قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - الترجمة الأمهرية - زين * - ترجمے کی لسٹ


معانی کا ترجمہ سورت: سورۂ یٰس   آیت:

ሱረቱ ያሲን

يسٓ
1. ያሲን::
عربی تفاسیر:
وَٱلۡقُرۡءَانِ ٱلۡحَكِيمِ
2-ጥበብ በተሞላበት ቁርኣን እምላለሁ::
عربی تفاسیر:
إِنَّكَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቹ መካከል አንዱ ነህ።
عربی تفاسیر:
عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
4. አንተ በእርግጥ በቀጥታው መንገድ ላይ ነህ ::
عربی تفاسیر:
تَنزِيلَ ٱلۡعَزِيزِ ٱلرَّحِيمِ
5.ቁርኣን አሸናፊውና አዛኙ ከሆነው አምላክ ከአላህ ተወረደ::
عربی تفاسیر:
لِتُنذِرَ قَوۡمٗا مَّآ أُنذِرَ ءَابَآؤُهُمۡ فَهُمۡ غَٰفِلُونَ
6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አባቶቻቸው ያልተስፈራሩትን ህዝቦች ልታስጠነቅቅበት ቁርኣን ተወረደ። እነርሱ ዘንጊዎች ናቸውና።
عربی تفاسیر:
لَقَدۡ حَقَّ ٱلۡقَوۡلُ عَلَىٰٓ أَكۡثَرِهِمۡ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
7. በአብዛኞቻቸቸው ላይ ቃሉ በእውነት ተረጋገጠ:: ስለዚህ እነርሱ አያምኑም::
عربی تفاسیر:
إِنَّا جَعَلۡنَا فِيٓ أَعۡنَٰقِهِمۡ أَغۡلَٰلٗا فَهِيَ إِلَى ٱلۡأَذۡقَانِ فَهُم مُّقۡمَحُونَ
8. እኛ በአንገቶቻቸው ላይ እንዛዝላዎችን አደረግን። (እንዛዝላይቱም) ወደ አገጮቻቸው ደራሽ ናት። እናም ከዚያም እነርሱ ራሶቻቸውን ያንጋጠጡ ናቸው።
عربی تفاسیر:
وَجَعَلۡنَا مِنۢ بَيۡنِ أَيۡدِيهِمۡ سَدّٗا وَمِنۡ خَلۡفِهِمۡ سَدّٗا فَأَغۡشَيۡنَٰهُمۡ فَهُمۡ لَا يُبۡصِرُونَ
9. ከበስተፊታቸዉም ግርዶን ከበስተኋላቸዉም ግርዶን አደረግንና ሸፈንናቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያዩም::
عربی تفاسیر:
وَسَوَآءٌ عَلَيۡهِمۡ ءَأَنذَرۡتَهُمۡ أَمۡ لَمۡ تُنذِرۡهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
10. ብታስጠነቅቃቸዉም ባታስጠነቅቃቸዉም ለእነርሱ ሁሉም እኩል ነው:: (ምንም ለውጥ አያመጣም) አያምኑምና::
عربی تفاسیر:
إِنَّمَا تُنذِرُ مَنِ ٱتَّبَعَ ٱلذِّكۡرَ وَخَشِيَ ٱلرَّحۡمَٰنَ بِٱلۡغَيۡبِۖ فَبَشِّرۡهُ بِمَغۡفِرَةٖ وَأَجۡرٖ كَرِيمٍ
11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምታስጠነቅቀው ግሳጼን የተከተለንና አር-ረህማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው:: እናም በምህረትና በመልካም ምንዳ አብስረው::
عربی تفاسیر:
إِنَّا نَحۡنُ نُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَنَكۡتُبُ مَا قَدَّمُواْ وَءَاثَٰرَهُمۡۚ وَكُلَّ شَيۡءٍ أَحۡصَيۡنَٰهُ فِيٓ إِمَامٖ مُّبِينٖ
12. እኛ ሙታንን በእርግጥ ህያው እናደርጋለን:: ያስቀደሙትንም ስራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን:: ሁሉን ነገርም ገላጭና መሪ በሆነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው::
عربی تفاسیر:
وَٱضۡرِبۡ لَهُم مَّثَلًا أَصۡحَٰبَ ٱلۡقَرۡيَةِ إِذۡ جَآءَهَا ٱلۡمُرۡسَلُونَ
13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱም የከተማይቱን (የአንጾኪያን) ሰዎች ምሳሌ መልዕክተኞች በመጧት ጊዜ የሆነውን ግለጽላቸው።
عربی تفاسیر:
إِذۡ أَرۡسَلۡنَآ إِلَيۡهِمُ ٱثۡنَيۡنِ فَكَذَّبُوهُمَا فَعَزَّزۡنَا بِثَالِثٖ فَقَالُوٓاْ إِنَّآ إِلَيۡكُم مُّرۡسَلُونَ
14. ወደ እነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክንና ባስተባበሉዋቸውም ጊዜ፤ በሶስተኛም ባበረታናቸውና «እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን» ባሏቸው ጊዜ የሆነውን ምሳሌ ግለጽላቸው።
عربی تفاسیر:
قَالُواْ مَآ أَنتُمۡ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا وَمَآ أَنزَلَ ٱلرَّحۡمَٰنُ مِن شَيۡءٍ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا تَكۡذِبُونَ
15. «እናንተ መሰላችን ሰዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም:: አር-ረህማንም ምንንም ነገር አላወረደም:: እናንተ የምትዋሹ እንጂ ሌላ አይደላችሁም» አሏቸው።
عربی تفاسیر:
قَالُواْ رَبُّنَا يَعۡلَمُ إِنَّآ إِلَيۡكُمۡ لَمُرۡسَلُونَ
16. መልዕክተኞቹም አሉ: «ጌታችን ያውቃል። እኛ ወደ እናንተ በእርግጥ መልክተኞች ነን።
عربی تفاسیر:
وَمَا عَلَيۡنَآ إِلَّا ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ
17. «በእኛ ላይም ግልጽ የሆነ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብንም።» አሉ።
عربی تفاسیر:
قَالُوٓاْ إِنَّا تَطَيَّرۡنَا بِكُمۡۖ لَئِن لَّمۡ تَنتَهُواْ لَنَرۡجُمَنَّكُمۡ وَلَيَمَسَّنَّكُم مِّنَّا عَذَابٌ أَلِيمٞ
18. ህዝቦቹም «እኛ በእናንተ ገደ ቢሶች ሆንን። ከዚህ ጥሪያችሁ ባትከለክሉም በእርግጥ እንወግራችኋለን:: ከእኛም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ያገኛችኋል» አሉ።
عربی تفاسیر:
قَالُواْ طَٰٓئِرُكُم مَّعَكُمۡ أَئِن ذُكِّرۡتُمۚ بَلۡ أَنتُمۡ قَوۡمٞ مُّسۡرِفُونَ
19. «ገደ ቢስነታችሁ ከናንተው ጋር ነው:: ብትገሰጹ (ትዝታላችሁን?) በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊ ህዝቦች ናችሁ» አሏቸው።
عربی تفاسیر:
وَجَآءَ مِنۡ أَقۡصَا ٱلۡمَدِينَةِ رَجُلٞ يَسۡعَىٰ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱتَّبِعُواْ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
20. ከከተማይቱም ሩቅ ዳርቻ የሚሮጥ ሰው መጣና (እንዲህ) አለ: «ወገኖቼ ሆይ! መልዕክተኞቹን ተከተሉ።
عربی تفاسیر:
ٱتَّبِعُواْ مَن لَّا يَسۡـَٔلُكُمۡ أَجۡرٗا وَهُم مُّهۡتَدُونَ
21. «እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመሩ ሲሆኑ ክፍያን የማይጠይቋችሁን ሰዎች ተከተሉ።
عربی تفاسیر:
وَمَالِيَ لَآ أَعۡبُدُ ٱلَّذِي فَطَرَنِي وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
22. «ያንንም የፈጠረኝንና ወደ እርሱም የምትመለሱበትን ጌታ የማልገዛበት ምን ምክንያት አለኝ?
عربی تفاسیر:
ءَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةً إِن يُرِدۡنِ ٱلرَّحۡمَٰنُ بِضُرّٖ لَّا تُغۡنِ عَنِّي شَفَٰعَتُهُمۡ شَيۡـٔٗا وَلَا يُنقِذُونِ
23. «ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልራህማን ሊጎዳኝ ቢፈልግ ምልጃቸው ከእኔ (ለመመለስ) ምንም አትጠቅመኝም አያድኑኝምም።
عربی تفاسیر:
إِنِّيٓ إِذٗا لَّفِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ
24. «እኔ ያን ጊዜ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነኝ።
عربی تفاسیر:
إِنِّيٓ ءَامَنتُ بِرَبِّكُمۡ فَٱسۡمَعُونِ
25. «እኔ በጌታችሁ አመንኩ። ስሙኝም።» አለ።
عربی تفاسیر:
قِيلَ ٱدۡخُلِ ٱلۡجَنَّةَۖ قَالَ يَٰلَيۡتَ قَوۡمِي يَعۡلَمُونَ
26. {1} «ገነትን ግባ» ተባለም። እርሱም አለ: «ወገኖቼ ቢያውቁ እመኛለሁ።
{1} ደብድበው ገደሉት ከሞተ በኋላ ጀነት ግባ ተባለ
عربی تفاسیر:
بِمَا غَفَرَ لِي رَبِّي وَجَعَلَنِي مِنَ ٱلۡمُكۡرَمِينَ
27. «ጌታዬ ለእኔ ምህረት ያደረገልኝና ከተከበሩትም ያደረገኝ መሆኑን።» (ቢያውቁ ተመኘሁ)
عربی تفاسیر:
۞ وَمَآ أَنزَلۡنَا عَلَىٰ قَوۡمِهِۦ مِنۢ بَعۡدِهِۦ مِن جُندٖ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا كُنَّا مُنزِلِينَ
28. ከእርሱም በኋላ በህዝቦቹ ላይ ልናጠፋቸው ሰራዊትን ከሰማይ አላወረድንም (በማንም) ላይ አውራጆችም አልነበርንም::
عربی تفاسیر:
إِن كَانَتۡ إِلَّا صَيۡحَةٗ وَٰحِدَةٗ فَإِذَا هُمۡ خَٰمِدُونَ
29. ቅጣታቸው አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አልነበረችም:: ወዲያውኑም እነርሱ ጠፊዎች ሆኑ::
عربی تفاسیر:
يَٰحَسۡرَةً عَلَى ٱلۡعِبَادِۚ مَا يَأۡتِيهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
30. በባሮች ላይ ዋ ቁጭት! ከመልዕክተኛ አንድም አልመጣላቸዉም በእርሱ ያፌዙበት ቢሆን እንጂ፤
عربی تفاسیر:
أَلَمۡ يَرَوۡاْ كَمۡ أَهۡلَكۡنَا قَبۡلَهُم مِّنَ ٱلۡقُرُونِ أَنَّهُمۡ إِلَيۡهِمۡ لَا يَرۡجِعُونَ
31. ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙዎችን ማጥፋታችንንና እነርሱ የማይመለሱ መሆናቸውን አላወቁምን?
عربی تفاسیر:
وَإِن كُلّٞ لَّمَّا جَمِيعٞ لَّدَيۡنَا مُحۡضَرُونَ
32. ሁሉም እኛ ዘንድ (የሚሰበሰቡ) የሚቀረቡ እንጂ ሌላ አይደሉም::
عربی تفاسیر:
وَءَايَةٞ لَّهُمُ ٱلۡأَرۡضُ ٱلۡمَيۡتَةُ أَحۡيَيۡنَٰهَا وَأَخۡرَجۡنَا مِنۡهَا حَبّٗا فَمِنۡهُ يَأۡكُلُونَ
33. የሞተችዉም ምድር ለእነርሱ ምልክት ናት:: ህያው አደረግናት:: ከእርሷ ፍሬን አወጣን፤ ከእሱም ይበላሉ::
عربی تفاسیر:
وَجَعَلۡنَا فِيهَا جَنَّٰتٖ مِّن نَّخِيلٖ وَأَعۡنَٰبٖ وَفَجَّرۡنَا فِيهَا مِنَ ٱلۡعُيُونِ
34. በእርሷ ውስጥ ከዘምባባዎችና ከወይኖች የሆነ አትክልቶችን አደረግን:: በእርሷም ውስጥ ምንጮችን አፈለቅን::
عربی تفاسیر:
لِيَأۡكُلُواْ مِن ثَمَرِهِۦ وَمَا عَمِلَتۡهُ أَيۡدِيهِمۡۚ أَفَلَا يَشۡكُرُونَ
35. ከፍሬዉና እጆቻቸው ከሰሩትም ይበሉ ዘንድ ይህን አደረግን:: አያመሰግኑምን?
عربی تفاسیر:
سُبۡحَٰنَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلۡأَزۡوَٰجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنۢبِتُ ٱلۡأَرۡضُ وَمِنۡ أَنفُسِهِمۡ وَمِمَّا لَا يَعۡلَمُونَ
36. ያ! ምድር ከምታበቅለው፤ ወንዴንና ሴቴን ከነፍሶቻቸዉም ከማያውቁትም ነገር (ዓይነቶችን) ሁሏንም የፈጠረ (አምላክ) ጥራት ይገባው::
عربی تفاسیر:
وَءَايَةٞ لَّهُمُ ٱلَّيۡلُ نَسۡلَخُ مِنۡهُ ٱلنَّهَارَ فَإِذَا هُم مُّظۡلِمُونَ
37. ሌሊቱም ለእነርሱ ምልክት ነው:: ከእርሱ ላይ ቀንን አንገፋለን:: ወዲያውኑም እነርሱ በጨለማ ውስጥ ይገባሉ::
عربی تفاسیر:
وَٱلشَّمۡسُ تَجۡرِي لِمُسۡتَقَرّٖ لَّهَاۚ ذَٰلِكَ تَقۡدِيرُ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡعَلِيمِ
38. ጸሐይም ለእርሷ ወደ ሆነው መርጊያ ትሮጣለች:: ይህ የአሸናፊውና የአዋቂው አምላክ የአላህ ውሳኔ ነው::
عربی تفاسیر:
وَٱلۡقَمَرَ قَدَّرۡنَٰهُ مَنَازِلَ حَتَّىٰ عَادَ كَٱلۡعُرۡجُونِ ٱلۡقَدِيمِ
39. ጨረቃንም የመስፈሪያዎች ባለቤት ሲሆን እንደ አሮጌ ዘንባባ ቀንዘል እስኪሆን ድረስ መሄዱን ለካነው::
عربی تفاسیر:
لَا ٱلشَّمۡسُ يَنۢبَغِي لَهَآ أَن تُدۡرِكَ ٱلۡقَمَرَ وَلَا ٱلَّيۡلُ سَابِقُ ٱلنَّهَارِۚ وَكُلّٞ فِي فَلَكٖ يَسۡبَحُونَ
40. ጸሐይ ጨረቃን ልትደርስበት አይገባትም:: ሌሊትም ቀንን ያለ ጊዜው ቀዳሚ አይሆንም:: ሁሉም በየመዞሪያቸው (በፈለክ) ውስጥ ይዋኛሉ::
عربی تفاسیر:
وَءَايَةٞ لَّهُمۡ أَنَّا حَمَلۡنَا ذُرِّيَّتَهُمۡ فِي ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ
41. እኛም የቀድሞ ትውልዳቸውን (አባቶቻቸውን) በተሞላች መርከብ ውስጥ የጫን መሆናችን ለእነርሱ ምልክት ነው::
عربی تفاسیر:
وَخَلَقۡنَا لَهُم مِّن مِّثۡلِهِۦ مَا يَرۡكَبُونَ
42. ከመሰሉም በእርሱ የሚሳፈሩበትን ለእነርሱ ፈጠርንላቸው::
عربی تفاسیر:
وَإِن نَّشَأۡ نُغۡرِقۡهُمۡ فَلَا صَرِيخَ لَهُمۡ وَلَا هُمۡ يُنقَذُونَ
43. ስንፈልግ እናሰምጣቸዋለን:: ለእነርሱም ነፃ የሚያደርጋቸው ረዳት የላቸዉም:: እንዲድኑ የሚደረጉም አይደሉም።
عربی تفاسیر:
إِلَّا رَحۡمَةٗ مِّنَّا وَمَتَٰعًا إِلَىٰ حِينٖ
44. እኛ ግን በችሮታችንና እስከ ጊዜ ሞታቸው ለማጣቀም አዳንናቸው::
عربی تفاسیر:
وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّقُواْ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيكُمۡ وَمَا خَلۡفَكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ
45. ለእነርሱም «በስተፊታችሁና በኋላችሁ ያለውን ነገር ተጠንቀቁ፤ ይታዘንላችኋልና» በተባለ ጊዜ ፊታቸውን ያዞራሉ።
عربی تفاسیر:
وَمَا تَأۡتِيهِم مِّنۡ ءَايَةٖ مِّنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِمۡ إِلَّا كَانُواْ عَنۡهَا مُعۡرِضِينَ
46. ከጌታቸውም ተዓምራት አንዲትም ተዓምር አትመጣላቸዉም ከእርሷ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጅ።
عربی تفاسیر:
وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ أَنفِقُواْ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ قَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَنُطۡعِمُ مَن لَّوۡ يَشَآءُ ٱللَّهُ أَطۡعَمَهُۥٓ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ
47. ለእነርሱም «አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ለግሱ» በተባሉ ጊዜ እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነዚያ በአላህ ላመኑት «አላህ ቢሻ ኖሮ የሚያበላውን እናበላለን? እናንተ በግልጽ ስህተት ውስጥ እንጂ በሌላ ላይ አይደላችሁም።» ይላሉ።
عربی تفاسیر:
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
48. «እውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ።
عربی تفاسیر:
مَا يَنظُرُونَ إِلَّا صَيۡحَةٗ وَٰحِدَةٗ تَأۡخُذُهُمۡ وَهُمۡ يَخِصِّمُونَ
49. እነርሱ የሚከራከሩ ሲሆኑ በድንገት የምትይዛቸው የሆነችን አንዲትን ጩኸት እንጂ ሌላን አይጠባበቁም::
عربی تفاسیر:
فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ تَوۡصِيَةٗ وَلَآ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِمۡ يَرۡجِعُونَ
50. ያን ጊዜ መናዘዝን እንኳን አይችሉም:: ወደ ቤተሰቦቻቸዉም አይመለሱም::
عربی تفاسیر:
وَنُفِخَ فِي ٱلصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ ٱلۡأَجۡدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ يَنسِلُونَ
51. በቀንዱም ይነፋል:: ወዲያውኑም እነርሱ ከየመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ::
عربی تفاسیر:
قَالُواْ يَٰوَيۡلَنَا مَنۢ بَعَثَنَا مِن مَّرۡقَدِنَاۜۗ هَٰذَا مَا وَعَدَ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَصَدَقَ ٱلۡمُرۡسَلُونَ
52. «ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን መልዕክተኞቹም እውነቱን የነገሩን ነው።» ይላሉ።
عربی تفاسیر:
إِن كَانَتۡ إِلَّا صَيۡحَةٗ وَٰحِدَةٗ فَإِذَا هُمۡ جَمِيعٞ لَّدَيۡنَا مُحۡضَرُونَ
53. እርሷ አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አይደለችም:: ወዲያውኑም እነርሱ እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀርቡ ናቸው::
عربی تفاسیر:
فَٱلۡيَوۡمَ لَا تُظۡلَمُ نَفۡسٞ شَيۡـٔٗا وَلَا تُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
54. ዛሬም ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም:: ትሰሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም (ይባላሉ።)
عربی تفاسیر:
إِنَّ أَصۡحَٰبَ ٱلۡجَنَّةِ ٱلۡيَوۡمَ فِي شُغُلٖ فَٰكِهُونَ
55. የገነት ሰዎች ዛሬ በእርግጥ በስራዎች ውስጥ ተደሳቾች ናቸው::
عربی تفاسیر:
هُمۡ وَأَزۡوَٰجُهُمۡ فِي ظِلَٰلٍ عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ مُتَّكِـُٔونَ
56. እነርሱም ሆኑ ሚስቶቻቸው በጥላዎች ውስጥ ናቸው:: ባለ አጎበር አልጋዎች ላይም ተደጋፊዎች ናቸው::
عربی تفاسیر:
لَهُمۡ فِيهَا فَٰكِهَةٞ وَلَهُم مَّا يَدَّعُونَ
57. በውስጧ ለእነርሱ ፍራፍሬዎች አሏቸው:: ለእነርሱም የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው::
عربی تفاسیر:
سَلَٰمٞ قَوۡلٗا مِّن رَّبّٖ رَّحِيمٖ
58. ለእነርሱም አዛኝ ከሆነው ጌታ በቃል ሰላምታ አለላቸው።
عربی تفاسیر:
وَٱمۡتَٰزُواْ ٱلۡيَوۡمَ أَيُّهَا ٱلۡمُجۡرِمُونَ
59. (አላህም ይላል): «እናንተ አመጸኞች ሆይ! ዛሬ ከትክክለኛ አማኞች ተለዩ።
عربی تفاسیر:
۞ أَلَمۡ أَعۡهَدۡ إِلَيۡكُمۡ يَٰبَنِيٓ ءَادَمَ أَن لَّا تَعۡبُدُواْ ٱلشَّيۡطَٰنَۖ إِنَّهُۥ لَكُمۡ عَدُوّٞ مُّبِينٞ
60. «የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አትገዙ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደ እናንተ አላዘዝኩምን?
عربی تفاسیر:
وَأَنِ ٱعۡبُدُونِيۚ هَٰذَا صِرَٰطٞ مُّسۡتَقِيمٞ
61. «ተገዙኝም ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው በማለትም::
عربی تفاسیر:
وَلَقَدۡ أَضَلَّ مِنكُمۡ جِبِلّٗا كَثِيرًاۖ أَفَلَمۡ تَكُونُواْ تَعۡقِلُونَ
62. «ከናንተም ብዙን ፍጡር በእርግጥ አሳስቷል:: የምታውቁም አልነበራችሁምን?
عربی تفاسیر:
هَٰذِهِۦ جَهَنَّمُ ٱلَّتِي كُنتُمۡ تُوعَدُونَ
63. «ይህቺ ያቺ ትቀጠሯት የነበረችው ገሀነም ናት።
عربی تفاسیر:
ٱصۡلَوۡهَا ٱلۡيَوۡمَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡفُرُونَ
64. «ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬዉኑ ግቧት።» (ይባላሉ።)
عربی تفاسیر:
ٱلۡيَوۡمَ نَخۡتِمُ عَلَىٰٓ أَفۡوَٰهِهِمۡ وَتُكَلِّمُنَآ أَيۡدِيهِمۡ وَتَشۡهَدُ أَرۡجُلُهُم بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ
65. ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል:: እግሮቻቸዉም ይሰሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ::
عربی تفاسیر:
وَلَوۡ نَشَآءُ لَطَمَسۡنَا عَلَىٰٓ أَعۡيُنِهِمۡ فَٱسۡتَبَقُواْ ٱلصِّرَٰطَ فَأَنَّىٰ يُبۡصِرُونَ
66. ብንፈልግ ኖሮ በዓይኖቻቸው ላይ በአበስን ነበር:: መንገድንም እንደ ልማዳቸው በተሸቀዳደሙ ነበር:: እንዴትስ ያያሉ?
عربی تفاسیر:
وَلَوۡ نَشَآءُ لَمَسَخۡنَٰهُمۡ عَلَىٰ مَكَانَتِهِمۡ فَمَا ٱسۡتَطَٰعُواْ مُضِيّٗا وَلَا يَرۡجِعُونَ
67. ብንፈልግ ኖሮ በስፍራቸው ላይ እንዳሉ ወደ ሌላ ፍጥረት በለወጥናቸው ነበር:: ከዚያም መሄድንም ሆነ መመለስን ባልቻሉም ነበር::
عربی تفاسیر:
وَمَن نُّعَمِّرۡهُ نُنَكِّسۡهُ فِي ٱلۡخَلۡقِۚ أَفَلَا يَعۡقِلُونَ
68. እድሜውንም የምናረዝመውን በፍጥረቱ ወደ ደካማነት እንመልሰዋለን:: አያውቁምን?
عربی تفاسیر:
وَمَا عَلَّمۡنَٰهُ ٱلشِّعۡرَ وَمَا يَنۢبَغِي لَهُۥٓۚ إِنۡ هُوَ إِلَّا ذِكۡرٞ وَقُرۡءَانٞ مُّبِينٞ
69. (ሙሐመድን) ቅኔንም አላስተማርነዉም:: ለእርሱም አይገባዉም:: እርሱ (መጽሐፉ) መገሰጫና ገላጭ ቁርኣን አንጅ (ቅኔ አይደለም)::
عربی تفاسیر:
لِّيُنذِرَ مَن كَانَ حَيّٗا وَيَحِقَّ ٱلۡقَوۡلُ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ
70. ግሳጼነቱም ልቡ ህያው የሆነን ሰው ሊያስፈራራበትና ቃሉም በከሓዲያን ላይ ይፈጸም ዘንድ ነው::
عربی تفاسیر:
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّا خَلَقۡنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتۡ أَيۡدِينَآ أَنۡعَٰمٗا فَهُمۡ لَهَا مَٰلِكُونَ
71. እኛ እጆቻችን ከሰሩት ለእነርሱ እንሰሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው::
عربی تفاسیر:
وَذَلَّلۡنَٰهَا لَهُمۡ فَمِنۡهَا رَكُوبُهُمۡ وَمِنۡهَا يَأۡكُلُونَ
72. ለእነርሱም ገራናት:: ስለዚህ ከእርሷ ውስጥ የሚጋልቡት አለ:: ከእርሷም ይመገባሉ::
عربی تفاسیر:
وَلَهُمۡ فِيهَا مَنَٰفِعُ وَمَشَارِبُۚ أَفَلَا يَشۡكُرُونَ
73. ለእነርሱም በእርሷ ውስጥ ሌሎች ጥቅሞችና መጠጦችም አሏቸው። ታዲያ አያመሰግኑምን?
عربی تفاسیر:
وَٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةٗ لَّعَلَّهُمۡ يُنصَرُونَ
74. መረዳትንም በመከጀል ከአላህ ሌላ አመለኩ።
عربی تفاسیر:
لَا يَسۡتَطِيعُونَ نَصۡرَهُمۡ وَهُمۡ لَهُمۡ جُندٞ مُّحۡضَرُونَ
75. ሊረዷቸውም አይችሉም። እነርሱም ለእርሳቸው ወደ እሳት የተቀረቡ ሰራዊት ናቸው::
عربی تفاسیر:
فَلَا يَحۡزُنكَ قَوۡلُهُمۡۘ إِنَّا نَعۡلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعۡلِنُونَ
76. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ንግግራቸዉም አያሳዝንህ:: እኛ የሚደብቁትንም የሚገልፁትንም እናውቃለንና::
عربی تفاسیر:
أَوَلَمۡ يَرَ ٱلۡإِنسَٰنُ أَنَّا خَلَقۡنَٰهُ مِن نُّطۡفَةٖ فَإِذَا هُوَ خَصِيمٞ مُّبِينٞ
77. ሰው እኛ ከፍትወት ጠብታ የፈጠርነው መሆናችንን አላወቀምን? ወዲያዉም እርሱ ትንሳኤን በመካድ ግልጽ ተከራካሪ ይሆናልን?
عربی تفاسیر:
وَضَرَبَ لَنَا مَثَلٗا وَنَسِيَ خَلۡقَهُۥۖ قَالَ مَن يُحۡيِ ٱلۡعِظَٰمَ وَهِيَ رَمِيمٞ
78. ለእኛም ምሳሌን አደረገልን:: መፈጠሩንም ረሳ:: «አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲሆኑ ህያው የሚያደርጋቸው ማነው?» አለ::
عربی تفاسیر:
قُلۡ يُحۡيِيهَا ٱلَّذِيٓ أَنشَأَهَآ أَوَّلَ مَرَّةٖۖ وَهُوَ بِكُلِّ خَلۡقٍ عَلِيمٌ
79. «ያ! በመጀመሪያ ጊዜ (ከኢምንት) ያስገኛት ጌታ እንደገና ህያው ያደረጋታል:: እርሱም በፍጡሩ ሁሉ ሁኔታ አዋቂ ነው።» በለው።
عربی تفاسیر:
ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلشَّجَرِ ٱلۡأَخۡضَرِ نَارٗا فَإِذَآ أَنتُم مِّنۡهُ تُوقِدُونَ
80. ያ! ለእናንተ ከእርጥብ ዛፍ እሳትን የፈጠረላችሁ ነው:: ወዲያውኑም እናንተ ከእርሱ ታቀጣጥላላችሁ::
عربی تفاسیر:
أَوَلَيۡسَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يَخۡلُقَ مِثۡلَهُمۚ بَلَىٰ وَهُوَ ٱلۡخَلَّٰقُ ٱلۡعَلِيمُ
81. ያ! ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ አይደለምን? እንዴታ ቻይ ነው እንጂ:: እርሱም በብዙ ፈጣሪውና እጅግ አዋቂው ነው።
عربی تفاسیر:
إِنَّمَآ أَمۡرُهُۥٓ إِذَآ أَرَادَ شَيۡـًٔا أَن يَقُولَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ
82. ነገሩ አንድን ነገር በሻ ጊዜ ሁን ማለት ብቻ ነው:: ከዚያ ወዲያው ይሆናልም::
عربی تفاسیر:
فَسُبۡحَٰنَ ٱلَّذِي بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيۡءٖ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
83. እናም ያ የነገሩ ሁሉ ስልጣን በእጁ የሆነው ጌታ ጥራት ይገባው:: ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::
عربی تفاسیر:
 
معانی کا ترجمہ سورت: سورۂ یٰس
سورتوں کی لسٹ صفحہ نمبر
 
قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - الترجمة الأمهرية - زين - ترجمے کی لسٹ

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

بند کریں