Check out the new design

Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси * - Таржималар мундарижаси

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Маънолар таржимаси Сура: Аъроф   Оят:
۞ قَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ لَنُخۡرِجَنَّكَ يَٰشُعَيۡبُ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَكَ مِن قَرۡيَتِنَآ أَوۡ لَتَعُودُنَّ فِي مِلَّتِنَاۚ قَالَ أَوَلَوۡ كُنَّا كَٰرِهِينَ
88. ከህዝቦቹ መካከል እነዚያ የኮሩት መሪዎችም፡- «ሹዐይብ ሆይ! አንተንና እነዚያን ካንተ ጋር ያመኑትን ከከተማችን እናወጣችኋለን ወይም ወደ ሃይማኖታችን መመለስ አለባችሁ።» አሉ:: እርሱም አላቸው: «የጠላንም ብንሆን?
Арабча тафсирлар:
قَدِ ٱفۡتَرَيۡنَا عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا إِنۡ عُدۡنَا فِي مِلَّتِكُم بَعۡدَ إِذۡ نَجَّىٰنَا ٱللَّهُ مِنۡهَاۚ وَمَا يَكُونُ لَنَآ أَن نَّعُودَ فِيهَآ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ رَبُّنَاۚ وَسِعَ رَبُّنَا كُلَّ شَيۡءٍ عِلۡمًاۚ عَلَى ٱللَّهِ تَوَكَّلۡنَاۚ رَبَّنَا ٱفۡتَحۡ بَيۡنَنَا وَبَيۡنَ قَوۡمِنَا بِٱلۡحَقِّ وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡفَٰتِحِينَ
89. «አላህ ከእርሷ ከአዳንን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፍን:: አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ወደ እርሷ ልንመለስ አይገባንም:: የጌታችን እውቀቱ ከሁሉ ሰፋ:: በአላህ ላይ ብቻ ተመካን:: ጌታችን ሆይ! በእኛና በወገኖቻችን መካከል ፍረድ:: አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህና።» አለ።
Арабча тафсирлар:
وَقَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ لَئِنِ ٱتَّبَعۡتُمۡ شُعَيۡبًا إِنَّكُمۡ إِذٗا لَّخَٰسِرُونَ
90. ከወገኖቹም መካከል እነዚያ በአላህ የካዱት መሪዎች ለሕዝቡ «ሹዐይብን ብትከተሉ እናንተ ያኔ ከሳሪዎች ናችሁ።» አሉ።
Арабча тафсирлар:
فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلرَّجۡفَةُ فَأَصۡبَحُواْ فِي دَارِهِمۡ جَٰثِمِينَ
91. ወዲያውኑ የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው:: በየቤታቸው ውስጥ ተደፍተው አደሩ::
Арабча тафсирлар:
ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ شُعَيۡبٗا كَأَن لَّمۡ يَغۡنَوۡاْ فِيهَاۚ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ شُعَيۡبٗا كَانُواْ هُمُ ٱلۡخَٰسِرِينَ
92. እነዚያ ሹዓይብን ያስተባበሉት ሰዎች በእርሷ እንዳልነበሩባት ሆኑ:: እነዚያ ሹዓይብን ያስተባበሉት ከሳሪዎቹ እነርሱው ሆኑ::
Арабча тафсирлар:
فَتَوَلَّىٰ عَنۡهُمۡ وَقَالَ يَٰقَوۡمِ لَقَدۡ أَبۡلَغۡتُكُمۡ رِسَٰلَٰتِ رَبِّي وَنَصَحۡتُ لَكُمۡۖ فَكَيۡفَ ءَاسَىٰ عَلَىٰ قَوۡمٖ كَٰفِرِينَ
93. ሹዐይብም ትቷቸው ከእነርሱ ዞረና «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልእክቶች በእርግጥ አደረስኩላችሁ። ለእናንተም መከርኩ:: ታዲያ በከሃዲ ሰዎች ላይ እንዴት አዝናለሁ?» አለ::
Арабча тафсирлар:
وَمَآ أَرۡسَلۡنَا فِي قَرۡيَةٖ مِّن نَّبِيٍّ إِلَّآ أَخَذۡنَآ أَهۡلَهَا بِٱلۡبَأۡسَآءِ وَٱلضَّرَّآءِ لَعَلَّهُمۡ يَضَّرَّعُونَ
94. በየትኛዉም ከተማ ለአላህ ይተናነሱ ዘንድ በድህነትና በችግር የያዝናቸው ብንሆን እንጂ አንድንም ነብይ አልላክንም::
Арабча тафсирлар:
ثُمَّ بَدَّلۡنَا مَكَانَ ٱلسَّيِّئَةِ ٱلۡحَسَنَةَ حَتَّىٰ عَفَواْ وَّقَالُواْ قَدۡ مَسَّ ءَابَآءَنَا ٱلضَّرَّآءُ وَٱلسَّرَّآءُ فَأَخَذۡنَٰهُم بَغۡتَةٗ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ
95.ከዚያም እስከበዙና «አባቶቻችንን ድህነትና በሺታ በእርግጥ ነክቷቸዋል፡፡ (ይኽም የጊዜ ልማድ ነው)» እስካሉ ድረስ በመጥፎው ስፍራ በጎውን ለወጥን፡፡ ወዲያውም እነርሱ የማያውቁ ኾነው በድንገት ያዝናቸው፡፡
Арабча тафсирлар:
 
Маънолар таржимаси Сура: Аъроф
Суралар мундарижаси Бет рақами
 
Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси - Таржималар мундарижаси

Таржима қилган Муҳаммад Заин Заҳр ад-Дин. Африка академияси томонидан нашр қилинган.

Ёпиш