Check out the new design

Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika * - Daftar isi terjemahan


Terjemahan makna Surah: Gāfir   Ayah:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا رُسُلٗا مِّن قَبۡلِكَ مِنۡهُم مَّن قَصَصۡنَا عَلَيۡكَ وَمِنۡهُم مَّن لَّمۡ نَقۡصُصۡ عَلَيۡكَۗ وَمَا كَانَ لِرَسُولٍ أَن يَأۡتِيَ بِـَٔايَةٍ إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِۚ فَإِذَا جَآءَ أَمۡرُ ٱللَّهِ قُضِيَ بِٱلۡحَقِّ وَخَسِرَ هُنَالِكَ ٱلۡمُبۡطِلُونَ
78. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም መልዕክተኞችን በእርግጥ ልከናል። ከእነርሱ ባንተ ላይ የተረክንልህ አለ:: ከእነርሱም ባንተ ላይ ያልተረክነውም አለ:: ለማንኛዉም መልዕክተኛ በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር ተዓምርን ሊያመጣ አይገባዉም:: የአላህም ትዕዛዝ በመጣ ጊዜ በእውነት ይፈረዳል:: እዚያ ዘንድም አጥፊዎች ይከስራሉ::
Tafsir berbahasa Arab:
ٱللَّهُ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَنۡعَٰمَ لِتَرۡكَبُواْ مِنۡهَا وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ
79. አላህ ያ ለእናንተ ግመልን ከብትንና ፍየልን ከእርሷ ከፊሏን ልትጋልቡ የፈጠረላችሁ ነውና:: ከእርሷም ትበላላችሁ::
Tafsir berbahasa Arab:
وَلَكُمۡ فِيهَا مَنَٰفِعُ وَلِتَبۡلُغُواْ عَلَيۡهَا حَاجَةٗ فِي صُدُورِكُمۡ وَعَلَيۡهَا وَعَلَى ٱلۡفُلۡكِ تُحۡمَلُونَ
80. ለእናተም በርሷ ውስጥ ጥቅሞች አሏችሁ:: በእርሷም ላይ ዕቃን በመጫን በልቦቻችሁ ያሰባችሁትን ጉዳይ ትደርሱ ዘንድ ፈጠረላችሁ። በእርሷም ላይ በመርከቦችም ላይ ትሳፈራላችሁ::
Tafsir berbahasa Arab:
وَيُرِيكُمۡ ءَايَٰتِهِۦ فَأَيَّ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ تُنكِرُونَ
81. ተዓምራትንም ያሳያችኋል:: ታዲያ ከአላህ ተዓምራት መካከል የትኛውን ትክዳላችሁ?
Tafsir berbahasa Arab:
أَفَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَانُوٓاْ أَكۡثَرَ مِنۡهُمۡ وَأَشَدَّ قُوَّةٗ وَءَاثَارٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ فَمَآ أَغۡنَىٰ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ
82. የእነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ፍፃሜ እንዴት እንደነበር ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን ? ከእነርሱ ይበልጥ ብዙዎች በኃይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶችም በጣም ብርቱዎች ነበሩ:: ያም ይሰሩት የነበሩት ለእነርሱ ምንም አልጠቀማቸዉም::
Tafsir berbahasa Arab:
فَلَمَّا جَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَرِحُواْ بِمَا عِندَهُم مِّنَ ٱلۡعِلۡمِ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
83. መልዕክተኞቻቸዉም ተዓምራትን ባመጡላችሁ ጊዜ እነርሱ ዘንድ ባለው ዕውቀት ተደሰቱ:: በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣትም በእነርሱ ላይ ሰፈረባቸው::
Tafsir berbahasa Arab:
فَلَمَّا رَأَوۡاْ بَأۡسَنَا قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَحۡدَهُۥ وَكَفَرۡنَا بِمَا كُنَّا بِهِۦ مُشۡرِكِينَ
84. ብርቱ ቅጣታችንንም ባዩ ጊዜ «በአላህ አንድነት አምነናል በእርሱም እናጋራ በነበርነው ጣዖታት ክደናል» አሉ::
Tafsir berbahasa Arab:
فَلَمۡ يَكُ يَنفَعُهُمۡ إِيمَٰنُهُمۡ لَمَّا رَأَوۡاْ بَأۡسَنَاۖ سُنَّتَ ٱللَّهِ ٱلَّتِي قَدۡ خَلَتۡ فِي عِبَادِهِۦۖ وَخَسِرَ هُنَالِكَ ٱلۡكَٰفِرُونَ
85. ብርቱ ቅጣታችንን ባዩ ጊዜ ማመናቸዉም የሚጠቅማቸው አልነበረም:: የአላህን ደንብ ያችን በባሮቹ ውስጥ ያለፈችውን ተጠንቀቁ:: በዚያ ጊዜም ከሓዲያን ከሰሩ::
Tafsir berbahasa Arab:
 
Terjemahan makna Surah: Gāfir
Daftar surah Nomor Halaman
 
Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika - Daftar isi terjemahan

Terjemahan oleh Muhammad Zain Zahreddin. Diterbitkan oleh Akademi Afrika.

Tutup