কুরআনুল কারীমের অর্থসমূহের অনুবাদ - الترجمة الأمهرية - زين * - অনুবাদসমূহের সূচী


অর্থসমূহের অনুবাদ সূরা: সূরা আস-সাজদাহ   আয়াত:

ሱረቱ አስ ሰጅደህ

الٓمٓ
1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም፤
আরবি তাফসীরসমূহ:
تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ لَا رَيۡبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
2. የመጽሐፉ መወረድ ጥርጥር የለበትም:: የወረደዉም ከዓለማቱ ጌታ ነው::
আরবি তাফসীরসমূহ:
أَمۡ يَقُولُونَ ٱفۡتَرَىٰهُۚ بَلۡ هُوَ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَ لِتُنذِرَ قَوۡمٗا مَّآ أَتَىٰهُم مِّن نَّذِيرٖ مِّن قَبۡلِكَ لَعَلَّهُمۡ يَهۡتَدُونَ
3. ይልቁንም «ቀጠፈው» ይላሉን? አይደለም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው:: በእርሱ ካንተ በፊት ከአስፈራሪ ነቢይ ያልመጣባቸውን ሕዝቦች በእርሱ ልታስፈራራበት ያወረደልህ ነው:: እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና::
আরবি তাফসীরসমূহ:
ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ مَا لَكُم مِّن دُونِهِۦ مِن وَلِيّٖ وَلَا شَفِيعٍۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُونَ
4. አላህ ያ! ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ከዚያም ለክብሩ በሚስማማ መልኩ በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ ነው:: ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ወዳጅም አማላጅም ምንም የላችሁም:: አትገሰጹምን?
আরবি তাফসীরসমূহ:
يُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ إِلَى ٱلۡأَرۡضِ ثُمَّ يَعۡرُجُ إِلَيۡهِ فِي يَوۡمٖ كَانَ مِقۡدَارُهُۥٓ أَلۡفَ سَنَةٖ مِّمَّا تَعُدُّونَ
5. ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፤ ከዚያም ከምትቆጥሩት (ዘመን) ልኩ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ ይወጣል::
আরবি তাফসীরসমূহ:
ذَٰلِكَ عَٰلِمُ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
6. ይህንን ያደረገው ሩቁንም ቅርቡንም ሁሉ አዋቂው፤ ሁሉን አሸናፊና አዛኙ ጌታ ነው::
আরবি তাফসীরসমূহ:
ٱلَّذِيٓ أَحۡسَنَ كُلَّ شَيۡءٍ خَلَقَهُۥۖ وَبَدَأَ خَلۡقَ ٱلۡإِنسَٰنِ مِن طِينٖ
7. ያ የፈጠረውን ነገር ሁሉ ያሳመረው:: የሰውንም ፍጥረት ከጭቃ የጀመረው ነው::
আরবি তাফসীরসমূহ:
ثُمَّ جَعَلَ نَسۡلَهُۥ مِن سُلَٰلَةٖ مِّن مَّآءٖ مَّهِينٖ
8. ከዚያም ዘሮቹን ከተንጣለለ ከደካማ ውሃ የፈጠረ ነው::
আরবি তাফসীরসমূহ:
ثُمَّ سَوَّىٰهُ وَنَفَخَ فِيهِ مِن رُّوحِهِۦۖ وَجَعَلَ لَكُمُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَٱلۡأَفۡـِٔدَةَۚ قَلِيلٗا مَّا تَشۡكُرُونَ
9. ከዚያም ቅርጹን አስተካከለው:: በእርሱ ውስጥም ከመንፈሱ ነፍስ ዘራበት:: ለናንተም ጆሮዎችን ዓይኖችንና ልቦችንም አደረገላችሁ። በጣም ጥቂትን ብቻ ታመሰግናላችሁ።
আরবি তাফসীরসমূহ:
وَقَالُوٓاْ أَءِذَا ضَلَلۡنَا فِي ٱلۡأَرۡضِ أَءِنَّا لَفِي خَلۡقٖ جَدِيدِۭۚ بَلۡ هُم بِلِقَآءِ رَبِّهِمۡ كَٰفِرُونَ
10. «በምድርም ውስጥ በስብሰን በጠፋን ጊዜ እኛ በአዲስ መፈጠር ውስጥ እንሆናለን?» አሉ:: በእውነቱ እነርሱ በጌታቸው መገናኘት ከሓዲያን ናቸው::
আরবি তাফসীরসমূহ:
۞ قُلۡ يَتَوَفَّىٰكُم مَّلَكُ ٱلۡمَوۡتِ ٱلَّذِي وُكِّلَ بِكُمۡ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمۡ تُرۡجَعُونَ
11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእናንተ ላይ የተወከለው መልአከ ሞት ይገድላችኋል:: ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ።» በላቸው።
আরবি তাফসীরসমূহ:
وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذِ ٱلۡمُجۡرِمُونَ نَاكِسُواْ رُءُوسِهِمۡ عِندَ رَبِّهِمۡ رَبَّنَآ أَبۡصَرۡنَا وَسَمِعۡنَا فَٱرۡجِعۡنَا نَعۡمَلۡ صَٰلِحًا إِنَّا مُوقِنُونَ
12. አመጸኞችም በጌታቸው ዘንድ ራሶቻቸውን ያቀረቀሩ ሆነው፡‐ «ጌታችን ሆይ! አየን። ሰማንም። መልካምን እንሠራለንና (ወደ ምድረ ዓለም) መልሰን እኛ አረጋጋጮች ነን» የሚሉ ሲሆኑ ብታይ ኖሮ( አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)።
আরবি তাফসীরসমূহ:
وَلَوۡ شِئۡنَا لَأٓتَيۡنَا كُلَّ نَفۡسٍ هُدَىٰهَا وَلَٰكِنۡ حَقَّ ٱلۡقَوۡلُ مِنِّي لَأَمۡلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ ٱلۡجِنَّةِ وَٱلنَّاسِ أَجۡمَعِينَ
13 በሻንም ኖሮ ነፍስን ሁሉ ቅንነቷን(እምነቷን) በሰጠናት ነበር:: ግን ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች የተሰበሰቡ ሆነው በእርግጥ እሞላለሁ ማለት ቃሉ ከእኔ ተረጋግጧል::
আরবি তাফসীরসমূহ:
فَذُوقُواْ بِمَا نَسِيتُمۡ لِقَآءَ يَوۡمِكُمۡ هَٰذَآ إِنَّا نَسِينَٰكُمۡۖ وَذُوقُواْ عَذَابَ ٱلۡخُلۡدِ بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
14. ይህንንም ቀናችሁን መገናኘትን በመርሳታችሁ ምክንያት ቅጣትን ቅመሱ! እኛ ተውናችሁ። ትሰሩት በነበራችሁትም ጥፋት ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ ይባላሉ::
আরবি তাফসীরসমূহ:
إِنَّمَا يُؤۡمِنُ بِـَٔايَٰتِنَا ٱلَّذِينَ إِذَا ذُكِّرُواْ بِهَا خَرُّواْۤ سُجَّدٗاۤ وَسَبَّحُواْ بِحَمۡدِ رَبِّهِمۡ وَهُمۡ لَا يَسۡتَكۡبِرُونَ۩
15. በአናቅጻችን የሚያምኑት እነዚያ በእርሷ በተገሰጹ ጊዜ ሰጋጆች ሆነው የሚወድቁትና እነርሱም የማይኮሩ ሆነው በጌታቸው ምስጋና (ተጎናጽፈው) የሚያወድሱት ሰዎች ብቻ ናቸው። {1}
{1} እዚህጋ ሱጁዱትላዋ (የንባብ ሱጁድ) መድረግ ያስፈልጋል። በሶላት ውስጥም ከሶላት ውጪም መድረጉ ይወደዳል።
আরবি তাফসীরসমূহ:
تَتَجَافَىٰ جُنُوبُهُمۡ عَنِ ٱلۡمَضَاجِعِ يَدۡعُونَ رَبَّهُمۡ خَوۡفٗا وَطَمَعٗا وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ
16. ጌታቸውን ለመፍራትና ለመከጀል የሚጠሩት ሆነው ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ቦታዎቻቸው ይርቃሉ:: ከሰጠናቸዉም ጸጋ ይለግሳሉ::
আরবি তাফসীরসমূহ:
فَلَا تَعۡلَمُ نَفۡسٞ مَّآ أُخۡفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعۡيُنٖ جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
17. ይሰሩት በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም::
আরবি তাফসীরসমূহ:
أَفَمَن كَانَ مُؤۡمِنٗا كَمَن كَانَ فَاسِقٗاۚ لَّا يَسۡتَوُۥنَ
18. አማኝ የሆነ ሰው አመጸኛ እንደሆነ ሰው ነውን? አይስተካከሉም::
আরবি তাফসীরসমূহ:
أَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَلَهُمۡ جَنَّٰتُ ٱلۡمَأۡوَىٰ نُزُلَۢا بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
19. እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሰሩማ ለነሱ ይሰሩት በነበሩት ምክንያት መስተንግዶ ሲሆኑ መኖሪያ ገነቶች አሏቸው::
আরবি তাফসীরসমূহ:
وَأَمَّا ٱلَّذِينَ فَسَقُواْ فَمَأۡوَىٰهُمُ ٱلنَّارُۖ كُلَّمَآ أَرَادُوٓاْ أَن يَخۡرُجُواْ مِنۡهَآ أُعِيدُواْ فِيهَا وَقِيلَ لَهُمۡ ذُوقُواْ عَذَابَ ٱلنَّارِ ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ
20. እነዚያ ያመጹትማ መኖሪያቸው እሳት ናት:: ከእርሷ መውጣትን በፈለጉ ቁጥር በእርሷ ውስጥ ይመለሳሉ ለእነርሱም «ያንን በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ» ይባላሉ።
আরবি তাফসীরসমূহ:
وَلَنُذِيقَنَّهُم مِّنَ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡأَدۡنَىٰ دُونَ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡأَكۡبَرِ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ
21. ይመለሱ ዘንድ ከትልቁ ቅጣት በፊት (በዚህ ዓለም) ትንሹን ቅጣት በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን::
আরবি তাফসীরসমূহ:
وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن ذُكِّرَ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِۦ ثُمَّ أَعۡرَضَ عَنۡهَآۚ إِنَّا مِنَ ٱلۡمُجۡرِمِينَ مُنتَقِمُونَ
22. በጌታዉም አናቅጽ ከተገሰጸና ከዚያም ከተዋት ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው? (የለም) እኛ ከተንኮለኞቹ ሁሉ ተበቃዮች ነን::
আরবি তাফসীরসমূহ:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ فَلَا تَكُن فِي مِرۡيَةٖ مِّن لِّقَآئِهِۦۖ وَجَعَلۡنَٰهُ هُدٗى لِّبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
23.ሙሳን መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: ለኢስራኢል ልጆችም መሪ አደረግነው::
আরবি তাফসীরসমূহ:
وَجَعَلۡنَا مِنۡهُمۡ أَئِمَّةٗ يَهۡدُونَ بِأَمۡرِنَا لَمَّا صَبَرُواْۖ وَكَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يُوقِنُونَ
24. በታገሱና በተዓምራታችን የሚያረጋግጡ በሆኑም ጊዜ ከእነርሱ በትዕዛዛችን የሚመሩ መሪዎችን አደረግን::
আরবি তাফসীরসমূহ:
إِنَّ رَبَّكَ هُوَ يَفۡصِلُ بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ
25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በዚያ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ሁሉ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል::
আরবি তাফসীরসমূহ:
أَوَلَمۡ يَهۡدِ لَهُمۡ كَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِن قَبۡلِهِم مِّنَ ٱلۡقُرُونِ يَمۡشُونَ فِي مَسَٰكِنِهِمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٍۚ أَفَلَا يَسۡمَعُونَ
26. ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ብዙዎችን ያጠፋን መሆናችን በመኖሪያዎቻቸው የሚሄዱ ሲሆኑ እነርሱ አልተገለጸላቸዉምን? በዚህ ውስጥ አያሌ ምልክቶች አሉበት:: አይሰሙምን?
আরবি তাফসীরসমূহ:
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّا نَسُوقُ ٱلۡمَآءَ إِلَى ٱلۡأَرۡضِ ٱلۡجُرُزِ فَنُخۡرِجُ بِهِۦ زَرۡعٗا تَأۡكُلُ مِنۡهُ أَنۡعَٰمُهُمۡ وَأَنفُسُهُمۡۚ أَفَلَا يُبۡصِرُونَ
27. እኛ ውሃን ወደ ደረቅ ምድር የምንነዳ እንስሶቻቸውና ነፍሶቻቸው ከእርሱ የሚበሉለትንም አዝመራ በእርሱ የምናወጣ መሆናችንን አያዩምን? አይመለከቱምን?
আরবি তাফসীরসমূহ:
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡفَتۡحُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
28. «ከእውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ፍርድ መቼ ነው።» ይላሉ።
আরবি তাফসীরসমূহ:
قُلۡ يَوۡمَ ٱلۡفَتۡحِ لَا يَنفَعُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِيمَٰنُهُمۡ وَلَا هُمۡ يُنظَرُونَ
29. «በፍርዱ ቀን እነዚያን የካዱትን ሰዎች እምነታቸው አይጠቅማቸዉም:: እነርሱም ጊዜን አይሰጡም።» በላቸው።
আরবি তাফসীরসমূহ:
فَأَعۡرِضۡ عَنۡهُمۡ وَٱنتَظِرۡ إِنَّهُم مُّنتَظِرُونَ
30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው:: ተጠባበቅም:: እነርሱም ተጠባባቂዎች ናቸውና::
আরবি তাফসীরসমূহ:
 
অর্থসমূহের অনুবাদ সূরা: সূরা আস-সাজদাহ
সূরাসমূহের সূচী পৃষ্ঠার নাম্বার
 
কুরআনুল কারীমের অর্থসমূহের অনুবাদ - الترجمة الأمهرية - زين - অনুবাদসমূহের সূচী

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

বন্ধ