للإطلاع على الموقع بحلته الجديدة

ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا * - فهرس التراجم

PDF XML CSV Excel API
تنزيل الملفات يتضمن الموافقة على هذه الشروط والسياسات

ترجمة معاني سورة: الحج   آية:
ٱلۡمُلۡكُ يَوۡمَئِذٖ لِّلَّهِ يَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡۚ فَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
56. በዚያ ቀን ንግስናው የአላህ ብቻ ነው:: በመካከላቸውም ይፈርዳል:: እነዚያም ያመኑትና መልካም ስራዎችን የሰሩት በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ናቸው።
التفاسير العربية:
وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا فَأُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٞ مُّهِينٞ
57. እነዚያም የካዱትና በአናቅጻችንም ያስተባበሉት ሁሉ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::
التفاسير العربية:
وَٱلَّذِينَ هَاجَرُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ ثُمَّ قُتِلُوٓاْ أَوۡ مَاتُواْ لَيَرۡزُقَنَّهُمُ ٱللَّهُ رِزۡقًا حَسَنٗاۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهُوَ خَيۡرُ ٱلرَّٰزِقِينَ
58. እነዚያም ለአላህ ሀይማኖት ሲሉ የተሰደዱና ከዚያም ሲታገሉ የተገደሉ ወይም የሞቱ አላህ መልካምን ሲሳይ በእርግጥ ይሰጣቸዋል:: አላህም እርሱ ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው::
التفاسير العربية:
لَيُدۡخِلَنَّهُم مُّدۡخَلٗا يَرۡضَوۡنَهُۥۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَعَلِيمٌ حَلِيمٞ
59. የሚወዱትን መግቢያ ገነትን በእርግጥ ያስገባቸዋል:: አላህም በእርግጥ አዋቂና ታጋሽ ነውና::
التفاسير العربية:
۞ ذَٰلِكَۖ وَمَنۡ عَاقَبَ بِمِثۡلِ مَا عُوقِبَ بِهِۦ ثُمَّ بُغِيَ عَلَيۡهِ لَيَنصُرَنَّهُ ٱللَّهُۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَعَفُوٌّ غَفُورٞ
60. (ነገሩ) ይህ ነው:: ያ በተበደለበት ብጤ (መጠን) የተበቀለና ከዚያ በእርሱ ላይ ግፍ የተዋለበት ሰው አላህ በእርግጥ ይረዳዋል:: አላህ ይቅር ባይና መሓሪ ነውና::
التفاسير العربية:
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ يُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِ وَأَنَّ ٱللَّهَ سَمِيعُۢ بَصِيرٞ
61. ይህ የሆነው አላህ ሌሊትን በቀን ውስጥ የሚያስገባ፤ ቀንንም በሌሊት ውስጥ የሚያስገባ (ቻይ) ፤ ሁሉንም ሰሚ፤ ሁሉንም ተመልካች በመሆኑ ነው።
التفاسير العربية:
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ هُوَ ٱلۡبَٰطِلُ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡكَبِيرُ
62. ይህ የሆነው አላህም ፍፁም እውነት በመሆኑ፤ ከርሱም ሌላ የሚገዙት ነገር ፍጹም ውሸት በመሆኑና አላህም የሁሉ በላይ ታላቅ በመሆኑ ነው::
التفاسير العربية:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَتُصۡبِحُ ٱلۡأَرۡضُ مُخۡضَرَّةًۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَطِيفٌ خَبِيرٞ
63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን ማውረዱንና ከዚያ ምድር የምትለመልም መሆኗን አላየህምን? አላህ ፍጹም ሩህሩህና ውስጠ አዋቂ ነውና::
التفاسير العربية:
لَّهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهُوَ ٱلۡغَنِيُّ ٱلۡحَمِيدُ
64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: አላህ እርሱ ተብቃቂዉና ምስጉኑ ነውና::
التفاسير العربية:
 
ترجمة معاني سورة: الحج
فهرس السور رقم الصفحة
 
ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا - فهرس التراجم

ترجمها محمد زين زهر الدين. صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

إغلاق