للإطلاع على الموقع بحلته الجديدة

ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا * - فهرس التراجم


ترجمة معاني سورة: الأعراف   آية:
وَٱلۡبَلَدُ ٱلطَّيِّبُ يَخۡرُجُ نَبَاتُهُۥ بِإِذۡنِ رَبِّهِۦۖ وَٱلَّذِي خَبُثَ لَا يَخۡرُجُ إِلَّا نَكِدٗاۚ كَذَٰلِكَ نُصَرِّفُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَشۡكُرُونَ
58. መልካሙ አገር በጌታው ፈቃድ በቃዩ ያማረ ሆኖ ይወጣል። ያ መጥፎ የሆነው አገር ደግሞ በቃዩ ደካማ ሆኖ እንጂ አይወጣም:: ልክ እንደዚሁ ለሚያመሰግኑ ህዝቦች ተዓምራትን እናብራራለን።
التفاسير العربية:
لَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ فَقَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓ إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ
59. ኑሕን ወደ ወገኖቹ ላክነው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ለእናንተ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።» አላቸው።
التفاسير العربية:
قَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِهِۦٓ إِنَّا لَنَرَىٰكَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ
60. ከህዝቦቹ መካከል መሪዎቹ «እኛ በግልጽ ስህተት ውስጥ ሆነህ እናይሀለን።» አሉት።
التفاسير العربية:
قَالَ يَٰقَوۡمِ لَيۡسَ بِي ضَلَٰلَةٞ وَلَٰكِنِّي رَسُولٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
61. ኑሕም አለ: «ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም። ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልዕክተኛ ነኝ።
التفاسير العربية:
أُبَلِّغُكُمۡ رِسَٰلَٰتِ رَبِّي وَأَنصَحُ لَكُمۡ وَأَعۡلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ
62. «የጌታዬን መልዕክቶች አደርስላችኋለሁ:: ለናንተም እመክራችኋለሁ:: ከአላህ በኩልም የማታውቁትን አውቃለሁ::
التفاسير العربية:
أَوَعَجِبۡتُمۡ أَن جَآءَكُمۡ ذِكۡرٞ مِّن رَّبِّكُمۡ عَلَىٰ رَجُلٖ مِّنكُمۡ لِيُنذِرَكُمۡ وَلِتَتَّقُواْ وَلَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ
63. «አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከናንተው ጎሳ መካከል በሆነ ሰው ላይ እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ስለመጣላችሁ ትደነቃላችሁን?» አላቸው።
التفاسير العربية:
فَكَذَّبُوهُ فَأَنجَيۡنَٰهُ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥ فِي ٱلۡفُلۡكِ وَأَغۡرَقۡنَا ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَآۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمًا عَمِينَ
64. ወዲያዉም አስተባበሉት:: እርሱንና እነዚያን ከእርሱ ጋር ያሉትንም በታንኳዋ ውስጥ አዳንናቸው:: እነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን ግን በባህር አሰመጥናቸው:: እነርሱ ልበ እውራን ህዝቦች ነበሩና::
التفاسير العربية:
۞ وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمۡ هُودٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ
65. ወደ ዓድ ህዝቦችም ወንድማቸውን ሁድን ላክን። «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: የአላህን ቅጣት አትፈሩምን?» አላቸው።
التفاسير العربية:
قَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦٓ إِنَّا لَنَرَىٰكَ فِي سَفَاهَةٖ وَإِنَّا لَنَظُنُّكَ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ
66. ከህዝቦቹ መካከል መሪዎቹም «እኛ በሞኝነት ላይ ሆነህ እናይሀለን:: እኛ ከውሸተኞቹ ነህ ብለንም እንጠረጥርሀለን።» አሉት።
التفاسير العربية:
قَالَ يَٰقَوۡمِ لَيۡسَ بِي سَفَاهَةٞ وَلَٰكِنِّي رَسُولٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
67. እርሱም አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ሞኝነት የለብኝም:: ግን እኔ ከአለማት ጌታ የተላኩ ነኝ።
التفاسير العربية:
 
ترجمة معاني سورة: الأعراف
فهرس السور رقم الصفحة
 
ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا - فهرس التراجم

ترجمها محمد زين زهر الدين. صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

إغلاق