Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - Muhammad Sadeq * - 対訳の目次

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

対訳 章: ユースフ章   節:
قَالَ مَعَاذَ ٱللَّهِ أَن نَّأۡخُذَ إِلَّا مَن وَجَدۡنَا مَتَٰعَنَا عِندَهُۥٓ إِنَّآ إِذٗا لَّظَٰلِمُونَ
«ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ያገኘንበትን ሰው እንጂ ሌላን ከመያዝ በአላህ እንጠብቃለን፡፡ እኛ ያን ጊዜ በእርግጥ በዳዮች ነን» አለ፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
فَلَمَّا ٱسۡتَيۡـَٔسُواْ مِنۡهُ خَلَصُواْ نَجِيّٗاۖ قَالَ كَبِيرُهُمۡ أَلَمۡ تَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ أَبَاكُمۡ قَدۡ أَخَذَ عَلَيۡكُم مَّوۡثِقٗا مِّنَ ٱللَّهِ وَمِن قَبۡلُ مَا فَرَّطتُمۡ فِي يُوسُفَۖ فَلَنۡ أَبۡرَحَ ٱلۡأَرۡضَ حَتَّىٰ يَأۡذَنَ لِيٓ أَبِيٓ أَوۡ يَحۡكُمَ ٱللَّهُ لِيۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلۡحَٰكِمِينَ
ከርሱም ተስፋን በቆረጡ ጊዜ የሚመካከሩ ሆነው ገለል አሉ፡፡ ታላቃቸው አለ «አባታቸሁ በናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መታመኛ ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑን ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ ለእኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ (የምስርን) ምድር አልለይም፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
ٱرۡجِعُوٓاْ إِلَىٰٓ أَبِيكُمۡ فَقُولُواْ يَٰٓأَبَانَآ إِنَّ ٱبۡنَكَ سَرَقَ وَمَا شَهِدۡنَآ إِلَّا بِمَا عَلِمۡنَا وَمَا كُنَّا لِلۡغَيۡبِ حَٰفِظِينَ
«ወደ አባታችሁ ተመለሱ በሉትም፡- አባታችን ሆይ! ልጅህ ሰረቀ፡፡ ባወቅነውም ነገር እንጂ አልመሰከርንም፡፡ ሩቁንም ነገር (ምስጢሩን) ዐዋቂዎች አልነበርንም፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
وَسۡـَٔلِ ٱلۡقَرۡيَةَ ٱلَّتِي كُنَّا فِيهَا وَٱلۡعِيرَ ٱلَّتِيٓ أَقۡبَلۡنَا فِيهَاۖ وَإِنَّا لَصَٰدِقُونَ
«ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ፡፡ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን፡፡»
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالَ بَلۡ سَوَّلَتۡ لَكُمۡ أَنفُسُكُمۡ أَمۡرٗاۖ فَصَبۡرٞ جَمِيلٌۖ عَسَى ٱللَّهُ أَن يَأۡتِيَنِي بِهِمۡ جَمِيعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡحَكِيمُ
(ያዕቆብ) «አይደለም ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን ለእናንተ ሸለሙላችሁ፡፡ (ሠራችሁትም)፡፡ መልካምም ትእግስት (ማድረግ) አለብኝ፡፡ እነርሱን (ሦስቱንም) የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል፡፡ እነሆ እርሱ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና» አላቸው፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
وَتَوَلَّىٰ عَنۡهُمۡ وَقَالَ يَٰٓأَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَٱبۡيَضَّتۡ عَيۡنَاهُ مِنَ ٱلۡحُزۡنِ فَهُوَ كَظِيمٞ
ከእነሱም ዘወር አለና «በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ፡፡ ዓይኖቹም ከሐዘን (ለቅሶ) የተነሳ ነጡ፡፡ እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالُواْ تَٱللَّهِ تَفۡتَؤُاْ تَذۡكُرُ يُوسُفَ حَتَّىٰ تَكُونَ حَرَضًا أَوۡ تَكُونَ مِنَ ٱلۡهَٰلِكِينَ
(እነርሱም) «በአላህ እንምላለን፡፡ ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠፊዎቹ እስከምትሆን ድረስ ዩሱፍን ከማውሳት አትወገድም» አሉ፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
قَالَ إِنَّمَآ أَشۡكُواْ بَثِّي وَحُزۡنِيٓ إِلَى ٱللَّهِ وَأَعۡلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ
«ጭንቀቴንና ሐዘኔንና የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ነገር ዐውቃለሁ» አላቸው፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: ユースフ章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - Muhammad Sadeq - 対訳の目次

シェイク・ムハンマド・サディクとムハンマド・アス=サーニー・ハビーブによる翻訳。ルゥワード翻訳事業センター監修

閉じる