Check out the new design

আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী * - অনুবাদসমূহৰ সূচীপত্ৰ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

অৰ্থানুবাদ ছুৰা: আল-আম্বীয়া   আয়াত:
قُلۡ إِنَّمَآ أُنذِرُكُم بِٱلۡوَحۡيِۚ وَلَا يَسۡمَعُ ٱلصُّمُّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا مَا يُنذَرُونَ
45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የማስፈራራችሁ በተወረድልኝ ብቻ ነው። ግን ደንቆሮዎች በሚስፈራሩበት ጊዜ ጥሪን አይሰሙም።» በላቸው።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَلَئِن مَّسَّتۡهُمۡ نَفۡحَةٞ مِّنۡ عَذَابِ رَبِّكَ لَيَقُولُنَّ يَٰوَيۡلَنَآ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ
46. ከጌታህ ቅጣትም ወላፈን ብትነካቸው «ዋ ጥፋታችን! እኛ በዳዮች ነበርን።» ይላሉ።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَنَضَعُ ٱلۡمَوَٰزِينَ ٱلۡقِسۡطَ لِيَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ فَلَا تُظۡلَمُ نَفۡسٞ شَيۡـٔٗاۖ وَإِن كَانَ مِثۡقَالَ حَبَّةٖ مِّنۡ خَرۡدَلٍ أَتَيۡنَا بِهَاۗ وَكَفَىٰ بِنَا حَٰسِبِينَ
47.በትንሳኤ ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን:: ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም:: ስራው የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢሆንም እርሷን እናመጣታለን:: ተቆጣጣሪነትም በእኛ በቃ::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ ٱلۡفُرۡقَانَ وَضِيَآءٗ وَذِكۡرٗا لِّلۡمُتَّقِينَ
48. ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንን ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
ٱلَّذِينَ يَخۡشَوۡنَ رَبَّهُم بِٱلۡغَيۡبِ وَهُم مِّنَ ٱلسَّاعَةِ مُشۡفِقُونَ
49. ለእነዚያ ጌታቸውን በሩቅ ለሚፈሩት እነርሱም ከሰዓቲቱ ተጨናቂዎች ለሆኑት መገሰጫን ሰጠን::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَهَٰذَا ذِكۡرٞ مُّبَارَكٌ أَنزَلۡنَٰهُۚ أَفَأَنتُمۡ لَهُۥ مُنكِرُونَ
50.ይህም (ቁርኣን) ያወረድነው የኾነ ብሩክ መገሰጫ ነው፡ ታዲያ እናንተ ለእርሱ ከሓዲያን ናችሁን?
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
۞ وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَآ إِبۡرَٰهِيمَ رُشۡدَهُۥ مِن قَبۡلُ وَكُنَّا بِهِۦ عَٰلِمِينَ
51. ለኢብራሂምም ከዚያ በፊት ቅን መንገዱን በእርግጥ ሰጠነው:: እኛም በእርሱ ተገቢነት አዋቂዎች ነበርን::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
إِذۡ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦ مَا هَٰذِهِ ٱلتَّمَاثِيلُ ٱلَّتِيٓ أَنتُمۡ لَهَا عَٰكِفُونَ
52. ለአባቱና ለህዝቦቹ፡- «ይህቺ ቅርጻ ቅርጽ ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የሆናችኃት ምንድን ናት?» ባለ ጊዜ መራነው።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
قَالُواْ وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا لَهَا عَٰبِدِينَ
53. «አባቶቻችንን ለእርሷ ተገዢዎች ሆነው አገኘን።» አሉት።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
قَالَ لَقَدۡ كُنتُمۡ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُمۡ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ
54. «እናንተም አባቶቻችሁም በእርግጥ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበራችሁ።» አላቸው።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
قَالُوٓاْ أَجِئۡتَنَا بِٱلۡحَقِّ أَمۡ أَنتَ مِنَ ٱللَّٰعِبِينَ
55. «በምሩ መጣህልን? ወይንስ አንተ ከሚቀልዱት ነህ?» አሉት።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
قَالَ بَل رَّبُّكُمۡ رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ ٱلَّذِي فَطَرَهُنَّ وَأَنَا۠ عَلَىٰ ذَٰلِكُم مِّنَ ٱلشَّٰهِدِينَ
56. (እርሱም) አለ: «አይደለም። ጌታችሁ የሰማያትና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው:: እኔም በይሃችሁ ላይ ከመስካሪዎች ነኝ።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَتَٱللَّهِ لَأَكِيدَنَّ أَصۡنَٰمَكُم بَعۡدَ أَن تُوَلُّواْ مُدۡبِرِينَ
57. «በአላህ እምላለሁ ዟሪዎች ሆናችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ጣዖቶቻችሁን ተንኮል እሰራባቸዋለሁ።» አለ።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
 
অৰ্থানুবাদ ছুৰা: আল-আম্বীয়া
ছুৰাৰ তালিকা পৃষ্ঠা নং
 
আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী - অনুবাদসমূহৰ সূচীপত্ৰ

মুহাম্মদ ঝাইন জহৰুদ্দিনৰ অনুবাদ। আফ্ৰিকা একাডেমীৰ পৰা প্ৰকাশিত।

বন্ধ