Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची


अर्थों का अनुवाद सूरा: अल्-ब-क़-रा   आयत:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ سَوَآءٌ عَلَيۡهِمۡ ءَأَنذَرۡتَهُمۡ أَمۡ لَمۡ تُنذِرۡهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ (በአላህ ፤ በአንተ መልዕክተኛነትና በአላህ አናቅጽ) የካዱት ሰዎች ብታስጠነቅቃቸዉም ባታስጠነቅቃቸዉም ለእነርሱ ሁሉም እኩል ነው:: (ምንም ለውጥ አያመጣም) አያምኑምና፡፡
अरबी तफ़सीरें:
خَتَمَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ وَعَلَىٰ سَمۡعِهِمۡۖ وَعَلَىٰٓ أَبۡصَٰرِهِمۡ غِشَٰوَةٞۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ
7. አላህ እነዚያ እውነትን እያወቁ የካዱ ሰዎችን በልቦቻቸው እና በመስሚያቸው ላይ አትሞባቸዋል:: በዓይኖቻቸው ላይም መሸፈኛ አለ:: ለእነርሱም በጀሀነም ውስጥ ከባድ ቅጣት አለባቸው፡፡
अरबी तफ़सीरें:
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَقُولُ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَبِٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَمَا هُم بِمُؤۡمِنِينَ
8. ከሰዎች መካከል ለይስሙላ «በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል» የሚሉ ክፍሎች አሉ:: እነርሱ ግን (የሚዋሹ እንጂ) ትክክለኛ አማኞች አይደሉም።
अरबी तफ़सीरें:
يُخَٰدِعُونَ ٱللَّهَ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَمَا يَخۡدَعُونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمۡ وَمَا يَشۡعُرُونَ
9. አላህንና እነዚያን በትክክል በአላህ ያመኑትን ሰዎች ያታልላሉ:: ነገር ግን በዚህ ተግባራቸው ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላን ማንንም አያታልሉም:: እነርሱ ግን ይህ መሆኑን በትክክል አያውቁም፡፡
अरबी तफ़सीरें:
فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ فَزَادَهُمُ ٱللَّهُ مَرَضٗاۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمُۢ بِمَا كَانُواْ يَكۡذِبُونَ
10. በልቦቻቸው ውስጥ (የንፍቅና) በሽታ ሰርጿል:: አላህም ሌላን በሽታ ጨመረባቸው:: ለእነርሱም ይዋሹ በነበሩበት ምክንያት አሳማሚ ቅጣት አለባቸው፡፡
अरबी तफ़सीरें:
وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ لَا تُفۡسِدُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ قَالُوٓاْ إِنَّمَا نَحۡنُ مُصۡلِحُونَ
11. በምድር ላይ ሁከትን አትፍጠሩ በተባሉ ጊዜ እኛ እኮ አስተካካዮች ነን ይላሉ፡፡
अरबी तफ़सीरें:
أَلَآ إِنَّهُمۡ هُمُ ٱلۡمُفۡسِدُونَ وَلَٰكِن لَّا يَشۡعُرُونَ
12. (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ:: አጥፊዎች እነርሱ ብቻ ናቸው:: ግን እነርሱ ይህንን አይገነዘቡም፡፡
अरबी तफ़सीरें:
وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ ءَامِنُواْ كَمَآ ءَامَنَ ٱلنَّاسُ قَالُوٓاْ أَنُؤۡمِنُ كَمَآ ءَامَنَ ٱلسُّفَهَآءُۗ أَلَآ إِنَّهُمۡ هُمُ ٱلسُّفَهَآءُ وَلَٰكِن لَّا يَعۡلَمُونَ
 13, «ሰዎቹ እንዳመኑት ሁሉ እናንተም እመኑ» በተባሉ ጊዜ «ቂሎቹ እንዳመኑት እናምናለንን?» ይላሉ። (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ። ቂሎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው:: እነርሱ ግን ይህንን አያውቁም።
अरबी तफ़सीरें:
وَإِذَا لَقُواْ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ قَالُوٓاْ ءَامَنَّا وَإِذَا خَلَوۡاْ إِلَىٰ شَيَٰطِينِهِمۡ قَالُوٓاْ إِنَّا مَعَكُمۡ إِنَّمَا نَحۡنُ مُسۡتَهۡزِءُونَ
14. ከእነዚያ በአላህ በትክክል ካመኑት ሰዎች ጋር በተገናኙ ጊዜ «እኛም (ልክ እንደ እናንተው) አምነናል» ይላሉ። ወደ ሰይጣኖቻቸው ባገለሉ ጊዜ ደግሞ «እኛ እኮ ከእናንተ ጋር ነን፤ እኛ በእነርሱ ተሳላቂዎች ብቻ ነን» ይላሉ።
अरबी तफ़सीरें:
ٱللَّهُ يَسۡتَهۡزِئُ بِهِمۡ وَيَمُدُّهُمۡ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ
15. አላህ በእነርሱ ይሳለቅባቸዋል:: በአመጻቸዉም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ ያቆያቸዋል፡፡
अरबी तफ़सीरें:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ ٱشۡتَرَوُاْ ٱلضَّلَٰلَةَ بِٱلۡهُدَىٰ فَمَا رَبِحَت تِّجَٰرَتُهُمۡ وَمَا كَانُواْ مُهۡتَدِينَ
16. እነዚህ እነዚያ ስህተትን በቅንነት የገዙ (የለወጡ) ሰዎች ናቸው:: እናም ንግዳቸው ትርፋማ አይደለም:: ቅኑን መንገድም አልተከተሉም፡፡
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: अल्-ब-क़-रा
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी द्वारा प्रकाशित.

बंद करें