Check out the new design

আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী * - অনুবাদসমূহৰ সূচীপত্ৰ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

অৰ্থানুবাদ ছুৰা: আল-আম্বীয়া   আয়াত:
وَمِنَ ٱلشَّيَٰطِينِ مَن يَغُوصُونَ لَهُۥ وَيَعۡمَلُونَ عَمَلٗا دُونَ ذَٰلِكَۖ وَكُنَّا لَهُمۡ حَٰفِظِينَ
82.ከሰይጣናትም ለእርሱ (ሉልን ለማውጣት) የሚጠልሙንና ከዚያ ሌላ ያለን ስራ የሚሰሩን ገራንለት፤ ለእነርሱም ተጠባባቂዎች ነበርን::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
۞ وَأَيُّوبَ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّي مَسَّنِيَ ٱلضُّرُّ وَأَنتَ أَرۡحَمُ ٱلرَّٰحِمِينَ
83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ:: አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ።» ሲል በተጣራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ فَكَشَفۡنَا مَا بِهِۦ مِن ضُرّٖۖ وَءَاتَيۡنَٰهُ أَهۡلَهُۥ وَمِثۡلَهُم مَّعَهُمۡ رَحۡمَةٗ مِّنۡ عِندِنَا وَذِكۡرَىٰ لِلۡعَٰبِدِينَ
84. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፤ ከጉዳትም በእርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ አስወገድን:: ቤተሰቦቹንም ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ከእኛ ዘንድ ለችሮታና ለተገዢዎች ለማስገንዘብ ሰጠነው::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَإِسۡمَٰعِيلَ وَإِدۡرِيسَ وَذَا ٱلۡكِفۡلِۖ كُلّٞ مِّنَ ٱلصَّٰبِرِينَ
85. ኢስማዒልንም፤ ኢድሪስንም፤ ዙልኪፍልንም፤ አስታውስ:: ሁሉም ከታጋሾች ናቸው::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَأَدۡخَلۡنَٰهُمۡ فِي رَحۡمَتِنَآۖ إِنَّهُم مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
86. በችሮታችንም ውስጥ አስገባናቸው:: እነርሱ ከመልካሞቹ ናቸውና::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَذَا ٱلنُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَٰضِبٗا فَظَنَّ أَن لَّن نَّقۡدِرَ عَلَيۡهِ فَنَادَىٰ فِي ٱلظُّلُمَٰتِ أَن لَّآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنتَ سُبۡحَٰنَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በሄደ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መሆናችንን ጠረጠረ:: ዓሳም ዋጠው:: በጨለማዎችም ውስጥ ሆኖ «ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም ጥራት ይገባህ:: እኔ በእርግጥ ከበዳዮች ነበርኩ።» በማለት ተጣራ።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ وَنَجَّيۡنَٰهُ مِنَ ٱلۡغَمِّۚ وَكَذَٰلِكَ نُـۨجِي ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
88. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው:: ከጭንቅም አዳነው:: ልክ እንደዚሁም ምዕምናንን እናድናለን::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَزَكَرِيَّآ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥ رَبِّ لَا تَذَرۡنِي فَرۡدٗا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡوَٰرِثِينَ
89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ዘከሪያንም «ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ:: አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ።» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ አስታውስ።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ وَوَهَبۡنَا لَهُۥ يَحۡيَىٰ وَأَصۡلَحۡنَا لَهُۥ زَوۡجَهُۥٓۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ يُسَٰرِعُونَ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِ وَيَدۡعُونَنَا رَغَبٗا وَرَهَبٗاۖ وَكَانُواْ لَنَا خَٰشِعِينَ
90. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው:: ለእርሱም የህያን ሰጠነው:: ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት:: እነርሱ በበጎ ስራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ሆነው የሚለምኑንም ነበሩ:: ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
 
অৰ্থানুবাদ ছুৰা: আল-আম্বীয়া
ছুৰাৰ তালিকা পৃষ্ঠা নং
 
আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী - অনুবাদসমূহৰ সূচীপত্ৰ

মুহাম্মদ ঝাইন জহৰুদ্দিনৰ অনুবাদ। আফ্ৰিকা একাডেমীৰ পৰা প্ৰকাশিত।

বন্ধ