Check out the new design

Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África * - Índice de traducciones

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Traducción de significados Capítulo: Al-Shu'araa   Versículo:
فَلَمَّا تَرَٰٓءَا ٱلۡجَمۡعَانِ قَالَ أَصۡحَٰبُ مُوسَىٰٓ إِنَّا لَمُدۡرَكُونَ
61. ሁለቱ ቡድኖችም በተያዩ ጊዜ የሙሳ ጓዶች «እኛ (የፈርዖን ሰዎች) የሚደርሱብን ነን።» አሉ።
Las Exégesis Árabes:
قَالَ كَلَّآۖ إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهۡدِينِ
62. ሙሳ «በፍፁም! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው። በእርግጥ ይመራኛል።» አለ።
Las Exégesis Árabes:
فَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنِ ٱضۡرِب بِّعَصَاكَ ٱلۡبَحۡرَۖ فَٱنفَلَقَ فَكَانَ كُلُّ فِرۡقٖ كَٱلطَّوۡدِ ٱلۡعَظِيمِ
63. ወደ ሙሳም «ባህሩን በበትርህ ምታው።» ስንል ላክንበት:: ከዚያ መታውና ተከፈለ፤ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ሆነ::
Las Exégesis Árabes:
وَأَزۡلَفۡنَا ثَمَّ ٱلۡأٓخَرِينَ
64. እዚያም ዘንድ ሌሎችን አቀረብን::
Las Exégesis Árabes:
وَأَنجَيۡنَا مُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُۥٓ أَجۡمَعِينَ
65. ሙሳንና ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም አዳን::
Las Exégesis Árabes:
ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ
66. ከዚያም ሌሎቹን አሰመጥን::
Las Exégesis Árabes:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
67. በዚህ ውስጥ ታላቅ ተዐምር አለበት፤ አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም።
Las Exégesis Árabes:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላህ እርሱ አሸናፊና አዛኝ ነው::
Las Exégesis Árabes:
وَٱتۡلُ عَلَيۡهِمۡ نَبَأَ إِبۡرَٰهِيمَ
69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም (በህዝቦችህ) ላይ የኢብራሂምን ወሬ አንብብላቸው::
Las Exégesis Árabes:
إِذۡ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦ مَا تَعۡبُدُونَ
70. ለአባቱና ለህዝቦቹ «ምንን ትገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ።
Las Exégesis Árabes:
قَالُواْ نَعۡبُدُ أَصۡنَامٗا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ
71. «ጣኦታትን እንገዛለን:: እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን።» አሉ።
Las Exégesis Árabes:
قَالَ هَلۡ يَسۡمَعُونَكُمۡ إِذۡ تَدۡعُونَ
72. ኢብራሂም አለ፡- «በጠራችኋቸው ጊዜ ይሰሟችኋልን?
Las Exégesis Árabes:
أَوۡ يَنفَعُونَكُمۡ أَوۡ يَضُرُّونَ
73. «ወይስ ይጠቅሟችኋልን? ወይስ ይጎዷችኋልን?»
Las Exégesis Árabes:
قَالُواْ بَلۡ وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا كَذَٰلِكَ يَفۡعَلُونَ
74. «የለም! ነገር ግን አባቶቻችን ልክ እንደዚሁ ሲሰሩ አገኘን(ና እኛም እነርሱን እንከተላለን።») አሉት።
Las Exégesis Árabes:
قَالَ أَفَرَءَيۡتُم مَّا كُنتُمۡ تَعۡبُدُونَ
75. እርሱም አለ: «ትገዙት የነበራችሁትን አስተዋላችሁን?
Las Exégesis Árabes:
أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُمُ ٱلۡأَقۡدَمُونَ
76. «እናንተም የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁም እየተገዛችሁት ያለውን።
Las Exégesis Árabes:
فَإِنَّهُمۡ عَدُوّٞ لِّيٓ إِلَّا رَبَّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
77. «እነርሱም ጣኦቶቹ ለእኔ ጠላቶች ናቸው:: የዓለማት ጌታ ብቻ ሲቀር:: እርሱማ ወዳጄ ነው።
Las Exégesis Árabes:
ٱلَّذِي خَلَقَنِي فَهُوَ يَهۡدِينِ
78. «እርሱ ያ የፈጠረኝ ነው:: እርሱም ይመራኛል።
Las Exégesis Árabes:
وَٱلَّذِي هُوَ يُطۡعِمُنِي وَيَسۡقِينِ
79. «ያም እርሱ የሚያበላኝና የሚያጠጣኝም ነው።
Las Exégesis Árabes:
وَإِذَا مَرِضۡتُ فَهُوَ يَشۡفِينِ
80. «በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል።
Las Exégesis Árabes:
وَٱلَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحۡيِينِ
81. «ያም የሚገድለኝ ከዚያም ህያው የሚያደርገኝ ነው።
Las Exégesis Árabes:
وَٱلَّذِيٓ أَطۡمَعُ أَن يَغۡفِرَ لِي خَطِيٓـَٔتِي يَوۡمَ ٱلدِّينِ
82. «ያም በፍርዱ ቀን ኃጢአቴን ሊምርልኝ የምከጅለው ነው።» (አለ)
Las Exégesis Árabes:
رَبِّ هَبۡ لِي حُكۡمٗا وَأَلۡحِقۡنِي بِٱلصَّٰلِحِينَ
83. (ኢብራሂምም) «ጌታዬ ሆይ! እውቀትን ስጠኝ በደጋጎቹም ሰዎች አስጠጋኝ።
Las Exégesis Árabes:
 
Traducción de significados Capítulo: Al-Shu'araa
Índice de Capítulos Número de página
 
Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África - Índice de traducciones

Traducida por Muhammad Zain Zahr Ad-Din. Publicada por la Academia de África.

Cerrar