የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የ አማርኛ ቋንቋ ትርጉም * - የትርጉሞች ማዉጫ

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ሱረቱ አን ነጅም   አንቀጽ:

ሱረቱ አን ነጅም

وَٱلنَّجۡمِ إِذَا هَوَىٰ
በኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمۡ وَمَا غَوَىٰ
ባልደረባችሁ (ነቢያችን ሙሐመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمَا يَنطِقُ عَنِ ٱلۡهَوَىٰٓ
ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنۡ هُوَ إِلَّا وَحۡيٞ يُوحَىٰ
እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
عَلَّمَهُۥ شَدِيدُ ٱلۡقُوَىٰ
ኀይሎቹ ብርቱው አስተማረው፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ذُو مِرَّةٖ فَٱسۡتَوَىٰ
የዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَهُوَ بِٱلۡأُفُقِ ٱلۡأَعۡلَىٰ
እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ثُمَّ دَنَا فَتَدَلَّىٰ
ከዚያም ቀረበ፤ ወረደም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَكَانَ قَابَ قَوۡسَيۡنِ أَوۡ أَدۡنَىٰ
(ከእርሱ) የሁለት ደጋኖች ጫፍ ያህል ወይም (ከዚህ) ይበልጥ የቀረበ ኾነም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَأَوۡحَىٰٓ إِلَىٰ عَبۡدِهِۦ مَآ أَوۡحَىٰ
ወደ ባሪያውም (አላህ) ያወረደውን አወረደ፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مَا كَذَبَ ٱلۡفُؤَادُ مَا رَأَىٰٓ
(ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَفَتُمَٰرُونَهُۥ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ
ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَقَدۡ رَءَاهُ نَزۡلَةً أُخۡرَىٰ
በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
عِندَ سِدۡرَةِ ٱلۡمُنتَهَىٰ
በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
عِندَهَا جَنَّةُ ٱلۡمَأۡوَىٰٓ
እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِذۡ يَغۡشَى ٱلسِّدۡرَةَ مَا يَغۡشَىٰ
ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مَا زَاغَ ٱلۡبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ
ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَقَدۡ رَأَىٰ مِنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِ ٱلۡكُبۡرَىٰٓ
ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَفَرَءَيۡتُمُ ٱللَّٰتَ وَٱلۡعُزَّىٰ
አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمَنَوٰةَ ٱلثَّالِثَةَ ٱلۡأُخۡرَىٰٓ
ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን (አያችሁን? የምትግገዟቸው ኃይል አላቸውን?) (የላቸውም)።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَلَكُمُ ٱلذَّكَرُ وَلَهُ ٱلۡأُنثَىٰ
ለእናንተ ወንድ ለእርሱም ሴት (ልጅ) ይኖራልን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
تِلۡكَ إِذٗا قِسۡمَةٞ ضِيزَىٰٓ
ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍፍል ናት፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنۡ هِيَ إِلَّآ أَسۡمَآءٞ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٍۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَمَا تَهۡوَى ٱلۡأَنفُسُۖ وَلَقَدۡ جَآءَهُم مِّن رَّبِّهِمُ ٱلۡهُدَىٰٓ
እነርሱ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፡፡ አላህ በእርሷ (መግገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ከጌታቸውም መምሪያ የመጣላቸው ሲኾኑ ጥርጣሬንና ነፍሶች የሚዘነበሉበትን እንጅ ሌላ አይከተሉም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَمۡ لِلۡإِنسَٰنِ مَا تَمَنَّىٰ
ለሰው የተመኘው ሁሉ አለውን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَلِلَّهِ ٱلۡأٓخِرَةُ وَٱلۡأُولَىٰ
መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም (ዓለም) የአላህ ብቻ ናቸው፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
۞ وَكَم مِّن مَّلَكٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ لَا تُغۡنِي شَفَٰعَتُهُمۡ شَيۡـًٔا إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ أَن يَأۡذَنَ ٱللَّهُ لِمَن يَشَآءُ وَيَرۡضَىٰٓ
በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች (ሊማለዱለት) ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ لَيُسَمُّونَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ تَسۡمِيَةَ ٱلۡأُنثَىٰ
እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمَا لَهُم بِهِۦ مِنۡ عِلۡمٍۖ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّۖ وَإِنَّ ٱلظَّنَّ لَا يُغۡنِي مِنَ ٱلۡحَقِّ شَيۡـٔٗا
ለእነርሱም በእርሱ ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬም ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَأَعۡرِضۡ عَن مَّن تَوَلَّىٰ عَن ذِكۡرِنَا وَلَمۡ يُرِدۡ إِلَّا ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا
ከግሣጼያችንም (ከቁርኣን) ከሸሸና አነስተኛይቱን ሕይወት እንጅ ሌላን ከማይሻ ሰው ዙር (ተወው)፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ذَٰلِكَ مَبۡلَغُهُم مِّنَ ٱلۡعِلۡمِۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِمَنِ ٱهۡتَدَىٰ
ይህ (አነስተኛይቱን ሕይወት መምረጥ) ከዕውቀት ድካቸው ነው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን በእርግጥ ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም የቀናውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ لِيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ أَسَٰٓـُٔواْ بِمَا عَمِلُواْ وَيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ بِٱلۡحُسۡنَى
በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያን ያጠፉትን በሠሩት ሊመነዳ (ሊቀጣ) እነዚያን ያሳመሩትንም በመልካሚቱ (ገነት) ሊመነዳ (ነው)፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ٱلَّذِينَ يَجۡتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡفَوَٰحِشَ إِلَّا ٱللَّمَمَۚ إِنَّ رَبَّكَ وَٰسِعُ ٱلۡمَغۡفِرَةِۚ هُوَ أَعۡلَمُ بِكُمۡ إِذۡ أَنشَأَكُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ وَإِذۡ أَنتُمۡ أَجِنَّةٞ فِي بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمۡۖ فَلَا تُزَكُّوٓاْ أَنفُسَكُمۡۖ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَنِ ٱتَّقَىٰٓ
(እነርሱ) እነዚያ የኃጢኣትን ታላለቆችና አስጸያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፡፡ ግን ትናንሾቹ (የሚማሩ) ናቸው፡፡ ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፡፡ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በኾናችሁ ጊዜ እርሱ በናንተ (ኹነታ) ዐዋቂ ነው፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَفَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي تَوَلَّىٰ
ያንን (ከእምነት) የዞረውን አየህን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَعۡطَىٰ قَلِيلٗا وَأَكۡدَىٰٓ
ጥቂትን የሰጠውንና ያቋረጠውንም (አየህን?)
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَعِندَهُۥ عِلۡمُ ٱلۡغَيۡبِ فَهُوَ يَرَىٰٓ
የሩቁ ምስጢር ዕውቀት እርሱ ዘንድ አልለን? ስለዚህ እርሱ ያያልን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَمۡ لَمۡ يُنَبَّأۡ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ
ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِبۡرَٰهِيمَ ٱلَّذِي وَفَّىٰٓ
በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?)
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰ
(እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَن لَّيۡسَ لِلۡإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ
ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَنَّ سَعۡيَهُۥ سَوۡفَ يُرَىٰ
ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ثُمَّ يُجۡزَىٰهُ ٱلۡجَزَآءَ ٱلۡأَوۡفَىٰ
ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلۡمُنتَهَىٰ
መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَنَّهُۥ هُوَ أَضۡحَكَ وَأَبۡكَىٰ
እነሆ እርሱም አስሳቀ፣ አስለቀሰም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَنَّهُۥ هُوَ أَمَاتَ وَأَحۡيَا
እነሆ እርሱም ገደለ፣ አስነሳም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَنَّهُۥ خَلَقَ ٱلزَّوۡجَيۡنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰ
እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድንና ሴትን ፈጠረ፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مِن نُّطۡفَةٍ إِذَا تُمۡنَىٰ
ከፍትወት ጠብታ (በማህጸን ውስጥ) በምትፈሰስ ጊዜ፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَنَّ عَلَيۡهِ ٱلنَّشۡأَةَ ٱلۡأُخۡرَىٰ
የኋለኛይቱም ማስነሳት በእርሱ ላይ ነው፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَنَّهُۥ هُوَ أَغۡنَىٰ وَأَقۡنَىٰ
እነሆ እርሱም አከበረ፣ ጥሪተኛም አደረገ፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَنَّهُۥ هُوَ رَبُّ ٱلشِّعۡرَىٰ
እነሆ እርሱም የሺዕራ ጌታ ነው፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَنَّهُۥٓ أَهۡلَكَ عَادًا ٱلۡأُولَىٰ
እነሆ እርሱም የፊተኛይቱን ዓድ አጥፍቷል፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَثَمُودَاْ فَمَآ أَبۡقَىٰ
ሰሙድንም (አጥፍቷል)፤ አላስቀረምም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَقَوۡمَ نُوحٖ مِّن قَبۡلُۖ إِنَّهُمۡ كَانُواْ هُمۡ أَظۡلَمَ وَأَطۡغَىٰ
በፊትም የኑሕን ሕዝቦች (አጥፍቷል)፡፡ እነርሱ በጣም በደለኞችና እጅግ የጠመሙ እነርሱ ነበሩና፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱلۡمُؤۡتَفِكَةَ أَهۡوَىٰ
የተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَغَشَّىٰهَا مَا غَشَّىٰ
ያለበሳትንም አለበሳት፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكَ تَتَمَارَىٰ
ከጌታህም ጸጋዎች በየትኛው ትጠራጠራለህ?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
هَٰذَا نَذِيرٞ مِّنَ ٱلنُّذُرِ ٱلۡأُولَىٰٓ
ይህ ከፊተኞቹ አስፈራሪዎች (ጎሳ) የኾነ አስፈራሪ ነው፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَزِفَتِ ٱلۡأٓزِفَةُ
ቀራቢይቱ (ኅልፈተ ዓለም) ቀረበች፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَيۡسَ لَهَا مِن دُونِ ٱللَّهِ كَاشِفَةٌ
ለእርሷ ከአላህ ሌላ ገላጭ የላትም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَفَمِنۡ هَٰذَا ٱلۡحَدِيثِ تَعۡجَبُونَ
ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَتَضۡحَكُونَ وَلَا تَبۡكُونَ
ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَنتُمۡ سَٰمِدُونَ
እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَٱسۡجُدُواْۤ لِلَّهِۤ وَٱعۡبُدُواْ۩
ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡ {1}
{1} ኢዝህ አንድ የንባብ ሱጁድ (ሱጁዱትላዋ) ይደረጋል።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ሱረቱ አን ነጅም
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የ አማርኛ ቋንቋ ትርጉም - የትርጉሞች ማዉጫ

ወደ አማርኛ በሸይኽ ሙሓመድ ሷዲቅ እና በሸይኽ ሙሓመድ ሣኒ ሓቢብ የተተረጎመ የቁርዓን መልዕክተ ትርጉም። በሩዋድ የትርጉም ማእከልም ተቆጣጣሪነት ማስተካከያ ተደርጎበታል። ዋናው የትርጉም ቅጅም ለአስተያየቶች፣ ተከታታይ ግምገማ እና መሻሻል ቀርቧል።

መዝጋት