Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

अर्थों का अनुवाद सूरा: अल्-आराफ़   आयत:
أُبَلِّغُكُمۡ رِسَٰلَٰتِ رَبِّي وَأَنَا۠ لَكُمۡ نَاصِحٌ أَمِينٌ
68. «የጌታዬን መልዕክቶች አደርስላችኋለሁ። እኔም ለእናንተ ታማኝና መካሪ ነኝና።
अरबी तफ़सीरें:
أَوَعَجِبۡتُمۡ أَن جَآءَكُمۡ ذِكۡرٞ مِّن رَّبِّكُمۡ عَلَىٰ رَجُلٖ مِّنكُمۡ لِيُنذِرَكُمۡۚ وَٱذۡكُرُوٓاْ إِذۡ جَعَلَكُمۡ خُلَفَآءَ مِنۢ بَعۡدِ قَوۡمِ نُوحٖ وَزَادَكُمۡ فِي ٱلۡخَلۡقِ بَصۜۡطَةٗۖ فَٱذۡكُرُوٓاْ ءَالَآءَ ٱللَّهِ لَعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ
69. ያስጠነቅቃችሁ ዘንድ ከናንተው መካከል በሆነ ሰው ከጌታችሁ የሆነ ግሳጼ ስለመጣባችሁ ትደነቃላችሁን? ከኑህ ህዝቦች በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በፍጥረትም ግዙፍነትን በጨመረላችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: የሻችሁትን ታገኙ ዘንድ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ::
अरबी तफ़सीरें:
قَالُوٓاْ أَجِئۡتَنَا لِنَعۡبُدَ ٱللَّهَ وَحۡدَهُۥ وَنَذَرَ مَا كَانَ يَعۡبُدُ ءَابَآؤُنَا فَأۡتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
70. «አላህን አንድ አድርገን ብቻውን እንድንገዛውና አባቶቻችን ይገዟቸው የነበሩትን አማልክት እንድንተው መጣህብን? እውነተኛ ከሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት እስቲ አምጣብን።» አሉ።
अरबी तफ़सीरें:
قَالَ قَدۡ وَقَعَ عَلَيۡكُم مِّن رَّبِّكُمۡ رِجۡسٞ وَغَضَبٌۖ أَتُجَٰدِلُونَنِي فِيٓ أَسۡمَآءٖ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّا نَزَّلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٖۚ فَٱنتَظِرُوٓاْ إِنِّي مَعَكُم مِّنَ ٱلۡمُنتَظِرِينَ
71. «ከጌታችሁ የሆነ ቅጣትና ቁጣ በእናንተ ላይ በእውነት ተረጋገጠ:: እናንተና አባቶቻችሁ አማልክት ብላችሁ በጠራችኋቸው ስሞች አላህ በእነርሱ ምንም ማስረጃ ላላወረደባቸው ትከራከሩኛላችሁን? ተጠባበቁ እኔም ከናንተ ጋር ከተጠባባቂዎቹ ነኝና።» አለ::
अरबी तफ़सीरें:
فَأَنجَيۡنَٰهُ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥ بِرَحۡمَةٖ مِّنَّا وَقَطَعۡنَا دَابِرَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَاۖ وَمَا كَانُواْ مُؤۡمِنِينَ
72. እርሱንና እነዚያን አብረውት የነበሩትን በችሮታችን ከቅጣት አዳናቸው::የእነዚያንም በተአምራታችን ያስተባበሉትንና አማኞች ያልነበሩትን መሠረት ቆረጥን፡፡
अरबी तफ़सीरें:
وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمۡ صَٰلِحٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥۖ قَدۡ جَآءَتۡكُم بَيِّنَةٞ مِّن رَّبِّكُمۡۖ هَٰذِهِۦ نَاقَةُ ٱللَّهِ لَكُمۡ ءَايَةٗۖ فَذَرُوهَا تَأۡكُلۡ فِيٓ أَرۡضِ ٱللَّهِۖ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٖ فَيَأۡخُذَكُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
73. ወደ ሰሙድ ህዝቦችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን:: «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም:: እውነተኛ ለመሆኔ ከጌታችሁ የሆነች ምልክት በእርግጥ መጥታላችኋለች:: ይህች ለእናንተ ተዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናትና ተዋት:: በአላህ ምድር ውስጥ እንደፈለገች ትብላ፤ ትጠጣም:: በክፉ አትንኳትም:: አሳማሚ ቅጣት ይይዛችኋልና።» አለ።
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: अल्-आराफ़
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी की ओर से निर्गत.

बंद करें