Check out the new design

Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija * - Sadržaj prijevodā


Prijevod značenja Sura: Nuh   Ajet:

ኑህ

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦٓ أَنۡ أَنذِرۡ قَوۡمَكَ مِن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
1. እኛ ኑህን ህዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ወገኖቹ ላክነው::
Tefsiri na arapskom jeziku:
قَالَ يَٰقَوۡمِ إِنِّي لَكُمۡ نَذِيرٞ مُّبِينٌ
2. እርሱም አለ፡- «ሀዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ (የቸገራችሁን) ገላጭ የሆንኩ አስጠንቃቂ ነኝ::
Tefsiri na arapskom jeziku:
أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَٱتَّقُوهُ وَأَطِيعُونِ
3. «አላህን ተገዙት፡-ፍሩት፤ እኔንም ታዘዙኝ በማለት አስጠንቃቂ ነኝ።
Tefsiri na arapskom jeziku:
يَغۡفِرۡ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمۡ وَيُؤَخِّرۡكُمۡ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمًّىۚ إِنَّ أَجَلَ ٱللَّهِ إِذَا جَآءَ لَا يُؤَخَّرُۚ لَوۡ كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
4. «ለእናንተ ኃጢአታችሁን ይምራል እስከ ተወሰነ ጊዜም ያቆያችኋል:: አላህ የወሰነው ጊዜ በመጣ ወቅት ግን ለአፍታም አይቆይም:: በትክክል የምታውቁት ብትሆኑ ኖሮ በታዘዛችሁ ነበር።»
Tefsiri na arapskom jeziku:
قَالَ رَبِّ إِنِّي دَعَوۡتُ قَوۡمِي لَيۡلٗا وَنَهَارٗا
5. ስለተቃወሙትም «ጌታየ ሆይ! እኔ በሌሊትም ሆነ በቀን ህዝቦቼን ጠራሁ።
Tefsiri na arapskom jeziku:
فَلَمۡ يَزِدۡهُمۡ دُعَآءِيٓ إِلَّا فِرَارٗا
6. «ጥሪየም ይበልጥ መሸሽን እንጂ ሌላ አልጨመረላቸዉም።
Tefsiri na arapskom jeziku:
وَإِنِّي كُلَّمَا دَعَوۡتُهُمۡ لِتَغۡفِرَ لَهُمۡ جَعَلُوٓاْ أَصَٰبِعَهُمۡ فِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَٱسۡتَغۡشَوۡاْ ثِيَابَهُمۡ وَأَصَرُّواْ وَٱسۡتَكۡبَرُواْ ٱسۡتِكۡبَارٗا
7. «እኔም ለእነርሱ ትምራቸው ዘንድ ወደ እምነት በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ:: ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ:: በመጥፎ ስራቸው ላይ ዘወተሩም:: ያለ ልክ መኩራትንም ኮሩ::
Tefsiri na arapskom jeziku:
ثُمَّ إِنِّي دَعَوۡتُهُمۡ جِهَارٗا
8. «ከዚያ እኔ በግልጽ ጠራኋቸው።
Tefsiri na arapskom jeziku:
ثُمَّ إِنِّيٓ أَعۡلَنتُ لَهُمۡ وَأَسۡرَرۡتُ لَهُمۡ إِسۡرَارٗا
9. «ከዚያ እኔ ለእነርሱ ጥሪየን ይፋ አደረኩ:: ለእነርሱ መመስጠርን መሰጠርኩም» አለ።
Tefsiri na arapskom jeziku:
فَقُلۡتُ ٱسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّكُمۡ إِنَّهُۥ كَانَ غَفَّارٗا
10. «እንዲህም አልኩ: ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት:: እርሱም በጣም መሀሪ ነውና።
Tefsiri na arapskom jeziku:
 
Prijevod značenja Sura: Nuh
Indeks sura Broj stranice
 
Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija - Sadržaj prijevodā

Prijevod je uradio Muhammed Zejn Zehruddin. Izdavač: Afrička akademija.

Zatvaranje