የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - አማርኛ ትርጉም ‐ ዘይን * - የትርጉሞች ማዉጫ


የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ሱረቱ አል ቀለም   አንቀጽ:

ሱረቱ አል ቀለም

نٓۚ وَٱلۡقَلَمِ وَمَا يَسۡطُرُونَ
1. ኑን፤ በብዕር እና በዚያም በሱ በሚጽፉት ሁሉ እምላለሁ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مَآ أَنتَ بِنِعۡمَةِ رَبِّكَ بِمَجۡنُونٖ
2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በጌታህ ጸጋ ምክኒያት ዕብድ አይደለህም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِنَّ لَكَ لَأَجۡرًا غَيۡرَ مَمۡنُونٖ
3. ላንተም ከጌታህ የማይቋረጥ ምንዳ (የልፋት ዋጋ) በእርግጥ አለህ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٖ
4. አንተም በታላቅ ጸባይ ላይ ነህ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَسَتُبۡصِرُ وَيُبۡصِرُونَ
5. ወደ ፊት አንተም ታያለህ፤ እነርሱም ያያሉ፤
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
بِأَييِّكُمُ ٱلۡمَفۡتُونُ
6. ዕብደት በማንኛችሁ እንዳለ (እብዱ ማን እንደሆነ)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُهۡتَدِينَ
7. ጌታህ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው አዋቂ ነው። ወደ ቀናው መንገድ ተመሪዎችንም አዋቂ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَلَا تُطِعِ ٱلۡمُكَذِّبِينَ
8. ስለዚህ ለአስተባባዩች (ሁሉ) አትታዘዝ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَدُّواْ لَوۡ تُدۡهِنُ فَيُدۡهِنُونَ
9. (አስተባባዩች) ብትመሳሰላቸውና እነርሱም ቢመሳሰሉህ ተመኙ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَا تُطِعۡ كُلَّ حَلَّافٖ مَّهِينٍ
10. መሓለኛን ወራዳን ሁሉ አትታዘዝ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
هَمَّازٖ مَّشَّآءِۭ بِنَمِيمٖ
11. ሰውን አነዋሪን፤ ነገር አሳባቂን፤
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مَّنَّاعٖ لِّلۡخَيۡرِ مُعۡتَدٍ أَثِيمٍ
12.ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፤ ወሰን አላፊን፤ ኃጢአተኛንም፤
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
عُتُلِّۭ بَعۡدَ ذَٰلِكَ زَنِيمٍ
13. ልበ ደረቅን ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ የዝሙት ልጅ ዲቃላን (አትታዘዝ)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَن كَانَ ذَا مَالٖ وَبَنِينَ
14. የገንዘብና የልጆች ባለቤት በመሆኑ (ያስተባብላል)።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ءَايَٰتُنَا قَالَ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
15. በእርሱ ላይ እንቀፆቻችን በሚነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
سَنَسِمُهُۥ عَلَى ٱلۡخُرۡطُومِ
16. በአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክትን እናደርግበታለን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّا بَلَوۡنَٰهُمۡ كَمَا بَلَوۡنَآ أَصۡحَٰبَ ٱلۡجَنَّةِ إِذۡ أَقۡسَمُواْ لَيَصۡرِمُنَّهَا مُصۡبِحِينَ
17. እኛ እነዚያን የአትክልቲቱን ባለቤቶች ማልደው ፍሬዋን ሊለቅሟት (አላህ ቢሻ ሳይሉ) በማሉ ጊዜ እንደሞከርን ሁሉ የመካ ሰዎችንም ሞከርናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَا يَسۡتَثۡنُونَ
18. (በመሓላቸው) አያስቀሩምም፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَطَافَ عَلَيۡهَا طَآئِفٞ مِّن رَّبِّكَ وَهُمۡ نَآئِمُونَ
19.እነርሱ የተኙ ሆነዉም ሳሉ ከጌታህ የሆነ ዟሪ በእርሷ ላይ ዞረባት::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَأَصۡبَحَتۡ كَٱلصَّرِيمِ
20. እንደ ሌሊት ጨለማ የከሰለች ሆና አነጋች (አደረች)።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَتَنَادَوۡاْ مُصۡبِحِينَ
21.ያነጉም ሆነው ተጠራሩ
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَنِ ٱغۡدُواْ عَلَىٰ حَرۡثِكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰرِمِينَ
22. "ቆራጮች እንደ ሆናችሁ ወደ እርሻችሁ ለመሄድ ማልዱ በማለት" (ተጠራሩ)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَٱنطَلَقُواْ وَهُمۡ يَتَخَٰفَتُونَ
23. እነርሱ የሚያሾካሾኩ ሆነው ሄዱም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَن لَّا يَدۡخُلَنَّهَا ٱلۡيَوۡمَ عَلَيۡكُم مِّسۡكِينٞ
24. ዛሬ በእናንተ ላይ አንድም ድሃ እንዳይገባት በማለትና
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَغَدَوۡاْ عَلَىٰ حَرۡدٖ قَٰدِرِينَ
25. ድሆችን በመከልከልም ላይ በሀሳባቸው ቻዮች ሆነው ማለዱ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَلَمَّا رَأَوۡهَا قَالُوٓاْ إِنَّا لَضَآلُّونَ
26. ከዚያ ተቃጥላ ባዩዋት ጊዜ (እንዲህ) አሉ: «እኛ በእርግጥ ተሳሳቾች ነን፤
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
بَلۡ نَحۡنُ مَحۡرُومُونَ
27. «ይልቁንም እኛ ከአላህ የተከለከልን እደለ ቢሶች ነን» አሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
قَالَ أَوۡسَطُهُمۡ أَلَمۡ أَقُل لَّكُمۡ لَوۡلَا تُسَبِّحُونَ
28. (ከመካከላቸው) ትክክለኛቸው (አስተዋያቸው)፡- «እናንተ አላህን ለምን አታጠሩም (አታወሱም) አላልኳችሁም ነበርን?» አለ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
قَالُواْ سُبۡحَٰنَ رَبِّنَآ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ
29. «(ሁላቸዉም) ጌታችን ጥራት ይገባው፤ እኛ በዳዩች ነበርን» አሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَلَٰوَمُونَ
30. እርስ በራሳቸው የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
قَالُواْ يَٰوَيۡلَنَآ إِنَّا كُنَّا طَٰغِينَ
31. «ዋ፤ጥፋታችን፤ እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን» አሉ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
عَسَىٰ رَبُّنَآ أَن يُبۡدِلَنَا خَيۡرٗا مِّنۡهَآ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا رَٰغِبُونَ
32. «ጌታችን ከእርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጀላል:: እኛ ወደ ጌታችን ከጃዩች ነን» አሉ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
كَذَٰلِكَ ٱلۡعَذَابُۖ وَلَعَذَابُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَكۡبَرُۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ
33. (የአላህ) ቅጣቱ ልክ እንደዚሁ ነው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ከዚህ የበለጠ ከባድ ነው:: የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ (ከዚህ ቅጣት በተጠነቀቁ ነበር)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّ لِلۡمُتَّقِينَ عِندَ رَبِّهِمۡ جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
34. ለጥንቁቆች በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَفَنَجۡعَلُ ٱلۡمُسۡلِمِينَ كَٱلۡمُجۡرِمِينَ
35. ሙስሊሞችን እንደ ከሓዲያን እናደርጋለን? (አናደርግም)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مَا لَكُمۡ كَيۡفَ تَحۡكُمُونَ
36. ለእናንተ ምን (አስረጂ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ( ምን ነካችሁ)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَمۡ لَكُمۡ كِتَٰبٞ فِيهِ تَدۡرُسُونَ
37. በእውነቱ ለእናንተ በእርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّ لَكُمۡ فِيهِ لَمَا تَخَيَّرُونَ
38. በውስጡ ለእናንተ የምትመርጡት አላችሁን? (የሚል)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَمۡ لَكُمۡ أَيۡمَٰنٌ عَلَيۡنَا بَٰلِغَةٌ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ إِنَّ لَكُمۡ لَمَا تَحۡكُمُونَ
39. ወይስ «ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ» በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሳኤ ቀን ደራሽ የሆኑ መሐላዎች ለእናንተ በእኛ ላይ አሏችሁን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
سَلۡهُمۡ أَيُّهُم بِذَٰلِكَ زَعِيمٌ
40. በዚህ ማንኛቸው ተያያዥ እንደ ኾነ ጠይቃቸው፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَمۡ لَهُمۡ شُرَكَآءُ فَلۡيَأۡتُواْ بِشُرَكَآئِهِمۡ إِن كَانُواْ صَٰدِقِينَ
41. ወይስ ለእነርሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) ተጋሪዎች አሏቸውን? እውነተኞችም እንደሆኑ ተጋሪዎቻቸውን ያምጡ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
يَوۡمَ يُكۡشَفُ عَن سَاقٖ وَيُدۡعَوۡنَ إِلَى ٱلسُّجُودِ فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ
42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ባት የሚገለጥበትን፤ (ከሓዲያን) ወደ መስገድ የሚጠሩበትና የማይችሉበትን ቀን (አስታውስ)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
خَٰشِعَةً أَبۡصَٰرُهُمۡ تَرۡهَقُهُمۡ ذِلَّةٞۖ وَقَدۡ كَانُواْ يُدۡعَوۡنَ إِلَى ٱلسُّجُودِ وَهُمۡ سَٰلِمُونَ
43. ዓይኖቻቸው የፈሩ፤ ውርደት የምትሸፍናቸው ሲሆኑ (ወደ ስግደት የሚጠሩበትን):: እነርሱ (በምድረ ዓለም) ደህና ሆነው ሳሉ ወደ ስግድት በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَذَرۡنِي وَمَن يُكَذِّبُ بِهَٰذَا ٱلۡحَدِيثِۖ سَنَسۡتَدۡرِجُهُم مِّنۡ حَيۡثُ لَا يَعۡلَمُونَ
44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመሆኑም እኔን በዚህ ንግግር ከሚያስተባብሉት ሰዎች ጋር ተወኝ፤ (ለእነርሱ እኔ እበቃሃለሁ):: ከማያውቁት ስፍራ አዘናግተን እንይዛቸዋለን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأُمۡلِي لَهُمۡۚ إِنَّ كَيۡدِي مَتِينٌ
45. እነርሱንም አዘገያቸዋለሁ:: (ዘዴዬ) ብቀላየ ብርቱ ነውና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَمۡ تَسۡـَٔلُهُمۡ أَجۡرٗا فَهُم مِّن مَّغۡرَمٖ مُّثۡقَلُونَ
46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወይንስ በእውነቱ (በማስተማርህ) ዋጋን እንዲከፍሉህ ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳ የተከበዱ ናቸውን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَمۡ عِندَهُمُ ٱلۡغَيۡبُ فَهُمۡ يَكۡتُبُونَ
47. ወይስ ከእነርሱ ዘንድ የሩቁ ምስጢር እውቀት አለን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَٱصۡبِرۡ لِحُكۡمِ رَبِّكَ وَلَا تَكُن كَصَاحِبِ ٱلۡحُوتِ إِذۡ نَادَىٰ وَهُوَ مَكۡظُومٞ
48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ)፤ ለጌታህ (ዉሳኔ) ፍርድ ታገስ:: (በመበሳጨትና ባለ መታገስ) እንደ ዓሳው ባለቤት እንደ (ነብዩ ዩኑስ) አትሁን:: እርሱ በጭንቀት የተሞላ ሆኖ (ጌታውን) በተጣራ ጊዜ
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَّوۡلَآ أَن تَدَٰرَكَهُۥ نِعۡمَةٞ مِّن رَّبِّهِۦ لَنُبِذَ بِٱلۡعَرَآءِ وَهُوَ مَذۡمُومٞ
49. ከጌታው የሆነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በምድረ በዳ ተወቃሽ ሆኖ በተጣለ ነበር::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَٱجۡتَبَٰهُ رَبُّهُۥ فَجَعَلَهُۥ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
50. ጌታዉም (በነብይነት) መረጠው:: ከደጋጎችም አደረገው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِن يَكَادُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَيُزۡلِقُونَكَ بِأَبۡصَٰرِهِمۡ لَمَّا سَمِعُواْ ٱلذِّكۡرَ وَيَقُولُونَ إِنَّهُۥ لَمَجۡنُونٞ
51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነሆ እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው (ሊያጠፉህ) ይቃረባሉ፤ «እርሱም በእርግጥ እብድ ነዉም» ይላሉ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمَا هُوَ إِلَّا ذِكۡرٞ لِّلۡعَٰلَمِينَ
52.እርሱ ግን ለዓለማት መገሰጫ (ገሳጭ) እንጂ ሌላ አይደለም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ሱረቱ አል ቀለም
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - አማርኛ ትርጉም ‐ ዘይን - የትርጉሞች ማዉጫ

አማርኛ ትርጉም

መዝጋት