Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

अर्थों का अनुवाद सूरा: अल्-ह़ज्ज   आयत:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ سَخَّرَ لَكُم مَّا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَٱلۡفُلۡكَ تَجۡرِي فِي ٱلۡبَحۡرِ بِأَمۡرِهِۦ وَيُمۡسِكُ ٱلسَّمَآءَ أَن تَقَعَ عَلَى ٱلۡأَرۡضِ إِلَّا بِإِذۡنِهِۦٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِٱلنَّاسِ لَرَءُوفٞ رَّحِيمٞ
65. አላህ በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ ለእናንተ የገራላችሁ መርከቦችንም በባህር ውስጥ በፈቃዱ የሚንሻለሉ ሲሆኑ የገራላችሁ መሆኑን፤ ሰማይንም በፈቃዱ ካልሆነ በምድር ላይ እንዳትወድቅ የሚይዛት መሆኑን አላየህምን? አላህ ለሰዎች በእርግጥ ሩህሩህና አዛኝ ነውና::
अरबी तफ़सीरें:
وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَحۡيَاكُمۡ ثُمَّ يُمِيتُكُمۡ ثُمَّ يُحۡيِيكُمۡۗ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَكَفُورٞ
66. እርሱም ያ ህያው ያደረጋችሁ ነው:: ከዚያም ይገድላችኋል:: ከዚያም ህያው ያደርጋችኋል:: ሰው በእርግጥ በጣም ከሓዲ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
لِّكُلِّ أُمَّةٖ جَعَلۡنَا مَنسَكًا هُمۡ نَاسِكُوهُۖ فَلَا يُنَٰزِعُنَّكَ فِي ٱلۡأَمۡرِۚ وَٱدۡعُ إِلَىٰ رَبِّكَۖ إِنَّكَ لَعَلَىٰ هُدٗى مُّسۡتَقِيمٖ
67. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለየህዝቡ ሁሉ እነርሱ የሚሰሩበት የሆነን ስርዓተ ሃይማኖት አድርገናል:: ስለዚህ በነገሩ አይከራከሩህ:: ወደ ጌታህ መንገድም ጥራ:: አንተ በእርግጥ በቅኑ መመርያ ላይ ነህና።
अरबी तफ़सीरें:
وَإِن جَٰدَلُوكَ فَقُلِ ٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا تَعۡمَلُونَ
68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢከራከሩህም (እንዲህ) በላቸው: «አላህ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነው።
अरबी तफ़सीरें:
ٱللَّهُ يَحۡكُمُ بَيۡنَكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فِيمَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ
69. «አላህ በትንሳኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትለያዩበት (ትወዛገቡበት) በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል።» (በላቸው)
अरबी तफ़सीरें:
أَلَمۡ تَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّ ذَٰلِكَ فِي كِتَٰبٍۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ
70. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መሆኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ እውነት ነው:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው::
अरबी तफ़सीरें:
وَيَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَمۡ يُنَزِّلۡ بِهِۦ سُلۡطَٰنٗا وَمَا لَيۡسَ لَهُم بِهِۦ عِلۡمٞۗ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِن نَّصِيرٖ
71. ከአላህ ሌላም ምንም ማስረጃን ያላወረደበትንና ለእነርሱም በእርሱ እውቀት የሌላቸውን ነገር ያመልካሉ፤ ለበዳዮች ምንም ረዳት የላቸዉም::
अरबी तफ़सीरें:
وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٖ تَعۡرِفُ فِي وُجُوهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلۡمُنكَرَۖ يَكَادُونَ يَسۡطُونَ بِٱلَّذِينَ يَتۡلُونَ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتِنَاۗ قُلۡ أَفَأُنَبِّئُكُم بِشَرّٖ مِّن ذَٰلِكُمُۚ ٱلنَّارُ وَعَدَهَا ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ
72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጻችን የተብራሩ ሆነው በእነርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ በእነዚያ በአላህ በካዱት ሰዎች ፊት ላይ ጥላቻን ታውቃለህ:: በእነዚያ አናቅጻችንን በሚያነቡት ላይም በኃይል ሊተናኮሏቸው ይቃረባሉ:: ይልቅ ከዚህ የከፋን ነገር ልንገራችሁን? እርሷም እሳት ናት:: አላህ ለእነዚያ በርሱ ለካዱት ሰዎች ሁሉ ቀጥሯታል:: መመለሻነቷ ምን ይከፋ በላቸው::
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: अल्-ह़ज्ज
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी की ओर से निर्गत.

बंद करें