Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची


अर्थों का अनुवाद सूरा: क़ाफ़   आयत:

ቃፍ

قٓۚ وَٱلۡقُرۡءَانِ ٱلۡمَجِيدِ
1. ቃፍ ፤ በተከበረው ቁርኣን እምላለሁ::
अरबी तफ़सीरें:
بَلۡ عَجِبُوٓاْ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٞ مِّنۡهُمۡ فَقَالَ ٱلۡكَٰفِرُونَ هَٰذَا شَيۡءٌ عَجِيبٌ
2. ይልቁንም ከእነርሱ መካከል የሆነ አስፈራሪ ስለ መጣላቸው ተደነቁ:: ከሓዲያንም አሉ: «ይህ አስደናቂ ነገር ነው።
अरबी तफ़सीरें:
أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗاۖ ذَٰلِكَ رَجۡعُۢ بَعِيدٞ
3. «በሞትንና አፈር በሆንን ጊዜ እንመለሳለንን? ይህ ሩቅ የሆነ መመለስ ነው።» አሉ።
अरबी तफ़सीरें:
قَدۡ عَلِمۡنَا مَا تَنقُصُ ٱلۡأَرۡضُ مِنۡهُمۡۖ وَعِندَنَا كِتَٰبٌ حَفِيظُۢ
4. ከእነርሱ አካል ምድር የምታጎድለውን በእርግጥ አውቀናል:: እኛም ዘንድ ጠባቂ መጽሐፍ አለ::
अरबी तफ़सीरें:
بَلۡ كَذَّبُواْ بِٱلۡحَقِّ لَمَّا جَآءَهُمۡ فَهُمۡ فِيٓ أَمۡرٖ مَّرِيجٍ
5. ይልቁንም ቁርኣን በመጣላቸው ጊዜ አስተባበሉ። እነርሱም በተምታታ ነገር ውስጥ ናቸው።
अरबी तफ़सीरें:
أَفَلَمۡ يَنظُرُوٓاْ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَوۡقَهُمۡ كَيۡفَ بَنَيۡنَٰهَا وَزَيَّنَّٰهَا وَمَا لَهَا مِن فُرُوجٖ
6. ወደ ሰማይም ከበላያቸው ስትሆን ለእርሷ ምንም ቀዳዳዎች የሌሏቸው ሆነው እንዴት እንደገነባናትና በከዋክብት እንዳጌጥናት አልተመለከቱምን?
अरबी तफ़सीरें:
وَٱلۡأَرۡضَ مَدَدۡنَٰهَا وَأَلۡقَيۡنَا فِيهَا رَوَٰسِيَ وَأَنۢبَتۡنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوۡجِۭ بَهِيجٖ
7. ምድርም ዘረጋናት በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት :: በውስጧም ከሚያስደስት አይነት ሁሉ አበቀልን::
अरबी तफ़सीरें:
تَبۡصِرَةٗ وَذِكۡرَىٰ لِكُلِّ عَبۡدٖ مُّنِيبٖ
8. ይህንን ያደረግነው ተመላሽ ለሆነ ባሪያ ሁሉ ለማሳየትና ለማስገንዘብ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
وَنَزَّلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ مُّبَٰرَكٗا فَأَنۢبَتۡنَا بِهِۦ جَنَّٰتٖ وَحَبَّ ٱلۡحَصِيدِ
9. ከሰማይም ብሩክን ውሃ አወረድን በእርሱም አትክልቶችንና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ አበቀልን::
अरबी तफ़सीरें:
وَٱلنَّخۡلَ بَاسِقَٰتٖ لَّهَا طَلۡعٞ نَّضِيدٞ
10. ዘንባባንም ረዣዥም ለእርሷ የተደራረበ እንቡጥ ያላት ስትሆን አበቀልን::
अरबी तफ़सीरें:
رِّزۡقٗا لِّلۡعِبَادِۖ وَأَحۡيَيۡنَا بِهِۦ بَلۡدَةٗ مَّيۡتٗاۚ كَذَٰلِكَ ٱلۡخُرُوجُ
11. ለባሮቹ ሲሳይ ትሆን ዘንድ (አዘጋጀናት):: በእርሱም የሞተችን ሀገር ሕያው አደረግንበት:: ከመቃብር መውጣትም ልክ እንደዚሁ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ وَأَصۡحَٰبُ ٱلرَّسِّ وَثَمُودُ
12. ከእነርሱ በፊት የኑህ ህዝቦችና የረስስ ሰዎችም ሰሙድም አስተባበሉ::
अरबी तफ़सीरें:
وَعَادٞ وَفِرۡعَوۡنُ وَإِخۡوَٰنُ لُوطٖ
13. ዓድም ፈርዖንም የሉጥ ወንድሞችም፤
अरबी तफ़सीरें:
وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡأَيۡكَةِ وَقَوۡمُ تُبَّعٖۚ كُلّٞ كَذَّبَ ٱلرُّسُلَ فَحَقَّ وَعِيدِ
14. የጫካው ባለቤቶችም የቱብበዕ ህዝቦችም ሁሉ መልዕክተኞችን አስተባበሉ:: ዛቻየም ተረጋገጠባቸው።
अरबी तफ़सीरें:
أَفَعَيِينَا بِٱلۡخَلۡقِ ٱلۡأَوَّلِۚ بَلۡ هُمۡ فِي لَبۡسٖ مِّنۡ خَلۡقٖ جَدِيدٖ
15. በመጀመሪያው መፍጠር ደከምን? በእውነቱ እነርሱ ከአዲስ መፍጠር በመጠራጠር ውስጥ ናቸው::
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: क़ाफ़
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी द्वारा प्रकाशित.

बंद करें