Check out the new design

قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی * - ترجمے کی لسٹ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

معانی کا ترجمہ سورت: مائدہ   آیت:
وَإِذَا نَادَيۡتُمۡ إِلَى ٱلصَّلَوٰةِ ٱتَّخَذُوهَا هُزُوٗا وَلَعِبٗاۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَعۡقِلُونَ
58. (ሙስሊሞች ሆይ!) ወደ ሶላት በጠራችሁም ጊዜ ጥሪዋን መሳለቂያና መጫዎቻ ያደርጓታል። ይህ እነርሱ የማያስተውሉ ህዝቦች በመሆናቸው ነው።
عربی تفاسیر:
قُلۡ يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ هَلۡ تَنقِمُونَ مِنَّآ إِلَّآ أَنۡ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيۡنَا وَمَآ أُنزِلَ مِن قَبۡلُ وَأَنَّ أَكۡثَرَكُمۡ فَٰسِقُونَ
59. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በአላህና ወደኛ በተወረደው በፊትም በተወረደው ለማመናችን አብዛኞቻችሁም አመጸኞች ለመኾናችሁ እንጅ (ሌላን ነገር) ከኛ ትጠላላችሁን?» በላቸው፡፡
عربی تفاسیر:
قُلۡ هَلۡ أُنَبِّئُكُم بِشَرّٖ مِّن ذَٰلِكَ مَثُوبَةً عِندَ ٱللَّهِۚ مَن لَّعَنَهُ ٱللَّهُ وَغَضِبَ عَلَيۡهِ وَجَعَلَ مِنۡهُمُ ٱلۡقِرَدَةَ وَٱلۡخَنَازِيرَ وَعَبَدَ ٱلطَّٰغُوتَۚ أُوْلَٰٓئِكَ شَرّٞ مَّكَانٗا وَأَضَلُّ عَن سَوَآءِ ٱلسَّبِيلِ
60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ዘንድ ቅጣቱ ከዚህ ሁሉ የከፋን ነገር ልንገራችሁን?» በላቸው:: እርሱም «አላህ የረገማቸውና በእነርሱም ላይ የተቆጣባቸው ናቸው:: ከመካከላቸዉም ዝንጀሮዎችና ከርከሮዎች ያደረጋቸው ጣዖትንም የተገዙ ሰዎች ሃይማኖት ነው:: እነዚያ በጣም በከፋ ስፍራ ናቸው:: ከቀጥተኛዉም መንገድ በጣም የተሳሳቱ ናቸው።»
عربی تفاسیر:
وَإِذَا جَآءُوكُمۡ قَالُوٓاْ ءَامَنَّا وَقَد دَّخَلُواْ بِٱلۡكُفۡرِ وَهُمۡ قَدۡ خَرَجُواْ بِهِۦۚ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا كَانُواْ يَكۡتُمُونَ
61. ( አማኞች ሆይ!) ወደ እናንተ በመጡ ጊዜ ከክህደት ጋር ሁነው የገቡ ከእርሱ (ከክህደቱ) ጋር ሁነውም የወጡ ሲሆኑ ልክ እንደናንተ «አምነናል» ይላሉ:: አላህ ያንን ይደብቁት የነበረውን ነገር ሁሉ ጠንቅቆ አዋቂ ነው::
عربی تفاسیر:
وَتَرَىٰ كَثِيرٗا مِّنۡهُمۡ يُسَٰرِعُونَ فِي ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡعُدۡوَٰنِ وَأَكۡلِهِمُ ٱلسُّحۡتَۚ لَبِئۡسَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
62. (መልዕክተኛችን መሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ ብዙዎቹን በኃጢአትና በበደል እርምንም የሆነ ለመብላት ሲጣደፉ ታያቸዋለህ:: ይሰሩት የነበረው በጣም ከፋ!
عربی تفاسیر:
لَوۡلَا يَنۡهَىٰهُمُ ٱلرَّبَّٰنِيُّونَ وَٱلۡأَحۡبَارُ عَن قَوۡلِهِمُ ٱلۡإِثۡمَ وَأَكۡلِهِمُ ٱلسُّحۡتَۚ لَبِئۡسَ مَا كَانُواْ يَصۡنَعُونَ
63. ቀሳውስቱና ሊቃውንቱ ከኃጢአት ንግግራቸውና እርምን ከመብላታቸው አይከለክሏቸዉም ኖሯልን? ይሰሩት የነበረው በጣም ከፋ!
عربی تفاسیر:
وَقَالَتِ ٱلۡيَهُودُ يَدُ ٱللَّهِ مَغۡلُولَةٌۚ غُلَّتۡ أَيۡدِيهِمۡ وَلُعِنُواْ بِمَا قَالُواْۘ بَلۡ يَدَاهُ مَبۡسُوطَتَانِ يُنفِقُ كَيۡفَ يَشَآءُۚ وَلَيَزِيدَنَّ كَثِيرٗا مِّنۡهُم مَّآ أُنزِلَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَ طُغۡيَٰنٗا وَكُفۡرٗاۚ وَأَلۡقَيۡنَا بَيۡنَهُمُ ٱلۡعَدَٰوَةَ وَٱلۡبَغۡضَآءَ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ كُلَّمَآ أَوۡقَدُواْ نَارٗا لِّلۡحَرۡبِ أَطۡفَأَهَا ٱللَّهُۚ وَيَسۡعَوۡنَ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَسَادٗاۚ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُفۡسِدِينَ
64. አይሁድ «የአላህ እጅ የታሰረ ነው።» አሉ:: እጆቻቸው ይታሰሩ:: ባሉትም ነገር ይረገሙ። ይልቁንም የአላህ ሁለቱም እጆቹ የተዘረጉ ናቸው:: እንደፈለገ ይለግሳል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው ቁርኣን ከእነርሱ መካከል ለብዙዎቹ ትዕቢትንና ክህደትን በእርግጥ ይጨምርባቸዋል:: በአይሁድ መካከል ጠብንና ጥላቻን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ አደረግን:: ለጦር እሳትን ባቀጣጠሉ ቁጥር አላህ ያጠፋባቸዋል:: በምድር ውስጥ ለማበላሸት ይሮጣሉ:: አላህም አበላሾችን ሁሉ አይወድም።
عربی تفاسیر:
 
معانی کا ترجمہ سورت: مائدہ
سورتوں کی لسٹ صفحہ نمبر
 
قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی - ترجمے کی لسٹ

محمد زین زہر الدین نے ترجمہ کیا۔ افریقہ اکیڈمی کی جانب سے شائع ہوا۔

بند کریں