Check out the new design

Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Муҳаммад Содиқ * - Таржималар мундарижаси

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Маънолар таржимаси Сура: Ҳадид   Оят:
هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ يَعۡلَمُ مَا يَلِجُ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا يَخۡرُجُ مِنۡهَا وَمَا يَنزِلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا يَعۡرُجُ فِيهَاۖ وَهُوَ مَعَكُمۡ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ
እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ፤ ከዚያም በዙፋኑ ላይ (ለሱ ክብር በሚስማማ መልኩ)የተደላደለ ነው፡፡ በምድር ውስጥ የሚገባውን፣ ከእርሷም የሚወጣውን፣ ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ያውቃል፡፡ እርሱም የትም ብትኾኑ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ @Мусаҳҳиҳ
እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ፤ ከዚያም በዙፋኑ ላይ (ስልጣኑ) የተደላደለ ነው፡፡ በምድር ውስጥ የሚገባውን፣ ከእርሷም የሚወጣውን፣ ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ያውቃል፡፡ እርሱም የትም ብትኾኑ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡
Арабча тафсирлар:
لَّهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ
የሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ነገሮችም (ሁሉ) ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ፡፡
Арабча тафсирлар:
يُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِۚ وَهُوَ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፡፡ ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል፡፡ እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን ዐዋቂ ነወ፡፡
Арабча тафсирлар:
ءَامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَأَنفِقُواْ مِمَّا جَعَلَكُم مُّسۡتَخۡلَفِينَ فِيهِۖ فَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنكُمۡ وَأَنفَقُواْ لَهُمۡ أَجۡرٞ كَبِيرٞ
በአላህና በመልክተኛው እመኑ፡፡ (አላህ) በእርሱ ተተኪዎች ባደረጋችሁም ገንዘብ ለግሱ፡፡ እነዚያም ከእናንተ ውስጥ ያመኑትና የለገሱት ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ አልላቸው፡፡
Арабча тафсирлар:
وَمَا لَكُمۡ لَا تُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلرَّسُولُ يَدۡعُوكُمۡ لِتُؤۡمِنُواْ بِرَبِّكُمۡ وَقَدۡ أَخَذَ مِيثَٰقَكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ
መልክተኛው በጌታችሁ እንድታምኑ የሚጠራችሁ ሲኾን (ጌታችሁ) ኪዳናችሁንም የያዛችሁ ስሆን በአላህ የማታምኑት ለናንተ ምን አላችሁ? የምታምኑ ብትሆኑ (ወደ እምነት ቸኩሉ)።
Арабча тафсирлар:
هُوَ ٱلَّذِي يُنَزِّلُ عَلَىٰ عَبۡدِهِۦٓ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖ لِّيُخۡرِجَكُم مِّنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ بِكُمۡ لَرَءُوفٞ رَّحِيمٞ
እርሱ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ሊያወጣችሁ ያ ግልጾች የኾኑን አንቀጾች በበሪያው ላይ የሚያወርድ ነው፡፡ አላህም ለእናንተ በእርግጥ ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡
Арабча тафсирлар:
وَمَا لَكُمۡ أَلَّا تُنفِقُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلِلَّهِ مِيرَٰثُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ لَا يَسۡتَوِي مِنكُم مَّنۡ أَنفَقَ مِن قَبۡلِ ٱلۡفَتۡحِ وَقَٰتَلَۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَعۡظَمُ دَرَجَةٗ مِّنَ ٱلَّذِينَ أَنفَقُواْ مِنۢ بَعۡدُ وَقَٰتَلُواْۚ وَكُلّٗا وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ
የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ሲኾን በአላህ መንገድ የማትለግሱትም ለእናንተ ምን አልላችሁ? ከእናንተ ውስጥ (መካን) ከመክፈት በፊት የለገሰና የተጋደለ ሰው (ከተከፈተች በኋላ ከለገሰና ከተጋደለ ጋር) አይስተካከልም፡፡ ከእነዚያ በኋላ ከለገሱትና ከተጋደሉት እነዚህ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው፡፡ ሁሉንም አላህ መልካሚቱን ተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡
Арабча тафсирлар:
مَّن ذَا ٱلَّذِي يُقۡرِضُ ٱللَّهَ قَرۡضًا حَسَنٗا فَيُضَٰعِفَهُۥ لَهُۥ وَلَهُۥٓ أَجۡرٞ كَرِيمٞ
ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድር ለእርሱም (አላህ) የሚያነባብርለት ሰው ማነው? ለእርሱም መልካም ምንዳ አልለው፡፡
Арабча тафсирлар:
 
Маънолар таржимаси Сура: Ҳадид
Суралар мундарижаси Бет рақами
 
Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Муҳаммад Содиқ - Таржималар мундарижаси

Шайх Муҳаммад Содиқ ва Муҳаммад Соний Ҳабиб томонидан таржима қилинган. Руод таржима маркази назорати остида ривожлантирилган, асл таржимани кўриб чиқиш, баҳолаш ва доимий ривожлантириш мақсадида мавжуд.

Ёпиш