Check out the new design

ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا * - لیست ترجمه ها

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ترجمهٔ معانی سوره: بقره   آیه:
وَإِذۡ نَجَّيۡنَٰكُم مِّنۡ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ يَسُومُونَكُمۡ سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ يُذَبِّحُونَ أَبۡنَآءَكُمۡ وَيَسۡتَحۡيُونَ نِسَآءَكُمۡۚ وَفِي ذَٰلِكُم بَلَآءٞ مِّن رَّبِّكُمۡ عَظِيمٞ
49. ከፈርዖን ቤተሰቦች (ከጎሳዎቹ) ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚያርዱና ሴቶቻችሁን የሚተዉ ሲሆኑ ከእነርሱ ባዳንናችሁ ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውሱ)። ያ ክስተት ከጌታችሁ ለእናንተ ታላቅ ፈተና ነበር።
تفسیرهای عربی:
وَإِذۡ فَرَقۡنَا بِكُمُ ٱلۡبَحۡرَ فَأَنجَيۡنَٰكُمۡ وَأَغۡرَقۡنَآ ءَالَ فِرۡعَوۡنَ وَأَنتُمۡ تَنظُرُونَ
50. (እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) በእናንተ ምክንያት ባህሩን በከፈልን ጊዜ የሆነውን ታሪክም አስታውሱ:: ወዲያውኑም አዳንናችሁ:: የፈርዖንንም ቤተሰቦች ዓይናችሁ እያየ አሰመጥናቸው::
تفسیرهای عربی:
وَإِذۡ وَٰعَدۡنَا مُوسَىٰٓ أَرۡبَعِينَ لَيۡلَةٗ ثُمَّ ٱتَّخَذۡتُمُ ٱلۡعِجۡلَ مِنۢ بَعۡدِهِۦ وَأَنتُمۡ ظَٰلِمُونَ
51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳ የአርባ ሌሊትን ቀጠሮ ከእኛ በወሰደበት ጊዜ (የሆነውን ታሪክ ለህዝቦችህ አስታውስ):: ከዚያም ከእርሱ (መሄድ) በኋላ እናንተ ራሳችሁን በዳዩች ስትሆኑ ወይፈንን አምላክ አደረጋችሁ::
تفسیرهای عربی:
ثُمَّ عَفَوۡنَا عَنكُم مِّنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
52. (ቢሆንም) ከዚያ በኋላ ታመሰግኑ ዘንድ ለእናንተ ምህረትን አደርግን::
تفسیرهای عربی:
وَإِذۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡفُرۡقَانَ لَعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ
53. (እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ወደ ትክክለኛው መንገድ) ትመሩ ዘንድ ለሙሳ እውነትንና ውሸትን የሚለይን መጽሐፍ በሰጠነው ጊዜ (የዋልንላችሁን ውለታ አስታውሱ)::
تفسیرهای عربی:
وَإِذۡ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوۡمِهِۦ يَٰقَوۡمِ إِنَّكُمۡ ظَلَمۡتُمۡ أَنفُسَكُم بِٱتِّخَاذِكُمُ ٱلۡعِجۡلَ فَتُوبُوٓاْ إِلَىٰ بَارِئِكُمۡ فَٱقۡتُلُوٓاْ أَنفُسَكُمۡ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ عِندَ بَارِئِكُمۡ فَتَابَ عَلَيۡكُمۡۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ
54. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ሙሳ ለሕዝቦቹ (እንዲህ) ባለም ጊዜ የዋልነውን ውለታ አስታውሱ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! እናንተ ወይፈንን አምላክ በማድረጋችሁ ነፍሶቻችሁን በደላችሁ:: በመሆኑም ወደ ፈጣሪያችሁ ተመለሱ:: ከመካከላችሁ ወንጀለኛ ወገኖቻችሁን ግደሉ:: ይሃችሁ ድርጊት በፈጣሪያችሁ ዘንድ ለእንናተ በላጭ ነው። በእናንተም ላይ ምህረቱን አወረደ:: እነሆ እርሱ (አላህ) ጸጸትን ተቀባይ ምህረተኛ አዛኝ ነውና።
تفسیرهای عربی:
وَإِذۡ قُلۡتُمۡ يَٰمُوسَىٰ لَن نُّؤۡمِنَ لَكَ حَتَّىٰ نَرَى ٱللَّهَ جَهۡرَةٗ فَأَخَذَتۡكُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ وَأَنتُمۡ تَنظُرُونَ
55. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) «ሙሳ ሆይ! አላህን በይፋ እስከምናይ ድረስ ለአንተ በፍጹም አናምንልህም።» ባላችሁ ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውሱ)። እናንተም በዓይናችሁ እየተመለከታችሁ መብረቅ መታችሁ።
تفسیرهای عربی:
ثُمَّ بَعَثۡنَٰكُم مِّنۢ بَعۡدِ مَوۡتِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
56. ከዚያም ታመሰግኑ ዘንድ ከሞታችሁ በኋላ አስነሳናችሁ፡፡
تفسیرهای عربی:
وَظَلَّلۡنَا عَلَيۡكُمُ ٱلۡغَمَامَ وَأَنزَلۡنَا عَلَيۡكُمُ ٱلۡمَنَّ وَٱلسَّلۡوَىٰۖ كُلُواْ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقۡنَٰكُمۡۚ وَمَا ظَلَمُونَا وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ
57. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) በናንተ ላይ ዳመናን አጠለልን:: እንደ ነጭ ማር ያለ «መንን» እና ድርጭትን ለምግብነት አወረድን:: «ከሰጠናችሁም ጣፋጮችን።» ብሉ አልን:: እኛን አልበደሉንም:: ነፍሶቻቸውን ግን ይበድሉ ነበር::
تفسیرهای عربی:
 
ترجمهٔ معانی سوره: بقره
فهرست سوره ها شماره صفحه
 
ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا - لیست ترجمه ها

مترجم: محمد زین زهرالدین. آکادمی آفریقا آن را منتشر كرده است.

بستن