Check out the new design

Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси * - Таржималар мундарижаси

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Маънолар таржимаси Сура: Зориёт   Оят:
وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلۡحُبُكِ
7.የ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በሆነችው ሰማይ እምላለሁ::
Арабча тафсирлар:
إِنَّكُمۡ لَفِي قَوۡلٖ مُّخۡتَلِفٖ
8. እናንተ በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ።
Арабча тафсирлар:
يُؤۡفَكُ عَنۡهُ مَنۡ أُفِكَ
9. ከእርሱ የሚዝዞር ሰው ይዝዞራል::
Арабча тафсирлар:
قُتِلَ ٱلۡخَرَّٰصُونَ
10. በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ::
Арабча тафсирлар:
ٱلَّذِينَ هُمۡ فِي غَمۡرَةٖ سَاهُونَ
11. እነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስህተት ውስጥ ዘንጊዎች የሆኑት::
Арабча тафсирлар:
يَسۡـَٔلُونَ أَيَّانَ يَوۡمُ ٱلدِّينِ
12. የዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደሆነ ይጠይቃሉ::
Арабча тафсирлар:
يَوۡمَ هُمۡ عَلَى ٱلنَّارِ يُفۡتَنُونَ
13. (እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው::
Арабча тафсирлар:
ذُوقُواْ فِتۡنَتَكُمۡ هَٰذَا ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تَسۡتَعۡجِلُونَ
14. «መከራችሁን ቅመሱ ይህ ያ በእርሱ ትቻኮሉበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)::
Арабча тафсирлар:
إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي جَنَّٰتٖ وَعُيُونٍ
15. አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው::
Арабча тафсирлар:
ءَاخِذِينَ مَآ ءَاتَىٰهُمۡ رَبُّهُمۡۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَبۡلَ ذَٰلِكَ مُحۡسِنِينَ
16. ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ሆነው በገነት ውስጥ ይሆናሉ:: እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና::
Арабча тафсирлар:
كَانُواْ قَلِيلٗا مِّنَ ٱلَّيۡلِ مَا يَهۡجَعُونَ
17. ከሌሊቱ ጥቂቱን ብቻ ይተኙ ነበር::
Арабча тафсирлар:
وَبِٱلۡأَسۡحَارِ هُمۡ يَسۡتَغۡفِرُونَ
18. በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምህረትን ይለምናሉ::
Арабча тафсирлар:
وَفِيٓ أَمۡوَٰلِهِمۡ حَقّٞ لِّلسَّآئِلِ وَٱلۡمَحۡرُومِ
19. በገንዘቦቻቸዉም ውስጥ ለለማኝና ከልመና ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አለ።
Арабча тафсирлар:
وَفِي ٱلۡأَرۡضِ ءَايَٰتٞ لِّلۡمُوقِنِينَ
20. በምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች አያሌ ምልክቶች አሉ::
Арабча тафсирлар:
وَفِيٓ أَنفُسِكُمۡۚ أَفَلَا تُبۡصِرُونَ
21. (ሰዎች ሆይ!) በነፍሶቻችሁም ውስጥ አያሌ ምልክቶች አሉ:: ታዲያ አትመለከቱምን?
Арабча тафсирлар:
وَفِي ٱلسَّمَآءِ رِزۡقُكُمۡ وَمَا تُوعَدُونَ
22. ሲሳያችሁም የምትቀጠሩት (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ነው።
Арабча тафсирлар:
فَوَرَبِّ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ إِنَّهُۥ لَحَقّٞ مِّثۡلَ مَآ أَنَّكُمۡ تَنطِقُونَ
23. በሰማይና በምድር ጌታም እምላለሁ። እርሱ እናንተ እንደምትናገሩት ብጤ እርግጠኛ (እውነት) ነው።
Арабча тафсирлар:
هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ضَيۡفِ إِبۡرَٰهِيمَ ٱلۡمُكۡرَمِينَ
24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?
Арабча тафсирлар:
إِذۡ دَخَلُواْ عَلَيۡهِ فَقَالُواْ سَلَٰمٗاۖ قَالَ سَلَٰمٞ قَوۡمٞ مُّنكَرُونَ
25. በእርሱም ላይ በገቡና «ሰላም» ባሉት ጊዜ ምን እንደሆነ አስታውስ። ሰላም ግና ያልታወቃችሁ ህዝቦች ናችሁ አላቸው።
Арабча тафсирлар:
فَرَاغَ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ فَجَآءَ بِعِجۡلٖ سَمِينٖ
26. ወደ ቤተሰቡም ተዘነበለና ወዲያውም የሰባ ወይፈን አመጣ::
Арабча тафсирлар:
فَقَرَّبَهُۥٓ إِلَيۡهِمۡ قَالَ أَلَا تَأۡكُلُونَ
27. ከዚያ ወደ እነርሱ (አዘጋጅቶ) አቀረበውና «አትበሉም ወይ? አላቸው።
Арабча тафсирлар:
فَأَوۡجَسَ مِنۡهُمۡ خِيفَةٗۖ قَالُواْ لَا تَخَفۡۖ وَبَشَّرُوهُ بِغُلَٰمٍ عَلِيمٖ
28. ከእነርሱ መፍራትን በልቡ አሳደረ። «አትፍራ» አሉትም በአዋቂ ልጅም አበስሩት::
Арабча тафсирлар:
فَأَقۡبَلَتِ ٱمۡرَأَتُهُۥ فِي صَرَّةٖ فَصَكَّتۡ وَجۡهَهَا وَقَالَتۡ عَجُوزٌ عَقِيمٞ
29. ሚስቱም (በደስታ) እየጮኸች መጣች፤ ፊቷንም መታች «መካን አሮጊት (ነኝ)» አለችም።
Арабча тафсирлар:
قَالُواْ كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡعَلِيمُ
30. እነርሱም «ጌታሽ 'እንዲሁ (ይሁን)' ብሏል። እነሆ እርሱ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ ነው» አሏት::
Арабча тафсирлар:
 
Маънолар таржимаси Сура: Зориёт
Суралар мундарижаси Бет рақами
 
Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси - Таржималар мундарижаси

Таржима қилган Муҳаммад Заин Заҳр ад-Дин. Африка академияси томонидан нашр қилинган.

Ёпиш