Check out the new design

Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси * - Таржималар мундарижаси


Маънолар таржимаси Сура: Иброҳим   Оят:
وَءَاتَىٰكُم مِّن كُلِّ مَا سَأَلۡتُمُوهُۚ وَإِن تَعُدُّواْ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ لَا تُحۡصُوهَآۗ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَظَلُومٞ كَفَّارٞ
34. ከለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው:: የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ እንኳ አትዘልቁትም:: ሰው በጣም በደለኛና ከሓዲ ነው::
Арабча тафсирлар:
وَإِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِيمُ رَبِّ ٱجۡعَلۡ هَٰذَا ٱلۡبَلَدَ ءَامِنٗا وَٱجۡنُبۡنِي وَبَنِيَّ أَن نَّعۡبُدَ ٱلۡأَصۡنَامَ
35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም ባለ ጊዜ አስታውስ: «ጌታዬ ሆይ! ይህንን ሀገር መካን ጸጥተኛ አድርገው:: እኔንና ልጆቼንም ጣኦታትን ከመገዛት አርቀን።
Арабча тафсирлар:
رَبِّ إِنَّهُنَّ أَضۡلَلۡنَ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلنَّاسِۖ فَمَن تَبِعَنِي فَإِنَّهُۥ مِنِّيۖ وَمَنۡ عَصَانِي فَإِنَّكَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
36. «ጌታዬ ሆይ! እነርሱ (ጣኦታቱ) ከሰዎች ብዙዎችን አሳስተዋልና:: የተከተለኝም ሰው እርሱ ከእኔ ነው:: ትዕዛዜን የጣሰ ሰው ግን አንተ መሓሪና አዛኝ ነህ።
Арабча тафсирлар:
رَّبَّنَآ إِنِّيٓ أَسۡكَنتُ مِن ذُرِّيَّتِي بِوَادٍ غَيۡرِ ذِي زَرۡعٍ عِندَ بَيۡتِكَ ٱلۡمُحَرَّمِ رَبَّنَا لِيُقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ فَٱجۡعَلۡ أَفۡـِٔدَةٗ مِّنَ ٱلنَّاسِ تَهۡوِيٓ إِلَيۡهِمۡ وَٱرۡزُقۡهُم مِّنَ ٱلثَّمَرَٰتِ لَعَلَّهُمۡ يَشۡكُرُونَ
37. «ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤትህ በካዕባ አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ:: ጌታችን ሆይ! ሶላትን ደንቡን ጠብቀው ይሰግዱ ዘንድ አስቀመጥኳቸው:: ከሰዎችም ልቦችን ወደ እነርሱ የሚናፍቁ አድርግ:: ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው::
Арабча тафсирлар:
رَبَّنَآ إِنَّكَ تَعۡلَمُ مَا نُخۡفِي وَمَا نُعۡلِنُۗ وَمَا يَخۡفَىٰ عَلَى ٱللَّهِ مِن شَيۡءٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا فِي ٱلسَّمَآءِ
38. «ጌታችን ሆይ! አንተ የምንደብቀውንም የምንገልጸውንም ሁሉ በእርግጥ ታውቃለህ:: በአላህ ላይ በምድርም በሰማይም ምንም ነገር አይደበቅም::
Арабча тафсирлар:
ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي وَهَبَ لِي عَلَى ٱلۡكِبَرِ إِسۡمَٰعِيلَ وَإِسۡحَٰقَۚ إِنَّ رَبِّي لَسَمِيعُ ٱلدُّعَآءِ
39. «ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማኢልንና ኢስሐቅን ለሰጠኝ አላህ ምስጋና ሁሉ ይገባው። ጌታዬ ልመናን ሰሚ ነውና::
Арабча тафсирлар:
رَبِّ ٱجۡعَلۡنِي مُقِيمَ ٱلصَّلَوٰةِ وَمِن ذُرِّيَّتِيۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلۡ دُعَآءِ
40. «ጌታዬ ሆይ! ሶላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ:: ከዘሮቼም አድርግ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ።
Арабча тафсирлар:
رَبَّنَا ٱغۡفِرۡ لِي وَلِوَٰلِدَيَّ وَلِلۡمُؤۡمِنِينَ يَوۡمَ يَقُومُ ٱلۡحِسَابُ
41. «ጌታችን ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ለአማኞችም ሁሉ ምርመራ በሚደረግበት ቀን ማረን።»
Арабча тафсирлар:
وَلَا تَحۡسَبَنَّ ٱللَّهَ غَٰفِلًا عَمَّا يَعۡمَلُ ٱلظَّٰلِمُونَۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمۡ لِيَوۡمٖ تَشۡخَصُ فِيهِ ٱلۡأَبۡصَٰرُ
42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ። የሚያቆያቸው ዓይኖች እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው::
Арабча тафсирлар:
 
Маънолар таржимаси Сура: Иброҳим
Суралар мундарижаси Бет рақами
 
Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси - Таржималар мундарижаси

Таржима қилган Муҳаммад Заин Заҳр ад-Дин. Африка академияси томонидан нашр қилинган.

Ёпиш