Check out the new design

የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ * - የትርጉሞች ማዉጫ


የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ሙሀመድ   አንቀጽ:
وَلَوۡ نَشَآءُ لَأَرَيۡنَٰكَهُمۡ فَلَعَرَفۡتَهُم بِسِيمَٰهُمۡۚ وَلَتَعۡرِفَنَّهُمۡ فِي لَحۡنِ ٱلۡقَوۡلِۚ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ أَعۡمَٰلَكُمۡ
30. (ሙሐመድ ሆይ!) ብንፈልግ ኖሮ እነርሱን ባሳየንህና በምልክታቸዉም በእርግጥ ባወቅካቸው ነበር:: ንግግርንም በማሸሞራቸው በእርግጥ ታውቃቸዋለህ:: አላህም ስራዎቻችሁን ሁሉ ያውቃልና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَنَبۡلُوَنَّكُمۡ حَتَّىٰ نَعۡلَمَ ٱلۡمُجَٰهِدِينَ مِنكُمۡ وَٱلصَّٰبِرِينَ وَنَبۡلُوَاْ أَخۡبَارَكُمۡ
31. (አማኞች ሆይ!) ከናንተ መካከል ተዋጊዎችንና ታጋሾቹን እስከምንገልጽ ድረስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን:: ወሬዎቻችሁንም (እስከምንገልጽ ድረስ) እንሞክራችኋለን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَشَآقُّواْ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ ٱلۡهُدَىٰ لَن يَضُرُّواْ ٱللَّهَ شَيۡـٔٗا وَسَيُحۡبِطُ أَعۡمَٰلَهُمۡ
32. እነዚያ የካዱና ከአላህም መንገድ ሰዎችን ያገዱ ለእነርሱም ቅኑ መንገድ ከተገለጸላቸው በኋላ መልዕክተኛውን የተከራከሩ ሁሉ አላህን በምንም አይጎዱትም:: ስራዎቻቸውንም በእርግጥ ያበላሻል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُواْ ٱلرَّسُولَ وَلَا تُبۡطِلُوٓاْ أَعۡمَٰلَكُمۡ
33. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ:: መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ስራዎቻችሁንም አታበላሹ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ ثُمَّ مَاتُواْ وَهُمۡ كُفَّارٞ فَلَن يَغۡفِرَ ٱللَّهُ لَهُمۡ
34. እነዚያ የካዱ ከአላህ መንገድ ሌሎችን ያገዱና ከዚያም እነርሱ ከሓዲያን ሆነው የሞቱ አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَلَا تَهِنُواْ وَتَدۡعُوٓاْ إِلَى ٱلسَّلۡمِ وَأَنتُمُ ٱلۡأَعۡلَوۡنَ وَٱللَّهُ مَعَكُمۡ وَلَن يَتِرَكُمۡ أَعۡمَٰلَكُمۡ
35. እናንተ አሸናፊዎች ስትሆኑና አላህም ከናንተ ጋር ሲሆን አትድከሙ:: ወደ እርቅም አትጥሩ:: ስራዎቻችሁን ፈጽሞ አያጎድልባችሁም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّمَا ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا لَعِبٞ وَلَهۡوٞۚ وَإِن تُؤۡمِنُواْ وَتَتَّقُواْ يُؤۡتِكُمۡ أُجُورَكُمۡ وَلَا يَسۡـَٔلۡكُمۡ أَمۡوَٰلَكُمۡ
36. ቅርቢቱ ሕይወት ጫወታና ዛዛታ ብቻ ናት:: ብታምኑና ቅጣቱንም ብትጠነቀቁ ምንዳዎቻችሁን ይሰጣችኋል:: ገንዘቦቻችሁንም ሁሉ አይጠይቃችሁም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِن يَسۡـَٔلۡكُمُوهَا فَيُحۡفِكُمۡ تَبۡخَلُواْ وَيُخۡرِجۡ أَضۡغَٰنَكُمۡ
37. እርሷን ቢጠይቃችሁና ችክ ቢልባችሁ ትሰስታላችሁ:: ቂሞቻችሁንም ያወጣል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
هَٰٓأَنتُمۡ هَٰٓؤُلَآءِ تُدۡعَوۡنَ لِتُنفِقُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ فَمِنكُم مَّن يَبۡخَلُۖ وَمَن يَبۡخَلۡ فَإِنَّمَا يَبۡخَلُ عَن نَّفۡسِهِۦۚ وَٱللَّهُ ٱلۡغَنِيُّ وَأَنتُمُ ٱلۡفُقَرَآءُۚ وَإِن تَتَوَلَّوۡاْ يَسۡتَبۡدِلۡ قَوۡمًا غَيۡرَكُمۡ ثُمَّ لَا يَكُونُوٓاْ أَمۡثَٰلَكُم
38. (አማኞች ሆይ!) አስተውሉ:: እናንተ እነዚያ በአላህ መንገድ ትለግሱ ዘንድ የምትጠሩ ናችሁ:: ከናንተም መካከልም የሚሰስት ሰው አለ:: የሚሰስት ሰው ሁሉ የሚሰስተው በራሱ ላይ ብቻ ነው:: አላህ በራሱ ተብቃቂ ነውና:: እናንተ ግን ድሆች ናችሁ:: ብትሸሹም ሌሎችን ሀዝቦች በቦታችሁ ይለውጣል:: ከዚያም ባለመታዘዝ እንደናንተ ብጤዎቻችሁ አይሆኑም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ሙሀመድ
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ - የትርጉሞች ማዉጫ

ከአፍሪካ አካዳሚ የተገኘ ‐ ተርጓሚ መሐመድ ዘይን ዘህረዲን

መዝጋት