Check out the new design

Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси * - Таржималар мундарижаси


Маънолар таржимаси Сура: Юнус   Оят:

ዩኑስ

الٓرۚ تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡحَكِيمِ
1. አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ እነዚህ ጥበብ ከተሞላው መፅሀፍ አንቀፆች ናቸው።
Арабча тафсирлар:
أَكَانَ لِلنَّاسِ عَجَبًا أَنۡ أَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ رَجُلٖ مِّنۡهُمۡ أَنۡ أَنذِرِ ٱلنَّاسَ وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَنَّ لَهُمۡ قَدَمَ صِدۡقٍ عِندَ رَبِّهِمۡۗ قَالَ ٱلۡكَٰفِرُونَ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٞ مُّبِينٌ
2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎችን (ከሓዲያንን) አስፈራራ፤ እነዚያን ያመኑትን ደግሞ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መሆኑን አብስር» በማለት ከእነርሱ መካከል ወደ ሆነ አንድ ሰው ራዕይን ማውረዳችን ለሰዎች ድንቅ ሆነባቸውን? ከሓዲያን «ይህ (ሰው) ግልጽ ድግምተኛ ነው።» አሉ።
Арабча тафсирлар:
إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ يُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَۖ مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ إِذۡنِهِۦۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡ فَٱعۡبُدُوهُۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
3. ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ ብቻ የፈጠራቸው አላህ ነው:: ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲሆን (ለሱ ክብር በምስማማ መልኩ) በዐርሹ ላይ ተደላደለ፡፡ ከእርሱ በጎ ፈቃድ በኋላ ቢሆን እንጂ አንድም አማላጅ የለም:: እነሆ ይህ አላህ ጌታችሁ ነው:: እናም በትክክል ተገዙት:: አትገሰጹምን?
Арабча тафсирлар:
إِلَيۡهِ مَرۡجِعُكُمۡ جَمِيعٗاۖ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقًّاۚ إِنَّهُۥ يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ لِيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ بِٱلۡقِسۡطِۚ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَهُمۡ شَرَابٞ مِّنۡ حَمِيمٖ وَعَذَابٌ أَلِيمُۢ بِمَا كَانُواْ يَكۡفُرُونَ
4. (ሰዎች ሆይ!) የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ እርሱ ብቻ ነው:: ይህም የተረጋገጠ የአላህ ቃል ኪዳን ነው:: እርሱ መፍጠርን ይጀምራል:: ከዚያም እነዚያ ያመኑትንና መልካም የሠሩትን ሰዎች በትክክል ይመነዳ ዘንድ ፍጡራንን ከሞት በኋላ ህያው ያደርጋል:: እነዚያ የካዱት ክፍሎች ግን በክህደታቸው ምክንያት የፈላ ውሃ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
Арабча тафсирлар:
هُوَ ٱلَّذِي جَعَلَ ٱلشَّمۡسَ ضِيَآءٗ وَٱلۡقَمَرَ نُورٗا وَقَدَّرَهُۥ مَنَازِلَ لِتَعۡلَمُواْ عَدَدَ ٱلسِّنِينَ وَٱلۡحِسَابَۚ مَا خَلَقَ ٱللَّهُ ذَٰلِكَ إِلَّا بِٱلۡحَقِّۚ يُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ
5. እርሱ ያ ጸሐይን አንጸባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ፤ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለጨረቃ የተለያዩ መስፈሪያ እርከኖችን የወሰነ ነው:: አላህ ይህንን በእውነት እንጂ በከንቱ አልፈጠረዉም:: ለሚያውቁ ሕዝቦችም አናቅጽን ያብራራል::
Арабча тафсирлар:
إِنَّ فِي ٱخۡتِلَٰفِ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ وَمَا خَلَقَ ٱللَّهُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَتَّقُونَ
6. ሌሊትና ቀን በመተካካታቸው አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ በፈጠረው ሁሉ ለሚጠነቀቁ ሕዝቦች ታላላቅ ተአምራት አሉ::
Арабча тафсирлар:
 
Маънолар таржимаси Сура: Юнус
Суралар мундарижаси Бет рақами
 
Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси - Таржималар мундарижаси

Таржима қилган Муҳаммад Заин Заҳр ад-Дин. Африка академияси томонидан нашр қилинган.

Ёпиш