Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची


अर्थों का अनुवाद सूरा: अर्-रअ़्द   आयत:
۞ مَّثَلُ ٱلۡجَنَّةِ ٱلَّتِي وُعِدَ ٱلۡمُتَّقُونَۖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ أُكُلُهَا دَآئِمٞ وَظِلُّهَاۚ تِلۡكَ عُقۡبَى ٱلَّذِينَ ٱتَّقَواْۚ وَّعُقۡبَى ٱلۡكَٰفِرِينَ ٱلنَّارُ
35. ያች ጥንቁቆች የተሰጧት ገነት ምጣኔዋ (ምሳሌዋ) እንደሚነገራችሁ ነው:: ከሥርዋ ወንዞች ይፈሳሉ:: ምግቧ ሁል ጊዜም የማያቋረጥ ነው:: ጥላዋም እንደዚሁ። ይህች ገነት የእነዚያ የተጠነቀቁት መጨረሻ ናት:: የከሓዲያን መጨረሻ ግን እሳት ናት::
अरबी तफ़सीरें:
وَٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ يَفۡرَحُونَ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيۡكَۖ وَمِنَ ٱلۡأَحۡزَابِ مَن يُنكِرُ بَعۡضَهُۥۚ قُلۡ إِنَّمَآ أُمِرۡتُ أَنۡ أَعۡبُدَ ٱللَّهَ وَلَآ أُشۡرِكَ بِهِۦٓۚ إِلَيۡهِ أَدۡعُواْ وَإِلَيۡهِ مَـَٔابِ
36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም መጽሐፉን የሰጠናቸውን ወደ አንተ በተወረደው ይደሰታሉ:: ከአህዛብም ከፊሉን የሚክዱ ሰዎች አሉ። «እኔ የታዘዝኩት አላህን ብቻ እንድገዛና በእርሱም እንዳላጋራ ነው። ወደ እርሱ እጠራለሁ:: መመለሻዬም ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው።
अरबी तफ़सीरें:
وَكَذَٰلِكَ أَنزَلۡنَٰهُ حُكۡمًا عَرَبِيّٗاۚ وَلَئِنِ ٱتَّبَعۡتَ أَهۡوَآءَهُم بَعۡدَ مَا جَآءَكَ مِنَ ٱلۡعِلۡمِ مَا لَكَ مِنَ ٱللَّهِ مِن وَلِيّٖ وَلَا وَاقٖ
37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትህ ሲሆን አወረድነው:: እውቀቱ ከመጣልህም በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን ብትከተል ከአላህ ቅጣት ወዳጅም ሆነ ጠባቂ ምንም የለህም::37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትህ ሲሆን አወረድነው:: እውቀቱ ከመጣልህም በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን ብትከተል ከአላህ ቅጣት ወዳጅም ሆነ ጠባቂ ምንም የለህም::
अरबी तफ़सीरें:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا رُسُلٗا مِّن قَبۡلِكَ وَجَعَلۡنَا لَهُمۡ أَزۡوَٰجٗا وَذُرِّيَّةٗۚ وَمَا كَانَ لِرَسُولٍ أَن يَأۡتِيَ بِـَٔايَةٍ إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِۗ لِكُلِّ أَجَلٖ كِتَابٞ
38. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ብዙ መልዕክተኞችን በእርግጥ ልከናል:: ለእነርሱም ሚስቶችንና ልጆችን አድርገናል:: ማንኛዉም መልዕክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ ተዓምር ሊያመጣ አይገባዉም:: ለየጊዜው ሁሉ ጽሑፍ አለው::
अरबी तफ़सीरें:
يَمۡحُواْ ٱللَّهُ مَا يَشَآءُ وَيُثۡبِتُۖ وَعِندَهُۥٓ أُمُّ ٱلۡكِتَٰبِ
39. አላህ የሚፈልገውን ያብሳል:: የሚሻውን ያጸድቃል:: የመጽሐፉ ዋና መሠረትም እርሱ ዘንድ ብቻ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
وَإِن مَّا نُرِيَنَّكَ بَعۡضَ ٱلَّذِي نَعِدُهُمۡ أَوۡ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِنَّمَا عَلَيۡكَ ٱلۡبَلَٰغُ وَعَلَيۡنَا ٱلۡحِسَابُ
40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ያስፈራራናቸውን ቅጣት ከፊሉን በሕይወት እያለህ ብናሳይህ መልካም ነው:: ወይም ሳናሳይህ ብንገድልህ ወቀሳ የለብህም:: ባንተ ላይ ያለብህ መልዕክትህን ማድረስ ብቻ ነው:: ምርመራው ግን በእኛ ላይ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّا نَأۡتِي ٱلۡأَرۡضَ نَنقُصُهَا مِنۡ أَطۡرَافِهَاۚ وَٱللَّهُ يَحۡكُمُ لَا مُعَقِّبَ لِحُكۡمِهِۦۚ وَهُوَ سَرِيعُ ٱلۡحِسَابِ
41. እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎድላት ሆነን የምናመጣባት መሆናችንን አላወቁምን? አላህም ይፈርዳል:: ለፍርዱም በይግባኝ ገልባጭ የለዉም:: እርሱም ምርመራው ፈጣን ነው::
अरबी तफ़सीरें:
وَقَدۡ مَكَرَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ فَلِلَّهِ ٱلۡمَكۡرُ جَمِيعٗاۖ يَعۡلَمُ مَا تَكۡسِبُ كُلُّ نَفۡسٖۗ وَسَيَعۡلَمُ ٱلۡكُفَّٰرُ لِمَنۡ عُقۡبَى ٱلدَّارِ
42. እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት ሰዎች መከሩ (አሴሩ):: አዘንግቶም የመያዙ ዘዴ በሙሉ የአላህ ብቻ ነው:: አላህ ነፍስ ሁሉ የምትሰራውን ያውቃል:: ከሓዲያን የመጨረሻይቱ አገር ለማን እንደምትሆን ወደፊት ያውቃሉ::
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: अर्-रअ़्द
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी द्वारा प्रकाशित.

बंद करें