Check out the new design

Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija * - Sadržaj prijevodā


Prijevod značenja Sura: El-Enfal   Ajet:
۞ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَا غَنِمۡتُم مِّن شَيۡءٖ فَأَنَّ لِلَّهِ خُمُسَهُۥ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِ إِن كُنتُمۡ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ وَمَآ أَنزَلۡنَا عَلَىٰ عَبۡدِنَا يَوۡمَ ٱلۡفُرۡقَانِ يَوۡمَ ٱلۡتَقَى ٱلۡجَمۡعَانِۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ
41.(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከማንኛዉም ነገር በጦርነት ከካሓዲያን የማረካችሁትም ሁሉ አንድ አምስተኛው ለአላህና ለመልዕክተኛው፤ ለነብዩ የዝምድና ባለቤቶች፤ ለየቲሞች፤ ለሚስኪኖች፤ ለመንገደኞችም የተገባ መሆኑን እወቁ:: በአላህና በዚያም እውነትና ውሸት በተለየበት ቀን ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙበት (በበድር) ቀን ባገልጋያችን ላይ ባወረድነውም የምታምኑ እንደ ሆናችሁ ይህንን እወቁ:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።
Tefsiri na arapskom jeziku:
إِذۡ أَنتُم بِٱلۡعُدۡوَةِ ٱلدُّنۡيَا وَهُم بِٱلۡعُدۡوَةِ ٱلۡقُصۡوَىٰ وَٱلرَّكۡبُ أَسۡفَلَ مِنكُمۡۚ وَلَوۡ تَوَاعَدتُّمۡ لَٱخۡتَلَفۡتُمۡ فِي ٱلۡمِيعَٰدِ وَلَٰكِن لِّيَقۡضِيَ ٱللَّهُ أَمۡرٗا كَانَ مَفۡعُولٗا لِّيَهۡلِكَ مَنۡ هَلَكَ عَنۢ بَيِّنَةٖ وَيَحۡيَىٰ مَنۡ حَيَّ عَنۢ بَيِّنَةٖۗ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَسَمِيعٌ عَلِيمٌ
42. (ሙስሊሞች ሆይ!) እናንተ በቅርቢቱ ዳርቻ ሁናችሁ እነርሱ ደግሞ በሩቂቱ ዳርቻ ሆነው የነጋዴዎቹም ቡድን ከናንተ በታች ሲሆኑ በሰፈራችሁ ጊዜ ያደረግንላችሁን አስታውሱ:: በተቃጠራችሁም ኖሮ ግን በቀጠሮው በተለያያችሁ ነበር:: ግን አላህ ሊሠራው የሚገባውን ነገር ሊፈጽምና የሚጠፋም ከአስረጅ መድረስ በኋላ እንዲጠፋ፤ ሕያው የሚሆንም ከአስረጅ መድረስ በኋላ ሕያው እንዲሆን ያለቀጠሮ አጋጠማችሁ:: አላህ በእርግጥ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና::
Tefsiri na arapskom jeziku:
إِذۡ يُرِيكَهُمُ ٱللَّهُ فِي مَنَامِكَ قَلِيلٗاۖ وَلَوۡ أَرَىٰكَهُمۡ كَثِيرٗا لَّفَشِلۡتُمۡ وَلَتَنَٰزَعۡتُمۡ فِي ٱلۡأَمۡرِ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ سَلَّمَۚ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሕልምህ እነርሱን ጥቂት አድርጎ ባሳየህ ጊዜ አስታውስ:: እነርሱን ብዙ አድርጎ ባሳየህም ኖሮ በፈራችሁና በነገሩ በተጨቃጨቃችሁ ነበር ግን አላህ አዳናችሁ:: እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለን ሁሉ አዋቂ ነውና::
Tefsiri na arapskom jeziku:
وَإِذۡ يُرِيكُمُوهُمۡ إِذِ ٱلۡتَقَيۡتُمۡ فِيٓ أَعۡيُنِكُمۡ قَلِيلٗا وَيُقَلِّلُكُمۡ فِيٓ أَعۡيُنِهِمۡ لِيَقۡضِيَ ٱللَّهُ أَمۡرٗا كَانَ مَفۡعُولٗاۗ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ
44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህም ሊሠራው የሚገባን ነገር ይፈጽም ዘንድ በተጋጠማችሁ ጊዜ እነርሱን በዓይኖቻችሁ ጥቂት አድርጎ ያሳያችሁንና በዓይኖቻቸውም ላይ ያሳነሳችሁን (አስታውሱ)፡፡ ነገሮቹም ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ፡፡
Tefsiri na arapskom jeziku:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا لَقِيتُمۡ فِئَةٗ فَٱثۡبُتُواْ وَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ كَثِيرٗا لَّعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ
45. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሰራዊትን በገጠማችሁ ጊዜ እርጉ (መክቱ):: አላህንም በብዙው አውሱ:: በእርግጥ ትድናላችሁና::
Tefsiri na arapskom jeziku:
 
Prijevod značenja Sura: El-Enfal
Indeks sura Broj stranice
 
Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija - Sadržaj prijevodā

Prijevod je uradio Muhammed Zejn Zehruddin. Izdavač: Afrička akademija.

Zatvaranje