للإطلاع على الموقع بحلته الجديدة

ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا * - فهرس التراجم


ترجمة معاني سورة: الأعراف   آية:
قَالَا رَبَّنَا ظَلَمۡنَآ أَنفُسَنَا وَإِن لَّمۡ تَغۡفِرۡ لَنَا وَتَرۡحَمۡنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ
23. «ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን:: ባትምረንና ባታዝንልን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንሆናለን።» አሉ።
التفاسير العربية:
قَالَ ٱهۡبِطُواْ بَعۡضُكُمۡ لِبَعۡضٍ عَدُوّٞۖ وَلَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُسۡتَقَرّٞ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٖ
24. (አላህም) «ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲሆን ከዚህ ዉጡ ወደ ምድር ውረዱ:: ለእናንተም በምድር ላይ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ።» አላቸው።
التفاسير العربية:
قَالَ فِيهَا تَحۡيَوۡنَ وَفِيهَا تَمُوتُونَ وَمِنۡهَا تُخۡرَجُونَ
25. «በእርሷ ላይ ትኖራላችሁ:: በእርሷም ላይ ትሞታላችሁ:: ከእርሷም ውስጥ ትወጣላችሁ።» አላቸው።
التفاسير العربية:
يَٰبَنِيٓ ءَادَمَ قَدۡ أَنزَلۡنَا عَلَيۡكُمۡ لِبَاسٗا يُوَٰرِي سَوۡءَٰتِكُمۡ وَرِيشٗاۖ وَلِبَاسُ ٱلتَّقۡوَىٰ ذَٰلِكَ خَيۡرٞۚ ذَٰلِكَ مِنۡ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ لَعَلَّهُمۡ يَذَّكَّرُونَ
26. የአደም ልጆች ሆይ! ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስና ጌጥን በእርግጥ በእናንተ ላይ አወረድን:: አላህን የመፍራትም ልብስም እርሱ የተሻለ ነው:: ይህ ከአላህ ተዓምራት ነው:: ይገሰጹ ዘንድ አወረደላቸው::
التفاسير العربية:
يَٰبَنِيٓ ءَادَمَ لَا يَفۡتِنَنَّكُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ كَمَآ أَخۡرَجَ أَبَوَيۡكُم مِّنَ ٱلۡجَنَّةِ يَنزِعُ عَنۡهُمَا لِبَاسَهُمَا لِيُرِيَهُمَا سَوۡءَٰتِهِمَآۚ إِنَّهُۥ يَرَىٰكُمۡ هُوَ وَقَبِيلُهُۥ مِنۡ حَيۡثُ لَا تَرَوۡنَهُمۡۗ إِنَّا جَعَلۡنَا ٱلشَّيَٰطِينَ أَوۡلِيَآءَ لِلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ
27. የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣን አባታችሁንና እናታችሁን ሀፍረተ ገላቸውን ሊያሳያቸው ልብሶቻቸውን ከእነርሱ የገፈፋቸው ሲሆን ከገነት እንዳወጣቸው ሁሉ እናንተንም አይሞክራችሁ:: እነሆ እርሱ ከነሰራዊቱ ከማታዩዋቸው ስፍራ ሁነው ያያቹሀልና: እኛ ሰይጣናትን ለእነዚያ ለማያምኑት ወዳጆች አድርገናል::
التفاسير العربية:
وَإِذَا فَعَلُواْ فَٰحِشَةٗ قَالُواْ وَجَدۡنَا عَلَيۡهَآ ءَابَآءَنَا وَٱللَّهُ أَمَرَنَا بِهَاۗ قُلۡ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَأۡمُرُ بِٱلۡفَحۡشَآءِۖ أَتَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ
28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መጥፎንም ሥራ በሠሩ ጊዜ፡- «በእርሷ ላይ አባቶቻችንን አገኘን:: አላህም በእርሷ አዞናል።» ይላሉ። «አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም፤ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?» በላቸው።
التفاسير العربية:
قُلۡ أَمَرَ رَبِّي بِٱلۡقِسۡطِۖ وَأَقِيمُواْ وُجُوهَكُمۡ عِندَ كُلِّ مَسۡجِدٖ وَٱدۡعُوهُ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَۚ كَمَا بَدَأَكُمۡ تَعُودُونَ
29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ በማስተካከል በፍትህ አዘዘ:: በየመስገጃ ቦታ ዘንድም ፊቶቻችሁን እርሱን ለመገዛት አስተካክሉ:: ሃይማኖትንም ለእርሱ ብቻ ፍጹም አድርጋችሁ አምልኩት:: መጀመሪያ እርሱ እንደፈጠራችሁ በመጨረሻም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁና።» በላቸው።
التفاسير العربية:
فَرِيقًا هَدَىٰ وَفَرِيقًا حَقَّ عَلَيۡهِمُ ٱلضَّلَٰلَةُۚ إِنَّهُمُ ٱتَّخَذُواْ ٱلشَّيَٰطِينَ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَيَحۡسَبُونَ أَنَّهُم مُّهۡتَدُونَ
30. ከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ:: ከፊሎቹ ደግሞ በእነርሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል:: እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና:: እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመሩ እንደሆኑ ያስባሉ::
التفاسير العربية:
 
ترجمة معاني سورة: الأعراف
فهرس السور رقم الصفحة
 
ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا - فهرس التراجم

ترجمها محمد زين زهر الدين. صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

إغلاق