Check out the new design

قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی * - ترجمے کی لسٹ


معانی کا ترجمہ سورت: شعراء   آیت:
قَالَ وَمَا عِلۡمِي بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
112. እርሱም አላቸው፡- «ይሰሩት በነበሩት ነገር ምን ዕውቀት አለኝና?
عربی تفاسیر:
إِنۡ حِسَابُهُمۡ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّيۖ لَوۡ تَشۡعُرُونَ
113. «ምርመራቸው በጌታዬ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም:: ብታውቁ ኖሮ ይህንን ትረዱት ነበር።
عربی تفاسیر:
وَمَآ أَنَا۠ بِطَارِدِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
114. «እኔ አማኞችን አባራሪ አይደለሁም።
عربی تفاسیر:
إِنۡ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٞ مُّبِينٞ
115. «እኔም እኮ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» (አለ)
عربی تفاسیر:
قَالُواْ لَئِن لَّمۡ تَنتَهِ يَٰنُوحُ لَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمَرۡجُومِينَ
116. «ኑህ ሆይ! ከምትለው ባትከለከል በእርግጥ ከሚወገሩት ትሆናለህ።» አሉት።
عربی تفاسیر:
قَالَ رَبِّ إِنَّ قَوۡمِي كَذَّبُونِ
117. እርሱም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! ህዝቦቼ አስተባበሉኝ።
عربی تفاسیر:
فَٱفۡتَحۡ بَيۡنِي وَبَيۡنَهُمۡ فَتۡحٗا وَنَجِّنِي وَمَن مَّعِيَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
118. «በእኔና በእነርሱም መካከል ተገቢ ፍርድን ፍረድ:: ከእነርሱ አድነኝም:: ከእኔ ጋር ያሉትን አማኞችም አድን።»
عربی تفاسیر:
فَأَنجَيۡنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ فِي ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ
119. እርሱንም ሆነ ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ በተሞላው መርከብ ውስጥ አዳንን::
عربی تفاسیر:
ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا بَعۡدُ ٱلۡبَاقِينَ
120. ከዚያም በኋላ ቀሪዎቹን አሰመጥን።
عربی تفاسیر:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
121. በዚህ ውስጥ ታላቅ ግሣጼ አለበት፤ አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም::
عربی تفاسیر:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
122. ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊዉና አዛኙ ነው::
عربی تفاسیر:
كَذَّبَتۡ عَادٌ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
123. ዓድ መልዕክተኞችን አስተባበለች፤
عربی تفاسیر:
إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ هُودٌ أَلَا تَتَّقُونَ
124. ወንድማቸው ሁድ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?
عربی تفاسیر:
إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ
125. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።
عربی تفاسیر:
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
126. «አላህን ብቻ ፍሩ ታዘዙኝም።
عربی تفاسیر:
وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
127. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ ብቻ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም።
عربی تفاسیر:
أَتَبۡنُونَ بِكُلِّ رِيعٍ ءَايَةٗ تَعۡبَثُونَ
128. «የምትጫወቱ ሆናችሁ በከፍተኛ ስፍራ ሁሉ ላይ ምልክት ትገነባላችሁን?
عربی تفاسیر:
وَتَتَّخِذُونَ مَصَانِعَ لَعَلَّكُمۡ تَخۡلُدُونَ
129. «የውሃ ማጠራቀሚያዎችንና ህንፃዎችንም ለዘላለም መኖርን የምትከጅሉ ሆናችሁ ትሰራላችሁን?
عربی تفاسیر:
وَإِذَا بَطَشۡتُم بَطَشۡتُمۡ جَبَّارِينَ
130. «በቀጣችሁም ጊዜ ጨካኞች ሆናችሁ ትቀጣላችሁን?
عربی تفاسیر:
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
131. «አላህንም ፍሩ። ታዘዙኝም።
عربی تفاسیر:
وَٱتَّقُواْ ٱلَّذِيٓ أَمَدَّكُم بِمَا تَعۡلَمُونَ
132. «ያንንም በምታውቁት ጸጋ ያጣቀማችሁን ጌታን (አላህን) ፍሩ።
عربی تفاسیر:
أَمَدَّكُم بِأَنۡعَٰمٖ وَبَنِينَ
133. «በእንስሳዎችና በልጆችም ያጣቀማችሁ።
عربی تفاسیر:
وَجَنَّٰتٖ وَعُيُونٍ
134. «በአትክልቶችና በምንጮችም ያጣቀማችሁን ጌታን (አላህን) ፍሩ።
عربی تفاسیر:
إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ
135. «እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁና።»
عربی تفاسیر:
قَالُواْ سَوَآءٌ عَلَيۡنَآ أَوَعَظۡتَ أَمۡ لَمۡ تَكُن مِّنَ ٱلۡوَٰعِظِينَ
136. እነርሱም አሉ: «ብትገስጽም ወይም ከገሳጮች ባትሆንም በእኛ ላይ እኩል ነው።
عربی تفاسیر:
 
معانی کا ترجمہ سورت: شعراء
سورتوں کی لسٹ صفحہ نمبر
 
قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی - ترجمے کی لسٹ

محمد زین زہر الدین نے ترجمہ کیا۔ افریقہ اکیڈمی کی جانب سے شائع ہوا۔

بند کریں