Check out the new design

قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی * - ترجمے کی لسٹ


معانی کا ترجمہ سورت: یونس   آیت:
۞ وَٱتۡلُ عَلَيۡهِمۡ نَبَأَ نُوحٍ إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِۦ يَٰقَوۡمِ إِن كَانَ كَبُرَ عَلَيۡكُم مَّقَامِي وَتَذۡكِيرِي بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَعَلَى ٱللَّهِ تَوَكَّلۡتُ فَأَجۡمِعُوٓاْ أَمۡرَكُمۡ وَشُرَكَآءَكُمۡ ثُمَّ لَا يَكُنۡ أَمۡرُكُمۡ عَلَيۡكُمۡ غُمَّةٗ ثُمَّ ٱقۡضُوٓاْ إِلَيَّ وَلَا تُنظِرُونِ
71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የኑህንም ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው:: ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውሱ «ህዝቦቼ ሆይ! በእናንተ ውስጥ ብዙን ጊዜ መቆየቴ የአላህንም ተዓምራት ለእናንተ ማስታወሴ በእናንተ ላይ የከበደ ቢሆንባችሁም በአላህ ላይ ተጠግቻለሁ:: ነገራችሁንም ከምታጋሯቸው ጣኦታት ጋር ሆናችሁ እስቲ ቁረጡ:: ከዚያም ነገራችሁ በእናንተ ላይ ድብቅ አይሁን ግለጹት:: ከዚያም የሻችሁትን ወደ እኔ አድርሱ:: ጊዜም አትስጡኝ (ከምንም አልቆጥራችሁም)::
عربی تفاسیر:
فَإِن تَوَلَّيۡتُمۡ فَمَا سَأَلۡتُكُم مِّنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِۖ وَأُمِرۡتُ أَنۡ أَكُونَ مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ
72. «ብትሸሹም (አትጎዱኝም::) ከምንዳ ምንንም አለመንኳችሁምና:: ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለምና:: ከሙስሊሞች እንድሆንም ታዝዣለሁ።»
عربی تفاسیر:
فَكَذَّبُوهُ فَنَجَّيۡنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ فِي ٱلۡفُلۡكِ وَجَعَلۡنَٰهُمۡ خَلَٰٓئِفَ وَأَغۡرَقۡنَا ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَاۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُنذَرِينَ
73. አስተባበሉት እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች በታንኳይቱ ውስጥ አዳንናቸው:: ለጠፉት ምትኮች አደረግናቸው:: እነዚያንም በአናቅጻችን ያስተባበሉትን አሰመጥን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተስፈራሩት ህዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበር እስቲ ተመልከት::
عربی تفاسیر:
ثُمَّ بَعَثۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِۦ رُسُلًا إِلَىٰ قَوۡمِهِمۡ فَجَآءُوهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَمَا كَانُواْ لِيُؤۡمِنُواْ بِمَا كَذَّبُواْ بِهِۦ مِن قَبۡلُۚ كَذَٰلِكَ نَطۡبَعُ عَلَىٰ قُلُوبِ ٱلۡمُعۡتَدِينَ
74. ከዚያም ከእርሱ በኋላ መልዕክተኞችን ወደየ ህዝቦቻቸው ላክን:: በግልጽ ማስረጃዎችም መጡላቸው:: ከመላካቸው በፊት ባስተባበሉት ነገር የሚያምኑ አልሆኑም:: ልክ እንደዚሁ በወሰን አላፊዎች ልቦች ላይ እናትማለን::
عربی تفاسیر:
ثُمَّ بَعَثۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِم مُّوسَىٰ وَهَٰرُونَ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ بِـَٔايَٰتِنَا فَٱسۡتَكۡبَرُواْ وَكَانُواْ قَوۡمٗا مُّجۡرِمِينَ
75. ከዚያም ከእነርሱ በኋላ ሙሳንና ሃሩንን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቱ በተአምራታችን ላክን:: ኮሩም:: ትእቢተኞች ህዝቦችም ነበሩ::
عربی تفاسیر:
فَلَمَّا جَآءَهُمُ ٱلۡحَقُّ مِنۡ عِندِنَا قَالُوٓاْ إِنَّ هَٰذَا لَسِحۡرٞ مُّبِينٞ
76. ከእኛም ዘንድ እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምት ነው።» አሉ።
عربی تفاسیر:
قَالَ مُوسَىٰٓ أَتَقُولُونَ لِلۡحَقِّ لَمَّا جَآءَكُمۡۖ أَسِحۡرٌ هَٰذَا وَلَا يُفۡلِحُ ٱلسَّٰحِرُونَ
77. ሙሳ አለ፡- «እውነቱን በመጣላችሁ ጊዜ ድግምተኞች የማይድኑ ሲኾኑ (እርሱ ድግምት ነው) ትላላችሁን?ይህ ድግምት ነውን?»
عربی تفاسیر:
قَالُوٓاْ أَجِئۡتَنَا لِتَلۡفِتَنَا عَمَّا وَجَدۡنَا عَلَيۡهِ ءَابَآءَنَا وَتَكُونَ لَكُمَا ٱلۡكِبۡرِيَآءُ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا نَحۡنُ لَكُمَا بِمُؤۡمِنِينَ
78. እነርሱም «አባቶቻችንን ካገኘንበት ሃይማኖት ልታዞሩንና በምድር ውስጥ ለእናንተም ኩራት ሹመት ልትኖራችሁ መጣህብን:: እኛ ለእናንተ በፍጹም አማኞች አይደለንም።» አሉ::
عربی تفاسیر:
 
معانی کا ترجمہ سورت: یونس
سورتوں کی لسٹ صفحہ نمبر
 
قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی - ترجمے کی لسٹ

محمد زین زہر الدین نے ترجمہ کیا۔ افریقہ اکیڈمی کی جانب سے شائع ہوا۔

بند کریں