Check out the new design

કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી * - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા


શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અશ્ શુઅરાઅ   આયત:

አሽ ሹዐራእ

طسٓمٓ
1. ጣ፤ሲን፤ሚይም::
અરબી તફસીરો:
تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُبِينِ
2. እነዚህ ግልጽ የሆነው መጽሀፍ አናቅጽ ናቸው::
અરબી તફસીરો:
لَعَلَّكَ بَٰخِعٞ نَّفۡسَكَ أَلَّا يَكُونُواْ مُؤۡمِنِينَ
3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን አማኞች ባለ መሆናቸው በቁጭት ነፍስህን እንዳታጠፋ ይፈራልሃል (ያሰጋል)::
અરબી તફસીરો:
إِن نَّشَأۡ نُنَزِّلۡ عَلَيۡهِم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ ءَايَةٗ فَظَلَّتۡ أَعۡنَٰقُهُمۡ لَهَا خَٰضِعِينَ
4. ብንሻ ኖሮ በእነርሱ ላይ ከሰማይ ተዓምርን እናወርድና አንገቶቻቸው (መሪዎቻቸው) ለእርሷ ተዋራጆች እናደርጋለን::
અરબી તફસીરો:
وَمَا يَأۡتِيهِم مِّن ذِكۡرٖ مِّنَ ٱلرَّحۡمَٰنِ مُحۡدَثٍ إِلَّا كَانُواْ عَنۡهُ مُعۡرِضِينَ
5. ከአር-ረህማን ዘንድ አዲስ የተወረደ ተግሳፅ አይመጣላቸዉም:: ከእርሱ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ::
અરબી તફસીરો:
فَقَدۡ كَذَّبُواْ فَسَيَأۡتِيهِمۡ أَنۢبَٰٓؤُاْ مَا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
6. በእርግጥም አስተባበሉ:: የዚያም በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ወሬዎች ፍጻሜ ይመጣባቸዋል::
અરબી તફસીરો:
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَى ٱلۡأَرۡضِ كَمۡ أَنۢبَتۡنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوۡجٖ كَرِيمٍ
7.ወደ ምድርም በውስጧ ከመልካም በቃይ ጎሳ ብዙን እንዳበቀልን አላዩምን።
અરબી તફસીરો:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
8. በዚህ አስደናቂ ምልክት አለበት፤ አብዛኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም።
અરબી તફસીરો:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በትክክል ሁሉን አሸናፊና አዛኝ ነው::
અરબી તફસીરો:
وَإِذۡ نَادَىٰ رَبُّكَ مُوسَىٰٓ أَنِ ٱئۡتِ ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ሙሳን «ወደ እነዚያ በደለኛ ህዝቦች ሂድ።» በማለት በጠራው ጊዜ የሆነውን አስታውስ።
અરબી તફસીરો:
قَوۡمَ فِرۡعَوۡنَۚ أَلَا يَتَّقُونَ
11. «ወደ ፈርዖን ህዝቦች አላህን አይፈሩምን?»
અરબી તફસીરો:
قَالَ رَبِّ إِنِّيٓ أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ
12. ሙሳም «ጌታዬ ሆይ! እኔ ያስተባብሉኛል ብዬ እፈራለሁ።
અરબી તફસીરો:
وَيَضِيقُ صَدۡرِي وَلَا يَنطَلِقُ لِسَانِي فَأَرۡسِلۡ إِلَىٰ هَٰرُونَ
13. «ልቤም ይጠባል፤ ምላሴም ይንተባተባል። ስለዚህ ወደ ሃሩንም ላክ።
અરબી તફસીરો:
وَلَهُمۡ عَلَيَّ ذَنۢبٞ فَأَخَافُ أَن يَقۡتُلُونِ
14. «በተጨማሪም ለእነርሱም በእኔ ላይ (የደም) ወንጀል አላቸው:: ስለዚህ እንዳይገድሉኝም እፈራለሁ።» አለ።
અરબી તફસીરો:
قَالَ كَلَّاۖ فَٱذۡهَبَا بِـَٔايَٰتِنَآۖ إِنَّا مَعَكُم مُّسۡتَمِعُونَ
15. አላህ አለ: «ተው! አይነኩህም ሁለታችሁም በተአምሮታችን ታጅባችሁ ሂዱ። እኛ ከናንተ ጋር ሁነን ሰሚዎች ነንና።
અરબી તફસીરો:
فَأۡتِيَا فِرۡعَوۡنَ فَقُولَآ إِنَّا رَسُولُ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
16. «ወደ ፈርዖንም ሂዱና። በሉትም: ‹እኛ የዓለማት ጌታ መልዕክተኞች ነን።
અરબી તફસીરો:
أَنۡ أَرۡسِلۡ مَعَنَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
17. «‹የኢስራኢልን ልጆችም ከእኛ ጋር ልቀቅልን።›» (በሉት)
અરબી તફસીરો:
قَالَ أَلَمۡ نُرَبِّكَ فِينَا وَلِيدٗا وَلَبِثۡتَ فِينَا مِنۡ عُمُرِكَ سِنِينَ
18. ፈርዖንም አለ፡ «ልጅ ሆንህ በእኛ ውስጥ አላሳደግንህምን? በእኛ ውስጥም ከዕድሜህ ብዙ ዓመታትን አልተቀመጥክምን?
અરબી તફસીરો:
وَفَعَلۡتَ فَعۡلَتَكَ ٱلَّتِي فَعَلۡتَ وَأَنتَ مِنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
19. «ያችን የሰራሃትን ስራስ አልሰራህምን? አንተ ከውለታ ቢሶች ነህ።» (አለ)።
અરબી તફસીરો:
 
શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અશ્ શુઅરાઅ
સૂરહ માટે અનુક્રમણિકા પેજ નંબર
 
કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા

તેનું અનુવાદ મુહમ્મદ ઝૈન ઝહરુદ્ દીન દ્વારા કરવામાં આવ્યું. આફ્રિકા એકેડમી દ્વારા પ્રકાશિત.

બંધ કરો