Check out the new design

ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا * - لیست ترجمه ها


ترجمهٔ معانی سوره: بقره   آیه:
قُلۡنَا ٱهۡبِطُواْ مِنۡهَا جَمِيعٗاۖ فَإِمَّا يَأۡتِيَنَّكُم مِّنِّي هُدٗى فَمَن تَبِعَ هُدَايَ فَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ
38. «ሁላችሁም (አደም፣ ሐዋና ሰይጣን) በአንድ ሆናችሁ ከገነት ወደ (ምድር) ውረዱ አልናቸውም። ከዚያም ከእኔ የሆነ መመሪያ ቢመጣላችሁ መመሪያዬን የተከተሉ በእነርሱ ላይ ስጋትም ትካዜም የለባቸውም።
تفسیرهای عربی:
وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَآ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
39. «እነዚያም በመልዕክተኞቻችን የካዱና በራዕያችን ያስተባበሉ ሁሉ ግን እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ የእሳት (ገሀነም) ጓዶች ናቸው።» (አልናቸው።)
تفسیرهای عربی:
يَٰبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱذۡكُرُواْ نِعۡمَتِيَ ٱلَّتِيٓ أَنۡعَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ وَأَوۡفُواْ بِعَهۡدِيٓ أُوفِ بِعَهۡدِكُمۡ وَإِيَّٰيَ فَٱرۡهَبُونِ
40. እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ያችን በእናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬን አስታውሱ:: ቃል ኪዳኔንም ሙሉ:: እኔም ቃልኪዳናችሁን እሞላላችኋለሁና። እኔንም ብቻ ፍሩኝ።
تفسیرهای عربی:
وَءَامِنُواْ بِمَآ أَنزَلۡتُ مُصَدِّقٗا لِّمَا مَعَكُمۡ وَلَا تَكُونُوٓاْ أَوَّلَ كَافِرِۭ بِهِۦۖ وَلَا تَشۡتَرُواْ بِـَٔايَٰتِي ثَمَنٗا قَلِيلٗا وَإِيَّٰيَ فَٱتَّقُونِ
41. (እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ከናንተ ጋር ያለውን መጽሐፍ እውቅና የሚሰጥ ሆኖ ባወረድኩት (ቁርኣን) እመኑ:: በእርሱም የመጀመሪያ ከሓዲያን አትሁኑ:: በአንቃጾቼ ጥቂት ገንዘብ አትለውጡ:: እኔንም ብቻ ፍሩኝ፡፡
تفسیرهای عربی:
وَلَا تَلۡبِسُواْ ٱلۡحَقَّ بِٱلۡبَٰطِلِ وَتَكۡتُمُواْ ٱلۡحَقَّ وَأَنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
42. እውነቱን ከውሸት ጋር አትቀላቅሉ:: እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡
تفسیرهای عربی:
وَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُواْ ٱلزَّكَوٰةَ وَٱرۡكَعُواْ مَعَ ٱلرَّٰكِعِينَ
43. ሶላትን ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ:: ዘካንም ለተገቢው አካል ስጡ:: ለጌታችሁም ከአጎንባሾች ጋር አጎንብሱ:: (ከሰጋጆች ጋር ስገዱ)።
تفسیرهای عربی:
۞ أَتَأۡمُرُونَ ٱلنَّاسَ بِٱلۡبِرِّ وَتَنسَوۡنَ أَنفُسَكُمۡ وَأَنتُمۡ تَتۡلُونَ ٱلۡكِتَٰبَۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ
44. እናንተ መጽሐፍን የምታነቡ ሆናችሁና ሰዎችን በበጎ ስራ እያዘዛችሁ ራሳችሁን በመልካም ምግባር ከማነጽ ትዘነጋላችሁን? አታስተውሉምን?
تفسیرهای عربی:
وَٱسۡتَعِينُواْ بِٱلصَّبۡرِ وَٱلصَّلَوٰةِۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى ٱلۡخَٰشِعِينَ
45.በመታገስና በሶላትም ተረዱ፡፡ እርሷ (ሶላት) በፈሪዎች ላይ እንጂ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት።
تفسیرهای عربی:
ٱلَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَٰقُواْ رَبِّهِمۡ وَأَنَّهُمۡ إِلَيۡهِ رَٰجِعُونَ
46. እነዚያ ከጌታቸው ጋር እንደሚገናኙና ወደ እርሱ ተመላሾች መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ናቸው።
تفسیرهای عربی:
يَٰبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱذۡكُرُواْ نِعۡمَتِيَ ٱلَّتِيٓ أَنۡعَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ وَأَنِّي فَضَّلۡتُكُمۡ عَلَى ٱلۡعَٰلَمِينَ
50. የእስራኤል ልጆች ሆይ! ያችን በናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬንና እኔም በዓለማት ላይ ያበለጥኳችሁ (አባቶቻችሁን በጊዜያቸው ከነበሩት ዓለማት ያበለጥኩዋቸው) መኾኔን አስታውሱ፡፡
تفسیرهای عربی:
وَٱتَّقُواْ يَوۡمٗا لَّا تَجۡزِي نَفۡسٌ عَن نَّفۡسٖ شَيۡـٔٗا وَلَا يُقۡبَلُ مِنۡهَا شَفَٰعَةٞ وَلَا يُؤۡخَذُ مِنۡهَا عَدۡلٞ وَلَا هُمۡ يُنصَرُونَ
48. ማንኛዋም ነፍስ ከሌላዋ ነፍስ ምንንም የማትመነዳበትን፤ ከእርሷም ምልጃን የማይቀበሉባትን፤ ከእርሷም ቤዛ የማይያዝባትንና እነርሱም በየትኛዉም አካል የማይረዱበትን ቀን ቅጣት ፍሩ (ተጠንቀቁ)፡፡
تفسیرهای عربی:
 
ترجمهٔ معانی سوره: بقره
فهرست سوره ها شماره صفحه
 
ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا - لیست ترجمه ها

مترجم: محمد زین زهرالدین. آکادمی آفریقا آن را منتشر كرده است.

بستن