Check out the new design

Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Académie d'Afrique * - Lexique des traductions


Traduction des sens Sourate: Al Ahqâf   Verset:
وَوَصَّيۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيۡهِ إِحۡسَٰنًاۖ حَمَلَتۡهُ أُمُّهُۥ كُرۡهٗا وَوَضَعَتۡهُ كُرۡهٗاۖ وَحَمۡلُهُۥ وَفِصَٰلُهُۥ ثَلَٰثُونَ شَهۡرًاۚ حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغَ أَشُدَّهُۥ وَبَلَغَ أَرۡبَعِينَ سَنَةٗ قَالَ رَبِّ أَوۡزِعۡنِيٓ أَنۡ أَشۡكُرَ نِعۡمَتَكَ ٱلَّتِيٓ أَنۡعَمۡتَ عَلَيَّ وَعَلَىٰ وَٰلِدَيَّ وَأَنۡ أَعۡمَلَ صَٰلِحٗا تَرۡضَىٰهُ وَأَصۡلِحۡ لِي فِي ذُرِّيَّتِيٓۖ إِنِّي تُبۡتُ إِلَيۡكَ وَإِنِّي مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ
15. የሰውን ልጅ ለወላጆቹ በጎ መዋል እንዳለበት በጥብቅ አዘዝነው:: እናቱ በችግር ላይ ሆና አረገዘችው:: በችግርም ላይ ሆና ወለደችው:: እርግዝናውና (ከጡት) መለያው ሙሉ ሰላሳ ወር ነው:: ከዚያም የጥንካሬውን ወቅት በደረሰ ጊዜ አርባ ዓመት በደረሰ ጊዜ «ጌታዬ ሆይ! ያን በእኔ ላይና በወላጆቼ ላይ የለገስከዉን ጸጋህን እንዳመሰግንህና የምትወደውን መልካም ስራም እንድሰራ ወደ ቀናው መንገድ ምራኝ:: ዘሮቼንም ለእኔ አብጅልኝ:: እኔ ወደ አንተ ብቻ ተመለስኩ:: እኔ ከሙስሊሞች አንዱ ነኝ» አለ::
Les exégèses en arabe:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ نَتَقَبَّلُ عَنۡهُمۡ أَحۡسَنَ مَا عَمِلُواْ وَنَتَجَاوَزُ عَن سَيِّـَٔاتِهِمۡ فِيٓ أَصۡحَٰبِ ٱلۡجَنَّةِۖ وَعۡدَ ٱلصِّدۡقِ ٱلَّذِي كَانُواْ يُوعَدُونَ
16. እነዚያ (ይህንን ባዩች ሁሉ) ከገነት ጓዶች መካከል ሲሆኑ እነዚያ ከሰሩት ስራ መልካሙን የምንቀበላቸውና ከኃጢአቶቻቸዉም የምናልፋቸው ሰዎች ናቸው:: ያንን ተስፋ ይሰጡት የነበሩትን እውነተኛ ቀጠሮ እንሞላላቸዋለን::
Les exégèses en arabe:
وَٱلَّذِي قَالَ لِوَٰلِدَيۡهِ أُفّٖ لَّكُمَآ أَتَعِدَانِنِيٓ أَنۡ أُخۡرَجَ وَقَدۡ خَلَتِ ٱلۡقُرُونُ مِن قَبۡلِي وَهُمَا يَسۡتَغِيثَانِ ٱللَّهَ وَيۡلَكَ ءَامِنۡ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞ فَيَقُولُ مَا هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
17. ያንንም ለሁለቱ ወላጆቹ አላህን የሚለምኑ ሲሆኑ «በአላህ እመን፤ የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ ነው፤» ሲሉት «ኡፍ! ከእኔ በፊት የብዙ ክፈለ ዘመናት ሰዎች ሳይወጡ በእርግጥ ያለፉ ሲሆኑ ከመቃብር እንደምወጣ ታስፈራሩኛላችሁን?» ይላልም: "ይህ የቀደምቶች ተረት እንጅ ሌላ አይደለም" ይላል።
Les exégèses en arabe:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ حَقَّ عَلَيۡهِمُ ٱلۡقَوۡلُ فِيٓ أُمَمٖ قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِهِم مِّنَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِۖ إِنَّهُمۡ كَانُواْ خَٰسِرِينَ
18. እነዚህ እነዚያ ከአጋንንትም ከሰዉም ከእነርሱ በፊት ካለፉት ህዝቦች ጋር የአላህ ቃሉ በእነርሱ ላይ የተረጋገጠባቸው ናቸው:: እነርሱ ከሳሪዎች ነበሩና::
Les exégèses en arabe:
وَلِكُلّٖ دَرَجَٰتٞ مِّمَّا عَمِلُواْۖ وَلِيُوَفِّيَهُمۡ أَعۡمَٰلَهُمۡ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ
19. ለሁሉም በሰሩት ስራ ልክ ተገቢ የሆኑ ደረጃዎች አሏቸው:: ስራዎቻቸውንም ይሞላላቸው ዘንድ ይህንን መነዳቸው:: እነርሱም አይበደሉም::
Les exégèses en arabe:
وَيَوۡمَ يُعۡرَضُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ عَلَى ٱلنَّارِ أَذۡهَبۡتُمۡ طَيِّبَٰتِكُمۡ فِي حَيَاتِكُمُ ٱلدُّنۡيَا وَٱسۡتَمۡتَعۡتُم بِهَا فَٱلۡيَوۡمَ تُجۡزَوۡنَ عَذَابَ ٱلۡهُونِ بِمَا كُنتُمۡ تَسۡتَكۡبِرُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَبِمَا كُنتُمۡ تَفۡسُقُونَ
20. እነዚያም የካዱት በእሳት ላይ በሚጋፈጡበት ቀን ጣፋጮቻችሁን በአነስተኛይቱ ሕይወታችሁ አሳለፋችሁ:: በእርሷም ተጣቀማችሁ። ስለዚህ በምድር ላይ ያለ አግባብ ትኮሩ በነበራችሁትና ታምጹ በነበራችሁት ምክኒያት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ ይባላሉ፡
Les exégèses en arabe:
 
Traduction des sens Sourate: Al Ahqâf
Lexique des sourates Numéro de la page
 
Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Académie d'Afrique - Lexique des traductions

La traduction par Muhammad Zayn Zahr Al-Dîn. Publiée par l'Académie d'Afrique.

Fermeture