क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - الترجمة الأمهرية - زين * - अनुवादों की सूची


अर्थों का अनुवाद सूरा: सूरा अद्-दुख़ान   आयत:

ሱረቱ አድ ዱኻን

حمٓ
1. ሓ፤ ሚይም፤
अरबी तफ़सीरें:
وَٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُبِينِ
2. ሁሉን ነገር አብራሪ በሆነው መጽሐፍ እንምላለን::
अरबी तफ़सीरें:
إِنَّآ أَنزَلۡنَٰهُ فِي لَيۡلَةٖ مُّبَٰرَكَةٍۚ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينَ
3. እኛ ቁርኣኑን በዚያች በተባረከችው ሌሊት ውስጥ አወረድነው:: እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና::
अरबी तफ़सीरें:
فِيهَا يُفۡرَقُ كُلُّ أَمۡرٍ حَكِيمٍ
4. በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይለያል::
अरबी तफ़सीरें:
أَمۡرٗا مِّنۡ عِندِنَآۚ إِنَّا كُنَّا مُرۡسِلِينَ
5. ከእኛ ዘንድ የሆነ ትዕዛዝ ሲሆን አወረድነው:: እኛ መልዕክተኞችን ላኪዎች ነበርንና::
अरबी तफ़सीरें:
رَحۡمَةٗ مِّن رَّبِّكَۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
6. (መልዕክተኞች) ከጌታህ በሆነው ችሮታ (ተላኩ)። እነሆ እርሱ(አላህ) የሚባለዉን ሁሉ ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና::
अरबी तफ़सीरें:
رَبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَآۖ إِن كُنتُم مُّوقِنِينَ
7. የሰማያት፤ የምድር እና በመካከላቸው ያሉ ነገሮች ሁሉ ጌታ ከሆነው (ተላኩ)። የምታረጋግጡ እንደሆናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መሆኑን እወቁ)::
अरबी तफ़सीरें:
لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۖ رَبُّكُمۡ وَرَبُّ ءَابَآئِكُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ
8. ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም። ህያው ያደርጋል። ህይወትም ይነሳል። ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
بَلۡ هُمۡ فِي شَكّٖ يَلۡعَبُونَ
9. በእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲሆኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው::
अरबी तफ़सीरें:
فَٱرۡتَقِبۡ يَوۡمَ تَأۡتِي ٱلسَّمَآءُ بِدُخَانٖ مُّبِينٖ
10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ( ሰዎችን) የሚሸፍን በሆነ ግልጽ ጭስ ሰማይ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ::
अरबी तफ़सीरें:
يَغۡشَى ٱلنَّاسَۖ هَٰذَا عَذَابٌ أَلِيمٞ
11.ሰዎችን ይሸፍናል ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው::
अरबी तफ़सीरें:
رَّبَّنَا ٱكۡشِفۡ عَنَّا ٱلۡعَذَابَ إِنَّا مُؤۡمِنُونَ
12. ጌታችን ሆይ! ክእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን:: እኛ ትክክለኛ አማኞች ነንና (ይላሉ::)
अरबी तफ़सीरें:
أَنَّىٰ لَهُمُ ٱلذِّكۡرَىٰ وَقَدۡ جَآءَهُمۡ رَسُولٞ مُّبِينٞ
13. አስረጂ መልዕክተኛ የመጣላቸው እና በአላህ የካዱ ሲሆኑ (ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል?
अरबी तफ़सीरें:
ثُمَّ تَوَلَّوۡاْ عَنۡهُ وَقَالُواْ مُعَلَّمٞ مَّجۡنُونٌ
14. ከዚያም «ከሰው የተስተማረ እብድ ነው» ያሉ ሲሆኑ ከእርሱ ዞሩ።
अरबी तफ़सीरें:
إِنَّا كَاشِفُواْ ٱلۡعَذَابِ قَلِيلًاۚ إِنَّكُمۡ عَآئِدُونَ
15. እኛ ቅጣትን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን። እናንተ ግን ወደ ክህደታችሁ በእርግጥ አንደገና ተመላሾች ናችሁ::
अरबी तफ़सीरें:
يَوۡمَ نَبۡطِشُ ٱلۡبَطۡشَةَ ٱلۡكُبۡرَىٰٓ إِنَّا مُنتَقِمُونَ
16. ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን እኛ ተበቃዮች ነን።
अरबी तफ़सीरें:
۞ وَلَقَدۡ فَتَنَّا قَبۡلَهُمۡ قَوۡمَ فِرۡعَوۡنَ وَجَآءَهُمۡ رَسُولٞ كَرِيمٌ
17. ከእነርሱ በፊት የፈርዖንን ህዝቦች በእርግጥ ሞከርን:: ክቡር መልዕክተኛም መጣላቸው::
अरबी तफ़सीरें:
أَنۡ أَدُّوٓاْ إِلَيَّ عِبَادَ ٱللَّهِۖ إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ
18. «የአላህን ባሮች ወደ እኔ አድርሱ (ለኔ ስጡኝ):: እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝና።
अरबी तफ़सीरें:
وَأَن لَّا تَعۡلُواْ عَلَى ٱللَّهِۖ إِنِّيٓ ءَاتِيكُم بِسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٖ
19. «በአላህም ላይ ላትኮሩ። እኔ ግልጽ የሆነን አስረጂ ያመጣሁላችሁ ነኝና በማለት መጣላቸው።
अरबी तफ़सीरें:
وَإِنِّي عُذۡتُ بِرَبِّي وَرَبِّكُمۡ أَن تَرۡجُمُونِ
20. «እኔ እንዳትወግሩኝ በጌታዬና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ።
अरबी तफ़सीरें:
وَإِن لَّمۡ تُؤۡمِنُواْ لِي فَٱعۡتَزِلُونِ
21. «በእኔም ባታምኑ ራቁኝ። ተውኝ።» አለ::
अरबी तफ़सीरें:
فَدَعَا رَبَّهُۥٓ أَنَّ هَٰٓؤُلَآءِ قَوۡمٞ مُّجۡرِمُونَ
22. «ቀጥሎም እነዚህ አመጸኞች ህዝቦች ናቸው (አጥፋቸው)።» ሲል ጌታውን ለመነ።
अरबी तफ़सीरें:
فَأَسۡرِ بِعِبَادِي لَيۡلًا إِنَّكُم مُّتَّبَعُونَ
23. (ጌታዉም አለ) «ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ሂድ። እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና።
अरबी तफ़सीरें:
وَٱتۡرُكِ ٱلۡبَحۡرَ رَهۡوًاۖ إِنَّهُمۡ جُندٞ مُّغۡرَقُونَ
24. «ባህሩንም የተከፈተ ሆኖ ተወው፤ እነርሱ የሚሰምጡ ሰራዊት ናቸውና» አለው።
अरबी तफ़सीरें:
كَمۡ تَرَكُواْ مِن جَنَّٰتٖ وَعُيُونٖ
25. ከአትክልቶችና ከምንጮች ብዙ ነገሮችን ትተው ሄዱ።
अरबी तफ़सीरें:
وَزُرُوعٖ وَمَقَامٖ كَرِيمٖ
26. ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም
अरबी तफ़सीरें:
وَنَعۡمَةٖ كَانُواْ فِيهَا فَٰكِهِينَ
27. በእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ትተው ሞቱ)።
अरबी तफ़सीरें:
كَذَٰلِكَۖ وَأَوۡرَثۡنَٰهَا قَوۡمًا ءَاخَرِينَ
28. ነገሩ ልክ እንደዚህ ሆነ፤ ለሌሎች ህዝቦች አወረስናትም።
अरबी तफ़सीरें:
فَمَا بَكَتۡ عَلَيۡهِمُ ٱلسَّمَآءُ وَٱلۡأَرۡضُ وَمَا كَانُواْ مُنظَرِينَ
29. ሰማይና ምድር በእነርሱ ላይ አላለቀሱም:: የሚቆዩም አልነበሩም::
अरबी तफ़सीरें:
وَلَقَدۡ نَجَّيۡنَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ مِنَ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡمُهِينِ
30. የኢስራኢል ልጆችን ከዚያ አዋራጅ ከሆነው ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው::
अरबी तफ़सीरें:
مِن فِرۡعَوۡنَۚ إِنَّهُۥ كَانَ عَالِيٗا مِّنَ ٱلۡمُسۡرِفِينَ
31. ከፈርዖን እርሱ (ፈርዖውን) የኮራ ከወሰን አላፊዎችም አንዱ ነበርና::
अरबी तफ़सीरें:
وَلَقَدِ ٱخۡتَرۡنَٰهُمۡ عَلَىٰ عِلۡمٍ عَلَى ٱلۡعَٰلَمِينَ
32. ከማወቅም ጋር ከዓለም ህዝቦች መካከል በእርግጥ መረጥናቸው::
अरबी तफ़सीरें:
وَءَاتَيۡنَٰهُم مِّنَ ٱلۡأٓيَٰتِ مَا فِيهِ بَلَٰٓؤٞاْ مُّبِينٌ
33. ከተአምራቶችም በውስጡ ግልጽ የሆነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው::
अरबी तफ़सीरें:
إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَيَقُولُونَ
34. እነዚህ (የመካ ካሓዲያን) በእርግጥ ይላሉ:
अरबी तफ़सीरें:
إِنۡ هِيَ إِلَّا مَوۡتَتُنَا ٱلۡأُولَىٰ وَمَا نَحۡنُ بِمُنشَرِينَ
35. «እርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ (ሌላ) አይደለችም። እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም።
अरबी तफ़सीरें:
فَأۡتُواْ بِـَٔابَآئِنَآ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
36. «እውነተኞችም እንደሆናችሁ አባቶቻችንን እስቲ አምጡልን።» (ይላሉ)
अरबी तफ़सीरें:
أَهُمۡ خَيۡرٌ أَمۡ قَوۡمُ تُبَّعٖ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ أَهۡلَكۡنَٰهُمۡۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ مُجۡرِمِينَ
37. እነርሱ በላጮች ናቸውን? ወይስ የቱበዕ ህዝቦችና እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት? እነርሱን አጠፋናቸው። እነርሱ አመጸኞች ነበሩ።
अरबी तफ़सीरें:
وَمَا خَلَقۡنَا ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَا لَٰعِبِينَ
38. ሰማያትና ምድርን በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ሆነን አልፈጠርንም::
अरबी तफ़सीरें:
مَا خَلَقۡنَٰهُمَآ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
39. ሁለቱንም በቁምነገር እንጂ አልፈጠርናቸዉም:: ግን አብዛሀኞቻቸው አያውቀዉም::
अरबी तफ़सीरें:
إِنَّ يَوۡمَ ٱلۡفَصۡلِ مِيقَٰتُهُمۡ أَجۡمَعِينَ
40. የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው::
अरबी तफ़सीरें:
يَوۡمَ لَا يُغۡنِي مَوۡلًى عَن مَّوۡلٗى شَيۡـٔٗا وَلَا هُمۡ يُنصَرُونَ
41. ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት እነርሱም የማይረዱበት ቀን ነው::
अरबी तफ़सीरें:
إِلَّا مَن رَّحِمَ ٱللَّهُۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
42. አላህ ያዘነለትና ያመነ ብቻ ሲቀር:: (እርሱ ይረዳል) እርሱ (አላህ) ሁሉን አሸናፊና አዛኝ ነውና::
अरबी तफ़सीरें:
إِنَّ شَجَرَتَ ٱلزَّقُّومِ
43. የዘቁም ዛፍ
अरबी तफ़सीरें:
طَعَامُ ٱلۡأَثِيمِ
44. የኃጢአተኞች ምግብ ናት::
अरबी तफ़सीरें:
كَٱلۡمُهۡلِ يَغۡلِي فِي ٱلۡبُطُونِ
45. እሱም ልክ እንደ ዘይት አተላ በሆዶች ውስጥ ይፈላል።
अरबी तफ़सीरें:
كَغَلۡيِ ٱلۡحَمِيمِ
46. እንደገነፈለ ውሃ አፈላል የሚፈላ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
خُذُوهُ فَٱعۡتِلُوهُ إِلَىٰ سَوَآءِ ٱلۡجَحِيمِ
47. ያዙትና ወደ ገሀነም መካከል (ውስጥ) በሀይል ጎትቱት (ገፍትሩት)::
अरबी तफ़सीरें:
ثُمَّ صُبُّواْ فَوۡقَ رَأۡسِهِۦ مِنۡ عَذَابِ ٱلۡحَمِيمِ
48. ከዚያም በራሱ ላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡበት::
अरबी तफ़सीरें:
ذُقۡ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡكَرِيمُ
49. (ይባላልም) «ቅመስ አንተ አሸናፊው፤ ክቡር የነበርክ ነህና።
अरबी तफ़सीरें:
إِنَّ هَٰذَا مَا كُنتُم بِهِۦ تَمۡتَرُونَ
50. «ይህ ያ በእርሱ ትጠራጠሩበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)::
अरबी तफ़सीरें:
إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي مَقَامٍ أَمِينٖ
51. ጥንቁቆች በእርግጥ በደህናማ መኖሪያ ውስጥ ናቸው::
अरबी तफ़सीरें:
فِي جَنَّٰتٖ وَعُيُونٖ
52. በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው::
अरबी तफ़सीरें:
يَلۡبَسُونَ مِن سُندُسٖ وَإِسۡتَبۡرَقٖ مُّتَقَٰبِلِينَ
53. ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሆነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ::
अरबी तफ़सीरें:
كَذَٰلِكَ وَزَوَّجۡنَٰهُم بِحُورٍ عِينٖ
54. ነገሩ ልክ እንደዚህ ነው። ዓይናማዎች የሆኑን ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን::
अरबी तफ़सीरें:
يَدۡعُونَ فِيهَا بِكُلِّ فَٰكِهَةٍ ءَامِنِينَ
55. በእርሷ ውስጥም የተማመኑ ሆነው ከፍራፍሬ ሁሉ ያዛሉ::
अरबी तफ़सीरें:
لَا يَذُوقُونَ فِيهَا ٱلۡمَوۡتَ إِلَّا ٱلۡمَوۡتَةَ ٱلۡأُولَىٰۖ وَوَقَىٰهُمۡ عَذَابَ ٱلۡجَحِيمِ
56. የፊተኛይቱን ሞት እንጂ ዳግመኛ በእርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም:: የገሀነምንም ቅጣት አላህ ጠብቋቸዋል።
अरबी तफ़सीरें:
فَضۡلٗا مِّن رَّبِّكَۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ
57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ይህም ) ከጌታህ (አላህ) የሆነ ትሩፋት ሲሆን ይህም እርሱ ታላቁ እድል ነው::
अरबी तफ़सीरें:
فَإِنَّمَا يَسَّرۡنَٰهُ بِلِسَانِكَ لَعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ
58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣኑንም በቋንቋህ ያገራነው ህዝቦች ይገነዘቡት ዘንድ ብቻ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
فَٱرۡتَقِبۡ إِنَّهُم مُّرۡتَقِبُونَ
59. ተጠባበቅ:: እነርሱም ተጠባባቂዎች ናቸውና::
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: सूरा अद्-दुख़ान
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - الترجمة الأمهرية - زين - अनुवादों की सूची

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

बंद करें