Check out the new design

Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси * - Таржималар мундарижаси


Маънолар таржимаси Сура: Раъд   Оят:

አር-ረዕድ

الٓمٓرۚ تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِۗ وَٱلَّذِيٓ أُنزِلَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَ ٱلۡحَقُّ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يُؤۡمِنُونَ
1. አሊፍ ፤ላም ፤ሚይም፤ ራ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ አናቅጽ ከመጽሐፉ አናቅጽ ናቸው:: ያም ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው እውነት ነው:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያምኑም::
Арабча тафсирлар:
ٱللَّهُ ٱلَّذِي رَفَعَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ بِغَيۡرِ عَمَدٖ تَرَوۡنَهَاۖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ وَسَخَّرَ ٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ كُلّٞ يَجۡرِي لِأَجَلٖ مُّسَمّٗىۚ يُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَ يُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ لَعَلَّكُم بِلِقَآءِ رَبِّكُمۡ تُوقِنُونَ
2. አላህ ያ ሰማያትን የምታይዋት ቋሚዎች ሳይኖራት በችሎታው ከፍ ያረጋት፤ ከዚያ በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ፤ ጸሐይንና ጨረቃንም የገራ ነው:: ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ:: ነገሩን ሁሉ ያስተናብራል:: ከጌታችሁ ጋር መገናኘትን ታረጋግጡ ዘንድ ተዓምራትን ይዘረዝራል::
Арабча тафсирлар:
وَهُوَ ٱلَّذِي مَدَّ ٱلۡأَرۡضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِيَ وَأَنۡهَٰرٗاۖ وَمِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ جَعَلَ فِيهَا زَوۡجَيۡنِ ٱثۡنَيۡنِۖ يُغۡشِي ٱلَّيۡلَ ٱلنَّهَارَۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ
3. እርሱ (አላህ)ያ ምድርን የዘረጋ፤ በእርሷም ውስጥ ተራራዎችንና ወንዞችን ያደረገ:: በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ዓይነቶችን ያደረገ ነው:: ሌሊትን በቀን ይሸፍናል:: በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ ብዙ ምልክቶች አሉ::
Арабча тафсирлар:
وَفِي ٱلۡأَرۡضِ قِطَعٞ مُّتَجَٰوِرَٰتٞ وَجَنَّٰتٞ مِّنۡ أَعۡنَٰبٖ وَزَرۡعٞ وَنَخِيلٞ صِنۡوَانٞ وَغَيۡرُ صِنۡوَانٖ يُسۡقَىٰ بِمَآءٖ وَٰحِدٖ وَنُفَضِّلُ بَعۡضَهَا عَلَىٰ بَعۡضٖ فِي ٱلۡأُكُلِۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَعۡقِلُونَ
4. በምድርም ውስጥ የተጎራበቱ ቁርጥራጮች አሉ:: የወይኖች አትክልቶችም፤ አዝርዕቶችም መንታዎችና መንታዎች ያልሆኑ ዘንባባዎችም አሉ:: በአንድ ውሃ ይጠጣሉ:: በጣዕም ግን ይለያያሉ ከፊልዋንም በከፊሉ ላይ በሚበላው ሰብል እናበልጣለን:: በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ ብዙ ተአምራት አለበት::
Арабча тафсирлар:
۞ وَإِن تَعۡجَبۡ فَعَجَبٞ قَوۡلُهُمۡ أَءِذَا كُنَّا تُرَٰبًا أَءِنَّا لَفِي خَلۡقٖ جَدِيدٍۗ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِرَبِّهِمۡۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ ٱلۡأَغۡلَٰلُ فِيٓ أَعۡنَاقِهِمۡۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብትደነቅም አፈር በሆንን ጊዜ እኛ አዲስ ፍጥረት እንሆናለን? ማለታቸው በጣም የሚደንቅ ነው:: እነዚህ እነዚያ ሰዎች ማለት እነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች ናቸው:: እነዚህም እንዛዝላዎች በአንገቶቻቸው ላይ ያሉባቸው ናቸው:: እነዚህም የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::
Арабча тафсирлар:
 
Маънолар таржимаси Сура: Раъд
Суралар мундарижаси Бет рақами
 
Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси - Таржималар мундарижаси

Таржима қилган Муҳаммад Заин Заҳр ад-Дин. Африка академияси томонидан нашр қилинган.

Ёпиш