوَدُّ ٱلۡمُجۡرِمُ لَوۡ يَفۡتَدِي مِنۡ عَذَابِ يَوۡمِئِذِۭ بِبَنِيهِ
11. (ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፤ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ቤዛ ሊያደርግ ይመኛል::
அரபு விரிவுரைகள்:
وَصَٰحِبَتِهِۦ وَأَخِيهِ
12. በሚስቱም በወንድሙም፤
அரபு விரிவுரைகள்:
وَفَصِيلَتِهِ ٱلَّتِي تُـٔۡوِيهِ
13. በዚያች በምታስጠጋው ጎሳውም፤
அரபு விரிவுரைகள்:
وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا ثُمَّ يُنجِيهِ
14. በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያ ሊያድነው (ይመኛል)::
அரபு விரிவுரைகள்:
كَلَّآۖ إِنَّهَا لَظَىٰ
15. ይተው፤እርሷ (እሳቲቱ) ነዲድ እሳት ናት።
அரபு விரிவுரைகள்:
نَزَّاعَةٗ لِّلشَّوَىٰ
16. የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትሆን፤
அரபு விரிவுரைகள்:
تَدۡعُواْ مَنۡ أَدۡبَرَ وَتَوَلَّىٰ
17. (ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደ እርሷ) ትጠራለች::
அரபு விரிவுரைகள்:
وَجَمَعَ فَأَوۡعَىٰٓ
18. ገንዘብን የሰበሰበንና ዘካውን ሳይሰጥ የቆጠረንም (ትጠራለች)::
அரபு விரிவுரைகள்:
۞ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ خُلِقَ هَلُوعًا
19. ሰው ቅጠ ቢስ ሆኖ ተፈጠረ::
அரபு விரிவுரைகள்:
إِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ جَزُوعٗا
20. ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጭተኛ፤
அரபு விரிவுரைகள்:
وَإِذَا مَسَّهُ ٱلۡخَيۡرُ مَنُوعًا
21. መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘው ጊዜ ከልካይ ሆኖ ተፈጠረ::
அரபு விரிவுரைகள்:
إِلَّا ٱلۡمُصَلِّينَ
22. ሰጋጆች ብቻ ሲቀሩ::
அரபு விரிவுரைகள்:
ٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ دَآئِمُونَ
23. እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘወታሪዎች የሆኑት::
அரபு விரிவுரைகள்:
وَٱلَّذِينَ فِيٓ أَمۡوَٰلِهِمۡ حَقّٞ مَّعۡلُومٞ
24. እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የሆኑት፤
அரபு விரிவுரைகள்:
لِّلسَّآئِلِ وَٱلۡمَحۡرُومِ
25. ለለማኝ እና ከልመና ለሚቆጠብም መብት (ያለባቸው የሆኑ)፤
அரபு விரிவுரைகள்:
وَٱلَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ
26. እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት የሚያረጋግጡ::
அரபு விரிவுரைகள்:
وَٱلَّذِينَ هُم مِّنۡ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشۡفِقُونَ
27. እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የሆኑት::
அரபு விரிவுரைகள்:
إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمۡ غَيۡرُ مَأۡمُونٖ
28. የጌታቸው ቅጣት የማያስተማምን ነውና።
அரபு விரிவுரைகள்:
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِفُرُوجِهِمۡ حَٰفِظُونَ
29. እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፤
அரபு விரிவுரைகள்:
إِلَّا عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَإِنَّهُمۡ غَيۡرُ مَلُومِينَ
30. በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው ባሮች ላይ ሲቀር:: እነርሱ በነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና::
அரபு விரிவுரைகள்:
فَمَنِ ٱبۡتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡعَادُونَ
31. ከዚያ ወዲያ የፈለገ እነዚያ እነርሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው።
அரபு விரிவுரைகள்:
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِأَمَٰنَٰتِهِمۡ وَعَهۡدِهِمۡ رَٰعُونَ
32. እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የሆኑት::
அரபு விரிவுரைகள்:
وَٱلَّذِينَ هُم بِشَهَٰدَٰتِهِمۡ قَآئِمُونَ
33. እነዚያም እነርሱ በምስክሮቻቸው ላይ ቀጥ ያሉት::
அரபு விரிவுரைகள்:
وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ يُحَافِظُونَ
34. እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት::
அரபு விரிவுரைகள்:
أُوْلَٰٓئِكَ فِي جَنَّٰتٖ مُّكۡرَمُونَ
35. እነዚያ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው::
அரபு விரிவுரைகள்:
فَمَالِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ قِبَلَكَ مُهۡطِعِينَ
36. እነዚያ (በአላህ) የካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?
அரபு விரிவுரைகள்:
عَنِ ٱلۡيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ عِزِينَ
37. ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ቡድኖች ሲሆኑ፤
அரபு விரிவுரைகள்:
أَيَطۡمَعُ كُلُّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُمۡ أَن يُدۡخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٖ
38. ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?
அரபு விரிவுரைகள்:
كَلَّآۖ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّمَّا يَعۡلَمُونَ
39. ይከልከል፤ በፍጹም እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍተወት ጠብታ) ፈጠርናቸው::
அரபு விரிவுரைகள்:
فَلَآ أُقۡسِمُ بِرَبِّ ٱلۡمَشَٰرِقِ وَٱلۡمَغَٰرِبِ إِنَّا لَقَٰدِرُونَ
40. (እናም ጉዳዩ ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: በምስራቆችና በምዕራቦች ጌታ እምላለሁ፤ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን::
அரபு விரிவுரைகள்:
عَلَىٰٓ أَن نُّبَدِّلَ خَيۡرٗا مِّنۡهُمۡ وَمَا نَحۡنُ بِمَسۡبُوقِينَ
41. ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም::
அரபு விரிவுரைகள்:
فَذَرۡهُمۡ يَخُوضُواْ وَيَلۡعَبُواْ حَتَّىٰ يُلَٰقُواْ يَوۡمَهُمُ ٱلَّذِي يُوعَدُونَ
42. ያንንም የሚሰፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚያገኙ ድረስ ተዋቸው፤ በአሉባልታዎችም ዉስጥ ይዋኙ፤ ይጫወቱም።
அரபு விரிவுரைகள்:
يَوۡمَ يَخۡرُجُونَ مِنَ ٱلۡأَجۡدَاثِ سِرَاعٗا كَأَنَّهُمۡ إِلَىٰ نُصُبٖ يُوفِضُونَ
43. ያ ቀን ወደ ጣዖት እንደሚሽቀዳደሙ ሆነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን ነው::
அரபு விரிவுரைகள்:
خَٰشِعَةً أَبۡصَٰرُهُمۡ تَرۡهَقُهُمۡ ذِلَّةٞۚ ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمُ ٱلَّذِي كَانُواْ يُوعَدُونَ
44. ዓይኖቻቸው ያፈሩ ሆነው፤ ውርደት ትሸፍናቸዋለች:: ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቀን ነው::
அரபு விரிவுரைகள்:
 
மொழிபெயர்ப்பு அத்தியாயம்: அல்மஆரிஜ்
அத்தியாயங்களின் அட்டவணை பக்க எண்
 
அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - ஆபிரிக்கா அகாடமி - மொழிபெயர்ப்பு அட்டவணை

மொழிபெயர்த்தவர் முகமது ஜைன் ஜஹ்ருத்தீன். ஆபிரிக்கா அகாடமி வெளியீடு.

மூடுக