Check out the new design

Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África * - Índice de traducciones


Traducción de significados Capítulo: Al-Shu'araa   Versículo:
مَآ أَغۡنَىٰ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يُمَتَّعُونَ
207. ይጣቀሙበት የነበሩት ሁሉ ከእነርሱ ምንም አያብቃቃቸዉም::
Las Exégesis Árabes:
وَمَآ أَهۡلَكۡنَا مِن قَرۡيَةٍ إِلَّا لَهَا مُنذِرُونَ
208. አንዲትንም ከተማ ለእርሷ አስፈራሪዎች ያሏት (እና ያስተባበለች) ሆና እንጂ አላጠፋንም::
Las Exégesis Árabes:
ذِكۡرَىٰ وَمَا كُنَّا ظَٰلِمِينَ
209. ይህች ግሣጼ ናት:: በዳዮችም አልነበርንም::
Las Exégesis Árabes:
وَمَا تَنَزَّلَتۡ بِهِ ٱلشَّيَٰطِينُ
210. ሰይጣናትም እርሱን ቁርኣንን አላወረዱትም::
Las Exégesis Árabes:
وَمَا يَنۢبَغِي لَهُمۡ وَمَا يَسۡتَطِيعُونَ
211. ለእነርሱም አይገባቸዉም፤ አይችሉምም::
Las Exégesis Árabes:
إِنَّهُمۡ عَنِ ٱلسَّمۡعِ لَمَعۡزُولُونَ
212. እነርሱ የመላዕክትን ንግግር ከመስማት የተከለከሉ ናቸው።
Las Exégesis Árabes:
فَلَا تَدۡعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُعَذَّبِينَ
213. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትገዛ:: ከሚቀጡት ትሆናለህና::
Las Exégesis Árabes:
وَأَنذِرۡ عَشِيرَتَكَ ٱلۡأَقۡرَبِينَ
214. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቅርቦች ዘመዶችህንም አስጠንቅቅ::
Las Exégesis Árabes:
وَٱخۡفِضۡ جَنَاحَكَ لِمَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
215. (ሙሐመድ ሆይ!) ከምዕምናንም ለተከተሉህ ሰዎች ክንፍህን ዝቅ አድርግ ልዝብ ሁን::
Las Exégesis Árabes:
فَإِنۡ عَصَوۡكَ فَقُلۡ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تَعۡمَلُونَ
216. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንቢ ካሉህ «እኔ ከምትሰሩት ወንጀል ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው።
Las Exégesis Árabes:
وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱلۡعَزِيزِ ٱلرَّحِيمِ
217. (ሙሐመድ ሆይ!) አሸናፊና አዛኝ በሆነው ጌታህ ላይም ተጠጋ::
Las Exégesis Árabes:
ٱلَّذِي يَرَىٰكَ حِينَ تَقُومُ
218. በዚያ ለሶላት በምትቆም ጊዜ በሚያይህ::
Las Exégesis Árabes:
وَتَقَلُّبَكَ فِي ٱلسَّٰجِدِينَ
219. በሰጋጆች ውስጥ መዘዋወርህንም (በሚያየው ጌታህ ላይ ተጠጋ::)
Las Exégesis Árabes:
إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
220. እነሆ እርሱ (አላህ) ሁሉ ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና።
Las Exégesis Árabes:
هَلۡ أُنَبِّئُكُمۡ عَلَىٰ مَن تَنَزَّلُ ٱلشَّيَٰطِينُ
221. ሰይጣናት በማን ላይ እንደሚወርዱ ልንገራችሁን?
Las Exégesis Árabes:
تَنَزَّلُ عَلَىٰ كُلِّ أَفَّاكٍ أَثِيمٖ
222. በውሸታም ኃጢአተኛ ሁሉ ላይ ይወርዳሉ::
Las Exégesis Árabes:
يُلۡقُونَ ٱلسَّمۡعَ وَأَكۡثَرُهُمۡ كَٰذِبُونَ
223. የሰሙትን ወደ ጠንቋዮች ይጥላሉ:: አብዛኞቻቸዉም ውሸታሞች ናቸው::
Las Exégesis Árabes:
وَٱلشُّعَرَآءُ يَتَّبِعُهُمُ ٱلۡغَاوُۥنَ
224. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎች ይከተሏቸዋል::
Las Exégesis Árabes:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّهُمۡ فِي كُلِّ وَادٖ يَهِيمُونَ
225. እነርሱ (በንግግር) ሸለቆ ሁሉ የሚዋልሉ መሆናቸውን አታይምን?
Las Exégesis Árabes:
وَأَنَّهُمۡ يَقُولُونَ مَا لَا يَفۡعَلُونَ
226. እነርሱም የማይሰሩትን ነገር የሚናገሩ መሆናቸውን አታይምን::
Las Exégesis Árabes:
إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَذَكَرُواْ ٱللَّهَ كَثِيرٗا وَٱنتَصَرُواْ مِنۢ بَعۡدِ مَا ظُلِمُواْۗ وَسَيَعۡلَمُ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ أَيَّ مُنقَلَبٖ يَنقَلِبُونَ
227. እነዚያ ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ አላህን በብዛት ያወሱ ከተበደሉም በኋላ (በቅኔ) የተከላከሉ ሲቀሩ፤ (እነርሱ አይወቀሱም)። እነዚያም የበደሉ ከሞቱ በኋላ እንዴት ያለን መመለስ እንደሚመለሱ በእርግጥ ያውቃሉ::
Las Exégesis Árabes:
 
Traducción de significados Capítulo: Al-Shu'araa
Índice de Capítulos Número de página
 
Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África - Índice de traducciones

Traducida por Muhammad Zain Zahr Ad-Din. Publicada por la Academia de África.

Cerrar