Check out the new design

Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Muhammad Sâdiq * - Lexique des traductions

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Traduction des sens Sourate: Al 'Imran   Verset:
وَلِيُمَحِّصَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَيَمۡحَقَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
አላህም እነዚያን ያመኑትን (ከኀጢአት) ሊያነጻና ከሓዲዎችንም ሊያጠፋ ነው፡፡
Les exégèses en arabe:
أَمۡ حَسِبۡتُمۡ أَن تَدۡخُلُواْ ٱلۡجَنَّةَ وَلَمَّا يَعۡلَمِ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ جَٰهَدُواْ مِنكُمۡ وَيَعۡلَمَ ٱلصَّٰبِرِينَ
በእውነቱ አላህ ከናንተ እነዚያን የታገሉትን ሳያውቅ (ሳይለይ) ታጋሾቹንም ሳያውቅ ገነትን ልትገቡ አሰባችሁን?
Les exégèses en arabe:
وَلَقَدۡ كُنتُمۡ تَمَنَّوۡنَ ٱلۡمَوۡتَ مِن قَبۡلِ أَن تَلۡقَوۡهُ فَقَدۡ رَأَيۡتُمُوهُ وَأَنتُمۡ تَنظُرُونَ
(በጦርነት ላይ) መሞትን ሳታገኙት በፊት በርግጥ የምትመኙት ነበራችሁ፡፡ እናንተም የምትመለከቱ ስትኾኑ በርግጥ አያችሁት (ታዲያ ለምን ሸሻችሁ)
Les exégèses en arabe:
وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٞ قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِهِ ٱلرُّسُلُۚ أَفَإِيْن مَّاتَ أَوۡ قُتِلَ ٱنقَلَبۡتُمۡ عَلَىٰٓ أَعۡقَٰبِكُمۡۚ وَمَن يَنقَلِبۡ عَلَىٰ عَقِبَيۡهِ فَلَن يَضُرَّ ٱللَّهَ شَيۡـٔٗاۚ وَسَيَجۡزِي ٱللَّهُ ٱلشَّٰكِرِينَ
ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ታዲያ ቢሞት ወይም ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን ወደ ኋላው የሚገለበጥ ሰው አላህን ምንም አይጎዳም፡፡ አላህ አመስጋኞቹን በእርግጥ ይመነዳል፡፡
Les exégèses en arabe:
وَمَا كَانَ لِنَفۡسٍ أَن تَمُوتَ إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِ كِتَٰبٗا مُّؤَجَّلٗاۗ وَمَن يُرِدۡ ثَوَابَ ٱلدُّنۡيَا نُؤۡتِهِۦ مِنۡهَا وَمَن يُرِدۡ ثَوَابَ ٱلۡأٓخِرَةِ نُؤۡتِهِۦ مِنۡهَاۚ وَسَنَجۡزِي ٱلشَّٰكِرِينَ
ለማንኛይቱም ነፍስ በአላህ ፍርድ ቢኾን እንጅ ልትሞት አይገባትም፡፡ (ጊዜውም) ተወስኖ ተጽፏል፡፡ የቅርቢቱንም ምንዳ የሚፈልግ ሰው ከእርስዋ እንሰጠዋለን፡፡ የመጨረሻይቱንም ምንዳ የሚፈልግ ሰው ከእርስዋ እንሰጠዋለን፤ አመስጋኞችንም በእርግጥ እንመነዳለን፡፡
Les exégèses en arabe:
وَكَأَيِّن مِّن نَّبِيّٖ قَٰتَلَ مَعَهُۥ رِبِّيُّونَ كَثِيرٞ فَمَا وَهَنُواْ لِمَآ أَصَابَهُمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَمَا ضَعُفُواْ وَمَا ٱسۡتَكَانُواْۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلصَّٰبِرِينَ
ከነቢይም ብዙ ሊቃውንት ከርሱ ጋር ኾነው የተዋጉ ብዙ ናቸው፡፡ በአላህም መንገድ ለሚደርስባቸው ነገር አልፈሩም፤ አልደከሙምም፡፡ (ለጠላት) አልተዋረዱምም፡፡ አላህ ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡
Les exégèses en arabe:
وَمَا كَانَ قَوۡلَهُمۡ إِلَّآ أَن قَالُواْ رَبَّنَا ٱغۡفِرۡ لَنَا ذُنُوبَنَا وَإِسۡرَافَنَا فِيٓ أَمۡرِنَا وَثَبِّتۡ أَقۡدَامَنَا وَٱنصُرۡنَا عَلَى ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡكَٰفِرِينَ
ንግግራቸውም «ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንና በነገራችን ሁሉ ወሰን ማለፋችንን ለእኛ ማር፣ ይዞታችንንም አደላድል፣ በከሓዲዎችም ሕዝቦች ላይ እርዳን» ማለታቸው እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡
Les exégèses en arabe:
فَـَٔاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ ثَوَابَ ٱلدُّنۡيَا وَحُسۡنَ ثَوَابِ ٱلۡأٓخِرَةِۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
አላህም የቅርቢቱን ምንዳና የመጨረሻይቱን መልካም ምንዳ ሰጣቸው፡፡ አላህም በጎ አድራጊዎችን ይወዳል፡፡
Les exégèses en arabe:
 
Traduction des sens Sourate: Al 'Imran
Lexique des sourates Numéro de la page
 
Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Muhammad Sâdiq - Lexique des traductions

Traduit par Cheikh Muhammad Sâdiq et Muhammad Ath-Thânî Habîb. Développement achevé sous la supervision du Centre Rouwwâd At-Tarjamah (Les Pionniers de la Traduction), avec accès à la traduction originale dans le but de la réception des suggestions des lecteurs, d'évaluation et de développement continu.

Fermeture