Check out the new design

قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى * - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى


مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: بەقەرە   ئايەت:
وَقَالُواْ كُونُواْ هُودًا أَوۡ نَصَٰرَىٰ تَهۡتَدُواْۗ قُلۡ بَلۡ مِلَّةَ إِبۡرَٰهِـۧمَ حَنِيفٗاۖ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
135. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድና ክርስቲያኖች በየበኩላቸው “አይሁድ ወይም ክርስቲያን ሁኑ ቅንን መንገድ ትመራላችሁና” አሉ:: “አይደለም ይልቁንም የኢብራሂምን ሀይማኖት ቀጥተኛ ሲሆን እንከተላለን፣ ኢብራሂምም ከአጋሪዎችም አልነበረም” በላቸው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
قُولُوٓاْ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيۡنَا وَمَآ أُنزِلَ إِلَىٰٓ إِبۡرَٰهِـۧمَ وَإِسۡمَٰعِيلَ وَإِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ وَٱلۡأَسۡبَاطِ وَمَآ أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَآ أُوتِيَ ٱلنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمۡ لَا نُفَرِّقُ بَيۡنَ أَحَدٖ مِّنۡهُمۡ وَنَحۡنُ لَهُۥ مُسۡلِمُونَ
136. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) «በአላህና ወደ እኛ በተወረደው ቁርኣን ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሀቅም፣ ወደ የዕቁብና ወደ ነገዶችም በተወረደው መለኮታዊ መልዕክት ሁሉ በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት፤ በዚያም ነብያት ሁሉ ከጌታቸው በተለገሱት ከእነርሱ አንዱን ከሌላው የማንለይ ስንሆን አመንን:: እኛም (ለአላህ) ፍጹም ታዛዦች ነን።» በሉ።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَإِنۡ ءَامَنُواْ بِمِثۡلِ مَآ ءَامَنتُم بِهِۦ فَقَدِ ٱهۡتَدَواْۖ وَّإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنَّمَا هُمۡ فِي شِقَاقٖۖ فَسَيَكۡفِيكَهُمُ ٱللَّهُۚ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
137. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እናንተ ባመናችሁበት መልኩ ካመኑ በእርግጥ በትክክለኛው ጎዳና ላይ ናቸው:: ከእርሱ ካፈነገጡ ግን እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው:: የእነርሱንም ተንኮል አላህ ይበቃሀል:: እርሱም ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
صِبۡغَةَ ٱللَّهِ وَمَنۡ أَحۡسَنُ مِنَ ٱللَّهِ صِبۡغَةٗۖ وَنَحۡنُ لَهُۥ عَٰبِدُونَ
138. የአላህን የተፈጥሮ መንከር (እምነት) ያዙ:: በመንከርም ከአላህ ይበልጥ ያማረ ማነው? (ማንም የለም):: እኛም ለእርሱ ብቻ ተገዢዎች ነን (በሉ)፡፡
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
قُلۡ أَتُحَآجُّونَنَا فِي ٱللَّهِ وَهُوَ رَبُّنَا وَرَبُّكُمۡ وَلَنَآ أَعۡمَٰلُنَا وَلَكُمۡ أَعۡمَٰلُكُمۡ وَنَحۡنُ لَهُۥ مُخۡلِصُونَ
139. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ጌታችንና ጌታችሁ ሲሆን ለእኛም ስራችን ያለን ስንሆን ለእናንተም ስራችሁ ያላችሁ ስትሆኑ እኛም ስራችንን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች ሆነን ሳለን በአላህ (ሀይማኖት) ትከራከሩናላችሁን?» በላቸው።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
أَمۡ تَقُولُونَ إِنَّ إِبۡرَٰهِـۧمَ وَإِسۡمَٰعِيلَ وَإِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ وَٱلۡأَسۡبَاطَ كَانُواْ هُودًا أَوۡ نَصَٰرَىٰۗ قُلۡ ءَأَنتُمۡ أَعۡلَمُ أَمِ ٱللَّهُۗ وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن كَتَمَ شَهَٰدَةً عِندَهُۥ مِنَ ٱللَّهِۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ
140. ወይስ «ኢብራሂምም፣ ኢስማዒልም፣ ኢስሐቅም፣ ያዕቆብም፣ እንዲሁም ነገዶቹም አይሁድ ወይም ክርስቲያኖች ነበሩ» ትላላችሁን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) “እናንተ ናችሁ የምታውቁት? ወይንስ አላህ?” በላቸው:: እርሱ ዘንድ ከአላህ የሆነችን ምስክርነት ከደበቀ ይበልጥ አጥፊ ማነው? አላህ የምትፈጽሙትን ሁሉ ዘንጊ አይደለም።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
تِلۡكَ أُمَّةٞ قَدۡ خَلَتۡۖ لَهَا مَا كَسَبَتۡ وَلَكُم مَّا كَسَبۡتُمۡۖ وَلَا تُسۡـَٔلُونَ عَمَّا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
141. እነዚህ ያለፉ ሕዝቦች ናቸው:: ለእነርሱ የሰሩት አላቸው:: ለእናንተም የሰራችሁት አላችሁ:: እነርሱ ይሰሩት ከነበሩት ሁሉ አትጠየቁም::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
 
مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: بەقەرە
سۈرە مۇندەرىجىسى بەت نومۇرى
 
قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى

مۇھەممەد زەين زەھرىدىن تەرجىمە قىلغان. ئافرىقا ئاكادېمىيىسى تەرىپىدىن نەشر قىلىنغان.

تاقاش