Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

अर्थों का अनुवाद सूरा: अल्-माइदा   आयत:
مِنۡ أَجۡلِ ذَٰلِكَ كَتَبۡنَا عَلَىٰ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ أَنَّهُۥ مَن قَتَلَ نَفۡسَۢا بِغَيۡرِ نَفۡسٍ أَوۡ فَسَادٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ ٱلنَّاسَ جَمِيعٗا وَمَنۡ أَحۡيَاهَا فَكَأَنَّمَآ أَحۡيَا ٱلنَّاسَ جَمِيعٗاۚ وَلَقَدۡ جَآءَتۡهُمۡ رُسُلُنَا بِٱلۡبَيِّنَٰتِ ثُمَّ إِنَّ كَثِيرٗا مِّنۡهُم بَعۡدَ ذَٰلِكَ فِي ٱلۡأَرۡضِ لَمُسۡرِفُونَ
32. በዚህ ምክንያት በኢስራኢል ልጆች ላይ «አንዲትን ንጹህ ነፍስን (ያልገደለችን) ወይም በምድር ላይ ምንንም ያላጠፋችን ነፍስ የገደለ ሁሉ ሰዎችን ሁሉ እንደገደለ ነው:: አንዲትን ነፍስ ህያው ያደረጋትም ሰዎችን ሁሉ ህያው እንዳደረገ ነው።» ማለትን ደነገግን። መልዕክተኞቻችንም ግልጽን ተዐምራት አምጥተውላቸዋል። ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ብዙዎቹ በምድር ላይ ወሰንን አላፊዎች ናቸው።
अरबी तफ़सीरें:
إِنَّمَا جَزَٰٓؤُاْ ٱلَّذِينَ يُحَارِبُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَيَسۡعَوۡنَ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَسَادًا أَن يُقَتَّلُوٓاْ أَوۡ يُصَلَّبُوٓاْ أَوۡ تُقَطَّعَ أَيۡدِيهِمۡ وَأَرۡجُلُهُم مِّنۡ خِلَٰفٍ أَوۡ يُنفَوۡاْ مِنَ ٱلۡأَرۡضِۚ ذَٰلِكَ لَهُمۡ خِزۡيٞ فِي ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ
33. የእነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚዋጉ፤ በምድርም ላይ ለጥፋት የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ቅጣት መገደል ወይም መሰቀል ወይም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቆረጥ ወይም ከሀገር መባረር ነው:: ይህ ቅጣት ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት ነው:: በመጨረሻይቱም ዓለም ከባድ ቅጣት አለባቸው::
अरबी तफ़सीरें:
إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُواْ مِن قَبۡلِ أَن تَقۡدِرُواْ عَلَيۡهِمۡۖ فَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
34. (ሙስሊሞች ሆይ!) (ይህ ተግባር የሚፈጸመው) እነዚያ በእነርሱ ላይ ከመቻላችሁ በፊት የተጸጸቱት ሲቀሩ (ነው)፤ አላህም መሀሪና አዛኝ መሆኑን እወቁ።
अरबी तफ़सीरें:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱبۡتَغُوٓاْ إِلَيۡهِ ٱلۡوَسِيلَةَ وَجَٰهِدُواْ فِي سَبِيلِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ
35. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: ወደ እርሱም የሚያቀርባችሁን ነገር ሁሉ ፈልጉ:: ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ላይ ብቻ ታገሉ::
अरबी तफ़सीरें:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوۡ أَنَّ لَهُم مَّا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا وَمِثۡلَهُۥ مَعَهُۥ لِيَفۡتَدُواْ بِهِۦ مِنۡ عَذَابِ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَا تُقُبِّلَ مِنۡهُمۡۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
36. እነዚያ የካዱት በምድር ላይ ያለ ነገርን ሁሉ እና ከርሱ ጋርም መሰሉ ተጨምሮላቸው ከትንሳኤ ቀን ቅጣት ነፃ ለመሆን እርሱን ቤዛ ቢሰጡ እንኳን ተቀባይነት አያገኙም። ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: अल्-माइदा
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी की ओर से निर्गत.

बंद करें