للإطلاع على الموقع بحلته الجديدة

ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا * - فهرس التراجم


ترجمة معاني سورة: الحج   آية:
حُنَفَآءَ لِلَّهِ غَيۡرَ مُشۡرِكِينَ بِهِۦۚ وَمَن يُشۡرِكۡ بِٱللَّهِ فَكَأَنَّمَا خَرَّ مِنَ ٱلسَّمَآءِ فَتَخۡطَفُهُ ٱلطَّيۡرُ أَوۡ تَهۡوِي بِهِ ٱلرِّيحُ فِي مَكَانٖ سَحِيقٖ
31. ለአላህ ታዛዦች፤ በእርሱ የማታጋሩና ወደ ቀጥተኞች መንገድ የተዘነበላችሁ ሁኑ:: በአላህ የሚያጋራ ሁሉ ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው ወይም ንፋስ በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ነው::
التفاسير العربية:
ذَٰلِكَۖ وَمَن يُعَظِّمۡ شَعَٰٓئِرَ ٱللَّهِ فَإِنَّهَا مِن تَقۡوَى ٱلۡقُلُوبِ
32. (ነገሩ) ይህ ነው። የአላህን ሃይማኖታዊ ምልክቶች የሚያከብር ሁሉ ይህ ድርጊቱ አላህን ከሚፈሩ ልቦች የሚፈጸም ጥንቃቄ ነው።
التفاسير العربية:
لَكُمۡ فِيهَا مَنَٰفِعُ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗى ثُمَّ مَحِلُّهَآ إِلَى ٱلۡبَيۡتِ ٱلۡعَتِيقِ
33. ለእናንተ በእርሷ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ጥቅሞች አሏችሁ:: ከዚያም የ(ኡዱሂያ)ማረጃ ስፍራ እጥንታዊው ቤት አጠገብ ነው::
التفاسير العربية:
وَلِكُلِّ أُمَّةٖ جَعَلۡنَا مَنسَكٗا لِّيَذۡكُرُواْ ٱسۡمَ ٱللَّهِ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّنۢ بَهِيمَةِ ٱلۡأَنۡعَٰمِۗ فَإِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞ فَلَهُۥٓ أَسۡلِمُواْۗ وَبَشِّرِ ٱلۡمُخۡبِتِينَ
34. ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ ለህዝቦች ሁሉ (ወደ አላህ) መስዋዕት ማቅረብን ሀይማኖታዊ ሥርአቶችን ደነገግን:: አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እርሱንም ብቻ ታዘዙ:: ለአላህ ተዋራጆችንም በመልካም ነገር አብስራቸው::
التفاسير العربية:
ٱلَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ ٱللَّهُ وَجِلَتۡ قُلُوبُهُمۡ وَٱلصَّٰبِرِينَ عَلَىٰ مَآ أَصَابَهُمۡ وَٱلۡمُقِيمِي ٱلصَّلَوٰةِ وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ
35. እነዚያን አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚጨነቁትን (የሚፈሩትን)፤ በደረሰባቸዉም መከራ ላይ ታጋሾችን፤ ሰላትንም አስተካክለው ሰጋጆችን፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ የሚለግሱትን በገነት አብስር::
التفاسير العربية:
وَٱلۡبُدۡنَ جَعَلۡنَٰهَا لَكُم مِّن شَعَٰٓئِرِ ٱللَّهِ لَكُمۡ فِيهَا خَيۡرٞۖ فَٱذۡكُرُواْ ٱسۡمَ ٱللَّهِ عَلَيۡهَا صَوَآفَّۖ فَإِذَا وَجَبَتۡ جُنُوبُهَا فَكُلُواْ مِنۡهَا وَأَطۡعِمُواْ ٱلۡقَانِعَ وَٱلۡمُعۡتَرَّۚ كَذَٰلِكَ سَخَّرۡنَٰهَا لَكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
36. ግመሎችንም ለእናንተ ከአላህ ሃይማኖት ምልክቶች አደረግናቸው:: በእነርሱ ለእናንተ ብዙ መልካም ጥቅሞች አሏችሁ:: በእርሷም ላይ ስታርዷት በሦስት እግሮቿ ቆማ የተሰለፈች ሆና የአላህን ስም አውሱ:: ጎኖቻቸዉም በወደቁ ጊዜ ከእርሷ ብሉ:: በግልጽ ለማኝንም ለልመና የሚያገዳድምንም አብሉ:: ልክ እንደዚሁ ታመሰግኑ ዘንድ ለእናንተ ገራናት::
التفاسير العربية:
لَن يَنَالَ ٱللَّهَ لُحُومُهَا وَلَا دِمَآؤُهَا وَلَٰكِن يَنَالُهُ ٱلتَّقۡوَىٰ مِنكُمۡۚ كَذَٰلِكَ سَخَّرَهَا لَكُمۡ لِتُكَبِّرُواْ ٱللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَىٰكُمۡۗ وَبَشِّرِ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
37. አላህን ስጋዎቿም ሆኑ ደሞቿ ፈጽሞ አይደርሰዉም:: ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል:: እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጎ ሰሪዎችንም አብስር::
التفاسير العربية:
۞ إِنَّ ٱللَّهَ يُدَٰفِعُ عَنِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ خَوَّانٖ كَفُورٍ
38. አላህ ከእነዚያ በእርሱ ካመኑት ላይ ይከላከልላቸዋል። አላህ ከዳተኛንና ውለታ ቢስን ሁሉ አይወድምና።
التفاسير العربية:
 
ترجمة معاني سورة: الحج
فهرس السور رقم الصفحة
 
ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا - فهرس التراجم

ترجمها محمد زين زهر الدين. صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

إغلاق