የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - አማርኛ ትርጉም ‐ ዘይን * - የትርጉሞች ማዉጫ


የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ሱረቱ አል ዋቂዓህ   አንቀጽ:

ሱረቱ አል ዋቂዓህ

إِذَا وَقَعَتِ ٱلۡوَاقِعَةُ
1. ተጨባጪቱ (ቂያማ) እውን በሆነች ጊዜ፤
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَيۡسَ لِوَقۡعَتِهَا كَاذِبَةٌ
2. (ቂያማ) እውን ለመሆኗ አንዲትም አስተባባይ ነፍስ የለችም።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
خَافِضَةٞ رَّافِعَةٌ
3. እርሷ (ገሚሱን) ዝቅ አድራጊና (ገሚሱን) ደግሞ ከፍ አድራጊ ናት::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِذَا رُجَّتِ ٱلۡأَرۡضُ رَجّٗا
4. ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَبُسَّتِ ٱلۡجِبَالُ بَسّٗا
5. ተራራዎች (እንደተፈጨ ዱቄት) መፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَكَانَتۡ هَبَآءٗ مُّنۢبَثّٗا
6. የተበተነ ብናኝ በሆኑም ጊዜ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَكُنتُمۡ أَزۡوَٰجٗا ثَلَٰثَةٗ
7. እናንተ (ሰዎች) ሶስት ዓይነቶችም በሆናችሁ ጊዜ (ገሚሱን ዝቅ እና ገሚሱን ከፍ ታደርጋለች)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَأَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ
8. እናም በዚያ ቀን የቀኝ ጓዶች ለመሆን የበቁ ሁሉ ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ
9. የግራ ጓዶች ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱلسَّٰبِقُونَ ٱلسَّٰبِقُونَ
10. እነዚያ (ለበጎ ስራ) ቀዳሚዎች የሆኑ ሁሉ (ለገነትም) ቀዳሚዎች ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلۡمُقَرَّبُونَ
11. እነዚያ (በአላህ ዘንድም) ባለሟሎች ናቸው
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
12. በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ሲሆኑ
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ثُلَّةٞ مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ
13. (የዚህ እድል ባለ ቤቶች) ከፊተኞቹ ብዙ ቡድኖች ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَقَلِيلٞ مِّنَ ٱلۡأٓخِرِينَ
14. ከኋለኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
عَلَىٰ سُرُرٖ مَّوۡضُونَةٖ
15. በተሸሞኑ አልጋዎች ላይ ይሆናሉ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مُّتَّكِـِٔينَ عَلَيۡهَا مُتَقَٰبِلِينَ
16. በእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲሆኑ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
يَطُوفُ عَلَيۡهِمۡ وِلۡدَٰنٞ مُّخَلَّدُونَ
17. እነርሱን (ለማገለገል) በእነርሱ ዙሪያ ሁልጊዜ የማያረጁ ወጣት ልጆች ይዘዋወራሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
بِأَكۡوَابٖ وَأَبَارِيقَ وَكَأۡسٖ مِّن مَّعِينٖ
18. ከ(ጠጅ) ምንጭ በብርጨቆዎች፣ በኩስኩስቶችና (እብሪቆች) በጽዋም በእነርሱ ዙሪያ እንዲዞሩ ይደረጋሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَّا يُصَدَّعُونَ عَنۡهَا وَلَا يُنزِفُونَ
19. ከእርሷ የራስ ምታት እንኳን አያገኛቸዉም:: አይሰክሩምም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَفَٰكِهَةٖ مِّمَّا يَتَخَيَّرُونَ
20. ከእሸቶች ከሚመርጡት ዓይነት
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَحۡمِ طَيۡرٖ مِّمَّا يَشۡتَهُونَ
21. ከሚፈልጉት የበራሪ ስጋ ይዘው ይዞሩላቸዋል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَحُورٌ عِينٞ
22. ዓይናማዎች የሆኑ ነጫጭ ቆንጆ ሴቶችም አሏቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
كَأَمۡثَٰلِ ٱللُّؤۡلُوِٕ ٱلۡمَكۡنُونِ
23. ልክ እንደተሸፈነ ሉል የሚመስሉ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
24. ለዚያ ይሰሩት በነበሩት መልካም ተግባር ምክንያት ዋጋ ይሆን ዘንድ ይህንን አደረግንላቸው።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَا يَسۡمَعُونَ فِيهَا لَغۡوٗا وَلَا تَأۡثِيمًا
25. በውስጧ ውድቅ ንግግርንና መወንጀልንም አይሰሙም።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِلَّا قِيلٗا سَلَٰمٗا سَلَٰمٗا
26. ሰላም ሰላም መባባልን ግን ይሰማሉ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡيَمِينِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلۡيَمِينِ
27. የቀኝ ጓዶች ምንኛ የከበሩ የቀኝ ጓዶች ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فِي سِدۡرٖ مَّخۡضُودٖ
28. በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَطَلۡحٖ مَّنضُودٖ
29. ፍሬው በተነባበረ ሙዝ ዛፍም ውስጥ ናቸው።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَظِلّٖ مَّمۡدُودٖ
30. በተዘረጋ ጥላ ስርም ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمَآءٖ مَّسۡكُوبٖ
31. በሚንቧቡ ውሃ አጠገብም ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَفَٰكِهَةٖ كَثِيرَةٖ
32. በብዙ ዓይነት ፍራፍሬዎችም ውስጥ ናቸው።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَّا مَقۡطُوعَةٖ وَلَا مَمۡنُوعَةٖ
33. ምንጊዜም የማትቋረጥ የማትከለከልም የሆነች፤
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَفُرُشٖ مَّرۡفُوعَةٍ
34. ከፍ በተደረጉ ምንጣፎች ላይም ናቸው።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّآ أَنشَأۡنَٰهُنَّ إِنشَآءٗ
35. እኛ (የገነት ሴቶችን) አዲስ ፍጥረት አድርገን ፈጠርናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَجَعَلۡنَٰهُنَّ أَبۡكَارًا
36. እናም ደናግሎችም አደረግናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
عُرُبًا أَتۡرَابٗا
37. ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎችና እኩያዎች አደረግናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لِّأَصۡحَٰبِ ٱلۡيَمِينِ
38. ለቀኝ ጓዶች አዘጋጀናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ثُلَّةٞ مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ
39. ከፊተኞቹ ብዙ ቡድኖች ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَثُلَّةٞ مِّنَ ٱلۡأٓخِرِينَ
40. ከኋለኞቹም ብዙ ቡድኖች ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَصۡحَٰبُ ٱلشِّمَالِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلشِّمَالِ
41. የግራ ጓዶችም ምንኛ የተዋረዱ የግራ ጓዶች ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فِي سَمُومٖ وَحَمِيمٖ
42. በመርዛም ንፋስና በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَظِلّٖ مِّن يَحۡمُومٖ
43. ከጥቁር ጭስም በሆነ ጥላ ውስጥ
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَّا بَارِدٖ وَلَا كَرِيمٍ
44. ቀዝቃዛም መልካምም ያልሆነ
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَبۡلَ ذَٰلِكَ مُتۡرَفِينَ
45. እነርሱ ከዚህ በፊት የነብያትን አስተምህሮት ወደ ጎን የተው የዱንያ ቅምጥሎች ነበሩና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَكَانُواْ يُصِرُّونَ عَلَى ٱلۡحِنثِ ٱلۡعَظِيمِ
46. በከባድ ኃጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَكَانُواْ يَقُولُونَ أَئِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ
47. (እንዲህ) ይሉ ነበርም፡ "ሞተን አፈር፣ አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَوَءَابَآؤُنَا ٱلۡأَوَّلُونَ
48. "የፊተኞቹ አባቶቻችንንም (ይቀሰቀሳሉን)?" (ይሉ ነበር)
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
قُلۡ إِنَّ ٱلۡأَوَّلِينَ وَٱلۡأٓخِرِينَ
49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) "ፊተኞቹም ሆኑ ኋለኞቹ
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَمَجۡمُوعُونَ إِلَىٰ مِيقَٰتِ يَوۡمٖ مَّعۡلُومٖ
50. "በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው" በላቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ثُمَّ إِنَّكُمۡ أَيُّهَا ٱلضَّآلُّونَ ٱلۡمُكَذِّبُونَ
51. ከዚያም እናንተ ጠማሞችና አስተባባዩች ሆይ!
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَأٓكِلُونَ مِن شَجَرٖ مِّن زَقُّومٖ
52. ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَمَالِـُٔونَ مِنۡهَا ٱلۡبُطُونَ
53. ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَشَٰرِبُونَ عَلَيۡهِ مِنَ ٱلۡحَمِيمِ
54. በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَشَٰرِبُونَ شُرۡبَ ٱلۡهِيمِ
55. የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
هَٰذَا نُزُلُهُمۡ يَوۡمَ ٱلدِّينِ
56. ይህ የፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
نَحۡنُ خَلَقۡنَٰكُمۡ فَلَوۡلَا تُصَدِّقُونَ
57. (ሰዎች ሆይ!) እኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَفَرَءَيۡتُم مَّا تُمۡنُونَ
58. በሴቶች ማህጸኖች የምታፈሱትን (የምትረጩትን ፍትወት) አያችሁን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ءَأَنتُمۡ تَخۡلُقُونَهُۥٓ أَمۡ نَحۡنُ ٱلۡخَٰلِقُونَ
59. እናንተ ትፈጥሩታላችሁን! ወይስ እኛ ነን ፈጣሪዎቹ?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
نَحۡنُ قَدَّرۡنَا بَيۡنَكُمُ ٱلۡمَوۡتَ وَمَا نَحۡنُ بِمَسۡبُوقِينَ
60. እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
عَلَىٰٓ أَن نُّبَدِّلَ أَمۡثَٰلَكُمۡ وَنُنشِئَكُمۡ فِي مَا لَا تَعۡلَمُونَ
61. ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም ቅርጽ እናንተኑ በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَقَدۡ عَلِمۡتُمُ ٱلنَّشۡأَةَ ٱلۡأُولَىٰ فَلَوۡلَا تَذَكَّرُونَ
62. የፊተኛይቱን አፈጣጠር በእርግጥ አውቃችኋል አትገነዘቡምን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَفَرَءَيۡتُم مَّا تَحۡرُثُونَ
63. የምትዘሩትን (አዝርአት) አያችሁን
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ءَأَنتُمۡ تَزۡرَعُونَهُۥٓ أَمۡ نَحۡنُ ٱلزَّٰرِعُونَ
64. እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَوۡ نَشَآءُ لَجَعَلۡنَٰهُ حُطَٰمٗا فَظَلۡتُمۡ تَفَكَّهُونَ
65. ብንሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባረደግነው እና የምትደነቁም በሆናችሁ ነበር::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّا لَمُغۡرَمُونَ
66. "እኛ በእዳ ተያዥዎች ነን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
بَلۡ نَحۡنُ مَحۡرُومُونَ
67. "በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለክልን ነን" ትሉ ነበር።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَفَرَءَيۡتُمُ ٱلۡمَآءَ ٱلَّذِي تَشۡرَبُونَ
68. ያንን ምትጠጡትን ውሃ አያችሁን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ءَأَنتُمۡ أَنزَلۡتُمُوهُ مِنَ ٱلۡمُزۡنِ أَمۡ نَحۡنُ ٱلۡمُنزِلُونَ
69. እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَوۡ نَشَآءُ جَعَلۡنَٰهُ أُجَاجٗا فَلَوۡلَا تَشۡكُرُونَ
70. ብንፈልግ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር:: አታመሰግኑምን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَفَرَءَيۡتُمُ ٱلنَّارَ ٱلَّتِي تُورُونَ
71. ያችንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ءَأَنتُمۡ أَنشَأۡتُمۡ شَجَرَتَهَآ أَمۡ نَحۡنُ ٱلۡمُنشِـُٔونَ
72. እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹ ነን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
نَحۡنُ جَعَلۡنَٰهَا تَذۡكِرَةٗ وَمَتَٰعٗا لِّلۡمُقۡوِينَ
73. እኛ ለገሀነም ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَسَبِّحۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلۡعَظِيمِ
74. የታላቁን ጌታህንም ስም አጥራው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
۞ فَلَآ أُقۡسِمُ بِمَوَٰقِعِ ٱلنُّجُومِ
75. በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِنَّهُۥ لَقَسَمٞ لَّوۡ تَعۡلَمُونَ عَظِيمٌ
76. እርሱም ብታውቁ ታላቅ መሀላ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّهُۥ لَقُرۡءَانٞ كَرِيمٞ
77. እርሱ የተከበረ ቁርኣን ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فِي كِتَٰبٖ مَّكۡنُونٖ
78. በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥም ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَّا يَمَسُّهُۥٓ إِلَّا ٱلۡمُطَهَّرُونَ
79. የተጥራሩት እንጂ ሌላ አይነካዉም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
تَنزِيلٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
80. ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَفَبِهَٰذَا ٱلۡحَدِيثِ أَنتُم مُّدۡهِنُونَ
81. በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَتَجۡعَلُونَ رِزۡقَكُمۡ أَنَّكُمۡ تُكَذِّبُونَ
82. ሲሳያችሁንም (ዝናብን) እናንተ የምታስተባበሉት ታደርጋላችሁን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَلَوۡلَآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلۡحُلۡقُومَ
83. ነፍስ ጉሮሮንም በደረሰች ጊዜ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَنتُمۡ حِينَئِذٖ تَنظُرُونَ
84. እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትሆኑ፤
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَنَحۡنُ أَقۡرَبُ إِلَيۡهِ مِنكُمۡ وَلَٰكِن لَّا تُبۡصِرُونَ
85. እኛም ግን እናንተ አታዩም እንጂ ከናንተ ይልቅ ወደ እርሱ የቀረብን ነን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَلَوۡلَآ إِن كُنتُمۡ غَيۡرَ مَدِينِينَ
86. የማትዳኙም ከሆናችሁ
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
تَرۡجِعُونَهَآ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
87. እውነተኞች እንደሆናችሁ ነፍሲቱን ወደ አካል ለምን አትመልሷትም?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَأَمَّآ إِن كَانَ مِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ
88. እናም ሟቹ ከባለሟሎቹ ከሆነም፤
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَرَوۡحٞ وَرَيۡحَانٞ وَجَنَّتُ نَعِيمٖ
89. ለእርሱ እረፍት መልካም ሲሳይና የመጠቀሚያ ገነት አለው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَمَّآ إِن كَانَ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلۡيَمِينِ
90. ሟቹ ከቀኝ ጓዶችም ከሆነ
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَسَلَٰمٞ لَّكَ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلۡيَمِينِ
91."ከቀኝ ጓዶች ስለሆንክ ላንተ ሰላም ነው የሚገባህ" ይባላል።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَمَّآ إِن كَانَ مِنَ ٱلۡمُكَذِّبِينَ ٱلضَّآلِّينَ
92. ሟች ከእነዚያ ከሚያስተባብሉት ጠማማዎች ከሆነ ደግሞ
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَنُزُلٞ مِّنۡ حَمِيمٖ
93. ከፈላ ውሃ የሆነ መስተንግዶ አለለት::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَتَصۡلِيَةُ جَحِيمٍ
94. በገሀነም መቃጠልም አለለት::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ حَقُّ ٱلۡيَقِينِ
95. ይህ እርሱ እርግጠኛው እውነት ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَسَبِّحۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلۡعَظِيمِ
96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የታላቁ ጌታህን ስም አጥራው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ሱረቱ አል ዋቂዓህ
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - አማርኛ ትርጉም ‐ ዘይን - የትርጉሞች ማዉጫ

አማርኛ ትርጉም

መዝጋት