Check out the new design

పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ * - అనువాదాల విషయసూచిక


భావార్ధాల అనువాదం సూరహ్: అల్-బఖరహ్   వచనం:
وَلَن تَرۡضَىٰ عَنكَ ٱلۡيَهُودُ وَلَا ٱلنَّصَٰرَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمۡۗ قُلۡ إِنَّ هُدَى ٱللَّهِ هُوَ ٱلۡهُدَىٰۗ وَلَئِنِ ٱتَّبَعۡتَ أَهۡوَآءَهُم بَعۡدَ ٱلَّذِي جَآءَكَ مِنَ ٱلۡعِلۡمِ مَا لَكَ مِنَ ٱللَّهِ مِن وَلِيّٖ وَلَا نَصِيرٍ
120. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድም ሆኑ ክርስቲያኖች የየራሳቸውን ሀይማኖትን እስከምትከተል ድረስ ፈጽሞ አይደሰቱብህም:: «ትክክለኛው መንገድ በእርግጥ የአላህ አመራር ነው።» በላቸው። ትክክለኛው እውቀት ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል አንተን ከአላህ የሚከላከልልህ ወዳጅም ሆነ ረዳት የለህም::
అరబీ భాషలోని ఖుర్ఆన్ వ్యాఖ్యానాలు:
ٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ يَتۡلُونَهُۥ حَقَّ تِلَاوَتِهِۦٓ أُوْلَٰٓئِكَ يُؤۡمِنُونَ بِهِۦۗ وَمَن يَكۡفُرۡ بِهِۦ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ
121. እነዚያ መጽሐፉን የሰጠናቸው ሰዎች ተገቢ ንባቡን ያነቡታል:: በእርሱም ያምናሉ:: እነዚያ በእርሱ የሚክዱ ግን ከሳሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው::
అరబీ భాషలోని ఖుర్ఆన్ వ్యాఖ్యానాలు:
يَٰبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱذۡكُرُواْ نِعۡمَتِيَ ٱلَّتِيٓ أَنۡعَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ وَأَنِّي فَضَّلۡتُكُمۡ عَلَى ٱلۡعَٰلَمِينَ
122. እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ! እኔ ያ በእናንተ ላይ የለገስኳችሁን ጸጋዎቼንና (በዘመናችሁ ከነበሩት) የዓለማት ሕዝቦች በላይ ያበለጥኳችሁ መሆኔን አስታውሱ።
అరబీ భాషలోని ఖుర్ఆన్ వ్యాఖ్యానాలు:
وَٱتَّقُواْ يَوۡمٗا لَّا تَجۡزِي نَفۡسٌ عَن نَّفۡسٖ شَيۡـٔٗا وَلَا يُقۡبَلُ مِنۡهَا عَدۡلٞ وَلَا تَنفَعُهَا شَفَٰعَةٞ وَلَا هُمۡ يُنصَرُونَ
123. አንዲት (አማኝ) ነፍስ ለሌላ (ከሓዲ) ነፍስ ምንንም የማትጠቅምበትን፤ ከእርሷም ቤዛ የማይወሰድበትን፤ ምልጃም ለእርሷ የማትፈይድበትን፤ እነርሱም ከየትም በኩል የማይረዱበትን ቀን ተጠንቀቁ፡፡
అరబీ భాషలోని ఖుర్ఆన్ వ్యాఖ్యానాలు:
۞ وَإِذِ ٱبۡتَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِـۧمَ رَبُّهُۥ بِكَلِمَٰتٖ فَأَتَمَّهُنَّۖ قَالَ إِنِّي جَاعِلُكَ لِلنَّاسِ إِمَامٗاۖ قَالَ وَمِن ذُرِّيَّتِيۖ قَالَ لَا يَنَالُ عَهۡدِي ٱلظَّٰلِمِينَ
124. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂምን ጌታው በትዕዛዛት በፈተነውና በፈጸማቸውም ጊዜ (የነበረውን ታሪክ አስታውስ):: «እኔ የሰው ዘር መሪ አድርጌሀላሁ።» አለው:: ኢብራሂምም «ከዘሮቼም አድርግ?» ሲል ጠየቀ:: አላህም «ኢብራሂም ሆይ! ቃል ኪዳኔ ለግፈኛ አጥፊዎች ተፈፃሚ አይሆንም እንጂ።» አለው።
అరబీ భాషలోని ఖుర్ఆన్ వ్యాఖ్యానాలు:
وَإِذۡ جَعَلۡنَا ٱلۡبَيۡتَ مَثَابَةٗ لِّلنَّاسِ وَأَمۡنٗا وَٱتَّخِذُواْ مِن مَّقَامِ إِبۡرَٰهِـۧمَ مُصَلّٗىۖ وَعَهِدۡنَآ إِلَىٰٓ إِبۡرَٰهِـۧمَ وَإِسۡمَٰعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيۡتِيَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلۡعَٰكِفِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ
125. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቤቱንም (ከዕባን) ለሰዎች መሰባሰቢያና የሰላም ማዕከል ባደረግን ጊዜ የነበረውን ታሪክ አሰታውስ:: (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከኢብራሂም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ:: ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ {1}
(1) ቤቱን የምለው ከእባን ነው የምያመለክተው
అరబీ భాషలోని ఖుర్ఆన్ వ్యాఖ్యానాలు:
وَإِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِـۧمُ رَبِّ ٱجۡعَلۡ هَٰذَا بَلَدًا ءَامِنٗا وَٱرۡزُقۡ أَهۡلَهُۥ مِنَ ٱلثَّمَرَٰتِ مَنۡ ءَامَنَ مِنۡهُم بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۚ قَالَ وَمَن كَفَرَ فَأُمَتِّعُهُۥ قَلِيلٗا ثُمَّ أَضۡطَرُّهُۥٓ إِلَىٰ عَذَابِ ٱلنَّارِۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ
126. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም «ጌታዬ ሆይ! ይህንን ሀገር (መካን) ሰላማዊ ሀገር አድርገው:: ከኗሪዉም መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነውን ክፍል ከፍራፍሬዎች ሲሳይ ስጠው።» ባለ ጊዜ (የነበረውን ታሪክ አስታውስ):: አላህም «የካደውንም በጥቂቱ እንዲጎናጸፍ አደርገዋለሁ:: ከዚያ ወደ እሳት ቅጣት እዳርገዋለሁ:: ይህም እጅግ አስከፊ መመለሻ ነው።» አለ
అరబీ భాషలోని ఖుర్ఆన్ వ్యాఖ్యానాలు:
 
భావార్ధాల అనువాదం సూరహ్: అల్-బఖరహ్
సూరాల విషయసూచిక పేజీ నెంబరు
 
పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ - అనువాదాల విషయసూచిక

దాని అనువాదము మహ్మద్ జీన్ జహ్రుద్దీన్. ఆఫ్రికా అకాడమీ నుండి విడుదల.

మూసివేయటం