Check out the new design

ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا * - لیست ترجمه ها


ترجمهٔ معانی سوره: صافات   آیه:
مَا لَكُمۡ لَا تَنَاصَرُونَ
25. ለነርሱም «ምን ሆናችሁ ነው የማትረዳዱት?» ይባላሉ።
تفسیرهای عربی:
بَلۡ هُمُ ٱلۡيَوۡمَ مُسۡتَسۡلِمُونَ
26. በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ማምለጫ የሌላቸው ወራዳዎች ናቸው::
تفسیرهای عربی:
وَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ
27. እርስ በራሳቸውም የሚወቃቀሱም ሆነው ይመጣሉ።
تفسیرهای عربی:
قَالُوٓاْ إِنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَأۡتُونَنَا عَنِ ٱلۡيَمِينِ
28. (ተከታዮቹ ለአስከታዮቻቸው) «እናንተ በጉልበት ትመጡብን ነበር» ይላሉ።
تفسیرهای عربی:
قَالُواْ بَل لَّمۡ تَكُونُواْ مُؤۡمِنِينَ
29. (አስከታዮቹም) ይላሉ፡- «አይደለም ፈጽሞ አማኞች አልነበራችሁም።
تفسیرهای عربی:
وَمَا كَانَ لَنَا عَلَيۡكُم مِّن سُلۡطَٰنِۭۖ بَلۡ كُنتُمۡ قَوۡمٗا طَٰغِينَ
30. «ለእኛም በናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም። በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ህዝቦች ነበራችሁና ነው እንጂ።
تفسیرهای عربی:
فَحَقَّ عَلَيۡنَا قَوۡلُ رَبِّنَآۖ إِنَّا لَذَآئِقُونَ
31. «በእኛም ላይ የጌታችን ቃል የተረጋገጠብንና ሁላችንም ቅጣቱን ቀማሽ ነን።
تفسیرهای عربی:
فَأَغۡوَيۡنَٰكُمۡ إِنَّا كُنَّا غَٰوِينَ
32. «እኛ ጠማሞች ስለ ነበርን ወደ ጥመት ጠራናችሁም።» ይላሉ።
تفسیرهای عربی:
فَإِنَّهُمۡ يَوۡمَئِذٖ فِي ٱلۡعَذَابِ مُشۡتَرِكُونَ
33. ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ተጋሪዎች ናቸው::
تفسیرهای عربی:
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَفۡعَلُ بِٱلۡمُجۡرِمِينَ
34. እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሰራለን።
تفسیرهای عربی:
إِنَّهُمۡ كَانُوٓاْ إِذَا قِيلَ لَهُمۡ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ يَسۡتَكۡبِرُونَ
35. እነርሱ «ከአላህ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም» በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ።
تفسیرهای عربی:
وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُوٓاْ ءَالِهَتِنَا لِشَاعِرٖ مَّجۡنُونِۭ
36. «እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን እንዴ?» ይሉ ነበር።
تفسیرهای عربی:
بَلۡ جَآءَ بِٱلۡحَقِّ وَصَدَّقَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
37. አይደለም እውነቱን ሃይማኖት አመጣ፤ መልዕክተኞቹንም እውነተኝነታቸውን አረጋገጠ።
تفسیرهای عربی:
إِنَّكُمۡ لَذَآئِقُواْ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡأَلِيمِ
38. እናንተ አሳማሚውን ቅጣት እርግጥ ቀማሾች ናችሁ::
تفسیرهای عربی:
وَمَا تُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
39. ትሰሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም::
تفسیرهای عربی:
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
40. ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ቅጣትን አይቀምሱም::
تفسیرهای عربی:
أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ رِزۡقٞ مَّعۡلُومٞ
41. እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አለላቸው::
تفسیرهای عربی:
فَوَٰكِهُ وَهُم مُّكۡرَمُونَ
42. ፍራፋሬዎች (አሉላቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው::
تفسیرهای عربی:
فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
43. በድሎት ገነቶች ውስጥ::
تفسیرهای عربی:
عَلَىٰ سُرُرٖ مُّتَقَٰبِلِينَ
44. ፊት ለፊት የሚተያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ ይንፈላሰሳሉ::
تفسیرهای عربی:
يُطَافُ عَلَيۡهِم بِكَأۡسٖ مِّن مَّعِينِۭ
45. ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዙ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል::
تفسیرهای عربی:
بَيۡضَآءَ لَذَّةٖ لِّلشَّٰرِبِينَ
46. ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከሆነች፤
تفسیرهای عربی:
لَا فِيهَا غَوۡلٞ وَلَا هُمۡ عَنۡهَا يُنزَفُونَ
47. በእርሷ ውስጥም የራስ ምታት የለባትም:: እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም::
تفسیرهای عربی:
وَعِندَهُمۡ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ عِينٞ
48. እነርሱ ዘንድ ዓይናቸውን በባሎቻቸው ላይ ብቻ አሳጣሪዎች የሆኑ ዓይናማ ሴቶች አሉ::
تفسیرهای عربی:
كَأَنَّهُنَّ بَيۡضٞ مَّكۡنُونٞ
49. እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) እንቁላል ይመስላሉ::
تفسیرهای عربی:
فَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ
50. የሚጠያያቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ::
تفسیرهای عربی:
قَالَ قَآئِلٞ مِّنۡهُمۡ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٞ
51. ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ (እንዲህ) ይላል: «እኔ ጓደኛ ነበረኝ።
تفسیرهای عربی:
 
ترجمهٔ معانی سوره: صافات
فهرست سوره ها شماره صفحه
 
ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا - لیست ترجمه ها

مترجم: محمد زین زهرالدین. آکادمی آفریقا آن را منتشر كرده است.

بستن