Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

अर्थों का अनुवाद सूरा: यूसुफ़   आयत:
قَالَ يَٰبُنَيَّ لَا تَقۡصُصۡ رُءۡيَاكَ عَلَىٰٓ إِخۡوَتِكَ فَيَكِيدُواْ لَكَ كَيۡدًاۖ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ لِلۡإِنسَٰنِ عَدُوّٞ مُّبِينٞ
5. አባቱም አለ: «ልጄ ሆይ! ይህን ህልምህን ለወንድሞችህ አትንገር። ባንተ ላይ ተንኮል እንዳያሴሩ። ምክንያቱም ሰይጣን ለሰው ልጅ ሁልጊዜም ግልጽ ጠላት ነውና።
अरबी तफ़सीरें:
وَكَذَٰلِكَ يَجۡتَبِيكَ رَبُّكَ وَيُعَلِّمُكَ مِن تَأۡوِيلِ ٱلۡأَحَادِيثِ وَيُتِمُّ نِعۡمَتَهُۥ عَلَيۡكَ وَعَلَىٰٓ ءَالِ يَعۡقُوبَ كَمَآ أَتَمَّهَا عَلَىٰٓ أَبَوَيۡكَ مِن قَبۡلُ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡحَٰقَۚ إِنَّ رَبَّكَ عَلِيمٌ حَكِيمٞ
6. «ጌታህ ልክ ይህን ህልም እንዳሳየህ ሁሉ ለነብይነትም ይመርጥሃል:: የንንግግሮችን ፍፃሜ ያስተምርሃል:: ጸጋውንም ቀደም ሲል ለአባቶችህ ለኢብራሂምና ለኢስሃቅ እንደሞላ ሁሉ ላንተና ለያዕቁብ ቤተሰቦችም ይሞላል:: ጌታህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።»
अरबी तफ़सीरें:
۞ لَّقَدۡ كَانَ فِي يُوسُفَ وَإِخۡوَتِهِۦٓ ءَايَٰتٞ لِّلسَّآئِلِينَ
7. በዩሱፍና በወንድሞቹ ታሪክ ዉስጥ እውቀትን በመሻት ለሚጠይቁ ሁሉ እያሌ ተዓምራት አሉ::
अरबी तफ़सीरें:
إِذۡ قَالُواْ لَيُوسُفُ وَأَخُوهُ أَحَبُّ إِلَىٰٓ أَبِينَا مِنَّا وَنَحۡنُ عُصۡبَةٌ إِنَّ أَبَانَا لَفِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ
8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) ባሉ ጊዜ: «እኛ በቁጥር ብዙዎች ሁነን እያለ ዩሱፍና ወንድሙ (ብንያም) ከአባታችን ዘንድ ከእኛ ይበልጥ ተወዳጆች ናቸው:: በእውነቱ አባታችን ግልጽ ስህተት ውስጥ ነው።
अरबी तफ़सीरें:
ٱقۡتُلُواْ يُوسُفَ أَوِ ٱطۡرَحُوهُ أَرۡضٗا يَخۡلُ لَكُمۡ وَجۡهُ أَبِيكُمۡ وَتَكُونُواْ مِنۢ بَعۡدِهِۦ قَوۡمٗا صَٰلِحِينَ
9. «ዩሱፍን ግደሉት ወይም እሩቅ ቦታ ጣሉት:: ይህን ካረጋችሁ የአባታችሁን ፊት ትኩረትና ውዴታ የራሳችሁ ብቻ ታደርጋላችሁ:: ከዚህ በኋላ ከኃጥያታችሁ በመመለስ መልካም ሰዎች ትሆናለችሁ።
अरबी तफ़सीरें:
قَالَ قَآئِلٞ مِّنۡهُمۡ لَا تَقۡتُلُواْ يُوسُفَ وَأَلۡقُوهُ فِي غَيَٰبَتِ ٱلۡجُبِّ يَلۡتَقِطۡهُ بَعۡضُ ٱلسَّيَّارَةِ إِن كُنتُمۡ فَٰعِلِينَ
10. ከእነሱ አንድ ተናጋሪ «ዩሱፍን አትግደሉ ግን በጉድጓድ አዘቅት ጨለማ ውስጥ ጣሉት፤ ከተጓዢዎች አንዱ ያነሳዋልና፡፡ ሠሪዎች ብትኾኑ (በዚሁ ተብቃቁ) አላቸው፡፡
अरबी तफ़सीरें:
قَالُواْ يَٰٓأَبَانَا مَا لَكَ لَا تَأۡمَ۬نَّا عَلَىٰ يُوسُفَ وَإِنَّا لَهُۥ لَنَٰصِحُونَ
11. አሉም: «አባታችን ሆይ! በዩሱፍ ጉዳይ እኛ ለእርሱ ቅን አሳቢዎች ሁነን ሳለ ለምን አታምነንም?
अरबी तफ़सीरें:
أَرۡسِلۡهُ مَعَنَا غَدٗا يَرۡتَعۡ وَيَلۡعَبۡ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
12. «እስቲ ይዝናና ይጫወት ዘንድ ነገ ከእኛ ጋር አብረህ ላከው::እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን።»
अरबी तफ़सीरें:
قَالَ إِنِّي لَيَحۡزُنُنِيٓ أَن تَذۡهَبُواْ بِهِۦ وَأَخَافُ أَن يَأۡكُلَهُ ٱلذِّئۡبُ وَأَنتُمۡ عَنۡهُ غَٰفِلُونَ
13. አባቱም «እርሱን መውሰዳችሁ ያሳዝነኛል። ዘንግታችሁት ተኩላ እንዳይበላዉም እፈራለሁ።» አለ።
अरबी तफ़सीरें:
قَالُواْ لَئِنۡ أَكَلَهُ ٱلذِّئۡبُ وَنَحۡنُ عُصۡبَةٌ إِنَّآ إِذٗا لَّخَٰسِرُونَ
14. እነርሱም «እኛ እንዲህ ጭፍሮች ሆነን ተኩላ ከበላውማ ከሳሪዎቹ እኛ ነን።» አሉ።
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: यूसुफ़
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी की ओर से निर्गत.

बंद करें