Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची


अर्थों का अनुवाद सूरा: आले इम्रान   आयत:
فَٱسۡتَجَابَ لَهُمۡ رَبُّهُمۡ أَنِّي لَآ أُضِيعُ عَمَلَ عَٰمِلٖ مِّنكُم مِّن ذَكَرٍ أَوۡ أُنثَىٰۖ بَعۡضُكُم مِّنۢ بَعۡضٖۖ فَٱلَّذِينَ هَاجَرُواْ وَأُخۡرِجُواْ مِن دِيَٰرِهِمۡ وَأُوذُواْ فِي سَبِيلِي وَقَٰتَلُواْ وَقُتِلُواْ لَأُكَفِّرَنَّ عَنۡهُمۡ سَيِّـَٔاتِهِمۡ وَلَأُدۡخِلَنَّهُمۡ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ ثَوَابٗا مِّنۡ عِندِ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ عِندَهُۥ حُسۡنُ ٱلثَّوَابِ
195. እናም ጌታቸው «እኔ ከናንተ ውስጥ የወንድንም ሆነ የሴትን መልካም ስራ ወሮታ አላጠፋም:: ከፊላችሁ የከፊሉ አካል ነው።» በማለት ልመናቸውን ተቀበላቸው:: እነዚያ ለዲን ሲሉ የተሰደዱ፣ ከአገሮቻቸዉም በግፍ የተባረሩ፣ በመንገዴም (ሁከት የደረሰባቸው)፣ የተጠቁ፣ የተጋደሉ እና የተገደሉም ክፉ ስራዎቻቸውን አብስላቸዋለሁ:: በስሮቻቸዉም ወንዞች የሚፈሰባቸውን ገነቶች አስገባቸዋለሁ:: እነርሱም ከአላህ ዘንድ የሆነን ከፍተኛ ምንዳ ይመነዳሉ:: አላህ እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አለና::
अरबी तफ़सीरें:
لَا يَغُرَّنَّكَ تَقَلُّبُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فِي ٱلۡبِلَٰدِ
196. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የእነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች በየአገሮች መንፈላሰስ አያታልህ።
अरबी तफ़सीरें:
مَتَٰعٞ قَلِيلٞ ثُمَّ مَأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمِهَادُ
197. አነስተኛ ጥቅም ነው። ከዚያ መኖሪያቸው ገሀነም ናት:: ገሀነም ደግሞ ማረፊያነቷ ምን ትከፋ!
अरबी तफ़सीरें:
لَٰكِنِ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ رَبَّهُمۡ لَهُمۡ جَنَّٰتٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا نُزُلٗا مِّنۡ عِندِ ٱللَّهِۗ وَمَا عِندَ ٱللَّهِ خَيۡرٞ لِّلۡأَبۡرَارِ
198. እነዚያ ጌታቸውን የፈሩት ግን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ዘወታሪዎች ሲሆኑ አላህ ዘንድ የተሰጡ መስተንግዶዎች አሏቸው:: አላህ ዘንድ ያለውም ምንዳ ለበጎ ሰሪዎች ሁሉ በላጭ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
وَإِنَّ مِنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ لَمَن يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيۡكُمۡ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيۡهِمۡ خَٰشِعِينَ لِلَّهِ لَا يَشۡتَرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ ثَمَنٗا قَلِيلًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ أَجۡرُهُمۡ عِندَ رَبِّهِمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلۡحِسَابِ
199. ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል አላህን ፈሪዎችና በአላህ አናቅጽም ጥቂትን ዋጋ የማይለውጡ ሲሆኑ በአላህና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው ቁርኣን በዚያም ወደ እነርሱ በተወረዱት ልዩ ልዩ መጽሐፍት የሚያምኑ ሰዎች አሉ:: እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ተገቢው ምንዳቸው አለላቸው አላህ ምርመራው ፈጣን ነው::
अरबी तफ़सीरें:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱصۡبِرُواْ وَصَابِرُواْ وَرَابِطُواْ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ
200. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእሳት ቅጣት ትድኑ ዘንድ ታገሱ፣ ተበራቱም፣ በጦር ኬላ ላይ ሆናችሁም ሶላትን ተጠባበቁ:: አላህንም በትክክል ፍሩ::
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: आले इम्रान
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी द्वारा प्रकाशित.

बंद करें